@.fano08: #CapCut ♦ ይህም ይመዝገብ ፦ የሕዝብ አደራን በሐቅ የተወጣው የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አኩሪ የፓርላማ ስንበት! ውጣ ውረዱ በበዛበት፣ ክህደት፣ አታላይነትና ጮሌነት በነገሠበት የሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ የሕዝብን እውነተኛ ውክልና ይዞ በሐቀኝነት መጽናት ቀላል ነገር አይደለም። በአገዛዙ ሥርዓት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚሰነዘሩ ጫናዎችን፣ ግልጽ ዛቻዎችን በጽናት ተቋቁሞ የውክልና ጊዜን እጅግ አኩሪ በሆነ ተግባር መፈጸም የታሪክ ተጋድሎ ነው። ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በፓርላማ ቆይታው ያለመከሰስ መብቱ በሕገ-ወጥ መንገድ ተገርስሶ ከአንድ ወር በላይ ለእስርና ለእንግልት ቢዳረግም ለአፍታም ቢሆን ለሕዝብ ከገባው ቃል ኪዳን ፈቀቅ አላለም። በእርግጥ ዶ/ር ደሳለኝ ገና ከጅምሩ፣ የዛሬ 6 ዓመት በየካቲት ወር ላይ ፦ “እኔ በሊቀመንበርነት ያገለገልኩበት ሁለት ዓመት በቂ ነው ብዬ አስባለሁ። በአዲስ መንፈስ ሥራ ሊሠራ የሚችል አዲስ አመራር እንዲመረጥ አድርገናል። ይህ በግል ፈቃዴ የተደረገ ውሳኔ ነው” በማለት ከአብን የፓርቲ ሊቀመንበርነት በገዛ ፈቃዱ በመልቀቅ ትልቅና ምሳሌያዊ የፖለቲካ ስልጣኔ አሳይቶናል። በኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ፤ የፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን ስንቱ ድርጅት ሲመሰርትና ሲያፈርስ እንዳላየን፣ ወንበር ከመልቀቅ ይልቅ ፓርቲ ማፍረስ ስንቱ መሪ ነኝ ባይ እንደ ቀለለው ፣ ስንት ተስፋ የተጣለባቸው ውህደቶችና ቅንጅቶች “እኔ ሊቀመንበር ካልሆንኩ” በሚል የራስ ወዳድነት አባዜ እንደከሸፉ እያወቅን ፤ ዛሬም ድረስ በተገኘው የፖለቲካ መድረክ ሁሉ መሪ ለመሆን ስንቱ ስብዕናው ቀሎ በታየበት መድረክ ዶ/ር ደሳለኝ ግን የስልጣን ጥምን አሸንፎ ሌላ ታሪክ ሰርቷል ። እርግጥ ነው ! እንዲህ ዓይነት መርህና ትልልቅ ዋጋ የተከፈለበት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከጊዜ ሂደት በኋላ በውስጥ ባሉ የፖለቲካ አድርባዮች ምክንያት ትንሳኤውን ሳይሆን የፖለቲካ ሞቱን አወጀ ። ያኔም ዶ/ር ደሳለኝ እውነቱን ፊት ለፊት ለመናገር አልፈራም “አብን ከዚህ በኋላ ከመኖሩ ይልቅ ባለመኖሩ የአማራን ሕዝብ የሚጠቅም ፓርቲ ነው” በማለት በቁጭት ከፓርቲው ተሰናበተ። ሆኖም ግን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው ውክልና አላበቃም ነበር። ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለወከለው ማኅበረሰብ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ሀገር ለተጋረጡብን መሠረታዊና ውስብስብ ችግሮች መፍትሔ እንዲገኝ በጥናት፣ በመረጃና በማስረጃ በማስደገፍ ሳይታክት በፓርላማው መድረክ ጠንካራ ጥያቄዎችንና ትችቶችን ሲሰነዝር ቆይቷል። እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው፤ ዶ/ር አበባው ደሳለው በተወካዮች ምክር ቤት ያደረገው የዲሞክራሲ ተጋድሎ ፍጹም የሚዘነጋ አለመሆኑን ነው። ዶ/ር አበባውም ከአብን ፓርቲ የለቀቀ ቢሆንም፣ የወከሉትን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለተቀረውም የኢትዮጵያ ሕዝብ እውነተኛ ድምፅ በመሆን፤ በሕዝብ እንደራሴ ምክር ቤት “ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ” በመሆን በታሪክ የሚወሳ ገድል ፈጽሟል። ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ስንገልጽ፣ ስለ አቶ ክርስቲያን ታደለ ምንም ሳይሉ ማለፍ እንዴት ይቻላል?! በፍጹም አይቻልም! በፓርላማው መድረክ ላይ፦ “ጠ/ሚ አብይ፤ ጥያቄ ሲቀረብቦት የወጡበትን ብሔር ከመጥላት አድርገው ይመለከታሉ? በአፍዎ ‘ኢትዮጵያ አትፈርስም’ ይላሉ፣ በድርጊትዎ ግን ያ አይደለም፤ ሥልጣንዎን በመልቀቅ የመፍትሔው አካል አይሆኑም ወይ?!” በማለት አሁን ለገባንበት ምስቅልቅል የፖለቲካ ቀውስ ተጠያቂ ቁጥር አንድ ለሆነው ለአገዛዙ ሥርዓት መሪ ያቀረበው ያ ኃይለኛ ጥያቄ እንዴት ይረሳል?! በፍጹም አይረሳም! እጅግ አሳዛኙ ነገር ክርስቲያን ታደለ በሚያቀርባቸው መሠረታዊ ጥያቄና በፓርላማው ውስጥ ባነሳቸው ሕዝባዊ ጉዳዮች ቂም የያዘው የአገዛዙ ሥርዓት አቶ ክርስቲያን እስካሁን ድረስ በግፍ እስር ቤት እያሰቃየው ይገኛል። የሚያስገርመውና የታሪካችን ትልቁ ምጸት ደግሞ፣ አሁን የአብን ከፍተኛ አመራር ነን ባዮች የሕዝብ ወገንተኛ የሆኑትን ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን፣ አቶ ክርስቲያን ታደለን እና ዶ/ር አበባው ደሳለውን “ከፓርቲው የተባረሩት በስነ-ምግባር ጉድለትና የሻዕቢያን የውክልና እንቅስቃሴ በማካሄዳቸው ነው” በማለት በድፍረትና ያላንዳች ሐፍረት ሲፈርጁ ተሰምተዋል ። በዚህ አደገኛና ርካሽ ፍረጃ ላይ ግንባር ቀደም የነበሩት ግለሰቦች ፤ ዛሬ ላይ በአጋዥነታቸው የአገዛዙ ሥርዓት የመወዳደሪያ ቦታ ለቆላቸው፣ በአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር ተሰጥቷቸው ገብተዋል። ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ሆይ! በዚያ በምክር ቤት መቀመጫህ ላይ ሳታዛንፍ፣ ሳታጎበድድና ለጥቅም ሳትሸነፍ፤ የተገፉ ወገኖችህ እውነተኛ ጩኸት፣ የሕዝብህም ታማኝ ጋሻ ሆነህ ዘልቀሃል። የተሸከምከውን ከባድ ሕዝባዊ አደራ በተግባር አስመስክረህ፤ ጉዞህን በአሸናፊነትና በልዕልና አጠናቀሃል! በአድርባዮች፣ በሆድ አደሮችና በጥቅመኛ ካድሬዎች በተከበበ የፖለቲካ ምስቅልቅል ውስጥ በመጽናትህ ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባሃል። እውነተኛ የሕዝብ ድምጽ በመሆንህ፤ ይህም ይመዝገብ ከልብ እናመሰግናለን 🙏

