@ethiopianservice: «የኑሮ ውድነት ሰማይ ደርሷል፤ መንግሥት ከቁጥር ጨዋታ ይውጣ» ዶ/ር ደሣለኝ ጫኔ፣ በስድስተኛው የፓርላማ ዘመን አምስተኛ ዓመት ማጠቃለያ የመንግሥት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ላይ ጠንከር ያሉ የትችትና የጥያቄ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል። የሕዝብ ተወካዩ ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታና የመንግሥትን መዋቅራዊ ድክመቶች በቅርበት ሲታዘቡ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ዶክተር ደሣለኝ በሪፖርቱ ግምገማ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦ 👉የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የኑሮ ውድነት፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የመግዛት አቅም ያሳጣና መካከለኛውን የኅብረተሰብ መደብ ያጠፋ ስውር ረሃብ መውለዱን ገልጸዋል። መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠሉትን የሰላም እጦቶችና የፖለቲካ ምኅዳሩን መጥበብ ችላ በማለት፣ በኢኮኖሚ ስኬት ስም የቁጥር ጨዋታዎችን እያቀረበ እውነታውን እየሸፈነ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። 👉የትምህርት ሥርዓት መዋቅራዊ ኪሳራ፦ በትምህርት ዘርፍ በኩል የታየውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ92 በመቶ መውደቅ የገለጹት ተወካዩ፣ ይህ አሳሳቢ ውጤት የመንግሥትን የትምህርት ሥርዓት መዋቅራዊ ኪሳራ የሚያሳይ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስትሩ ሊጠየቁበት ይገባል ብለዋል። 👉የሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር፦ በሀገሪቱ ሰብአዊ ቀውስ እያለ የመረጃ ማጥራት በሚል ሰበብ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 2.3 ሚሊዮን ዝቅ ተደርጎ መቅረቡ እውነታውን የማይወክል፣ የፖለቲካ ቁጥር ማሳመሪያ ነው ሲሉ ነቅፈዋል። የቀረቡ የመፍትሔ ሐሳቦች ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ እንደ መፍትሔ ያቀረቡት መንግሥት ትኩረቱን ከኮሪደር ልማትና ከሪዞርቶች ግንባታ በመቀነስ፣ ወደ መሠረታዊ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ወደ ማኅበራዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሞችና ሁሉንም የታጠቁ ኃይሎች ያካተተ እውነተኛ ብሔራዊ የፖለቲካ ድርድር ላይ እንዲያደርግ ነው። በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሮችን በኃይል ከመፍታት ወጥተው፣ ሕዝቡ በአዲሱ የ2019 ዓመተ ምህረት በተግባር ሊያየው የሚችለውን ግልጽ የሰላም የጊዜ ሰሌዳና ቁርጠኝነት እንዲያብራሩ በይፋ ጠይቀዋል። #Ethiopia #AbiyAhmed #Parliament #africa #news

Ethiopian service
Ethiopian service
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 07 July 2026 08:22:38 GMT
4435
71
0
2

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @ethiopianservice, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About