(A..የነዚያ ዘር)⛪️🤝🕌🇨🇬
(A..የነዚያ ዘር)⛪️🤝🕌🇨🇬
Open In TikTok:
Region: QA
Tuesday 07 July 2026 15:57:36 GMT
15270
2183
162
171

Music

Download

Comments

bdranaga.badreya
Bdranaga badreya naga :
2026-07-08 14:51:30
12
yeshi5269
yeshi :
የኔ ወንድ ጀግና🥰😘😘😘😘
2026-07-08 19:08:32
2
adiiilove2
የጎጃሟ እንቁ ግዮን❤🌾🌻 :
2026-07-08 20:08:06
2
user1113556881224wa
wondered. love :
2026-07-08 04:12:25
3
user6339811854282
ሉባባ በሽር :
የኔ ጀግና
2026-07-09 05:13:24
1
user9067196314216
user9067196314216 :
👑👑❤️
2026-07-08 10:16:48
2
user9067196314216
user9067196314216 :
❤️❤️
2026-07-08 10:16:19
2
wbe455
wbe :
🥰🥰
2026-07-08 19:19:40
1
rahmaraho458
rahmaraho458 :
2026-07-08 15:59:47
1
hawa.imar
Hawa Imarz :
2026-07-08 06:57:46
1
user7104413482635
tigist aymro :
💛
2026-07-08 20:01:53
1
user4116193286715
Abebech :
የኔ ጀግና🥰🥰🥰🥰
2026-07-09 14:57:45
1
soll.kutbir
soll ከወሎ :
2026-07-09 08:12:10
1
hay.hay4879
hayat hayat :
2026-07-08 16:34:36
1
To see more videos from user @.fano08, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About