@mme20252017: ኤልሳቤጥ ኦልደን "ቤቲ" ስኮት የተወለደችው የካቲት 22፣ 1906 ዓ.ም. በሚቺጋን ግዛት፣ አልቢዮን በተባለች ከተማ ሲሆን፣ ያደገችው ግን በቻይና ቺንግታኦ ከተማ ውስጥ ነው። ወላጆቿም ሚስዮናውያን ሲሆኑ ይህ አስተዳደጓም ገና ራሷን ጠንቅቃ ሳታውቅም ጭምር ለወደፊት ጥሪዋ መሠረት የጣለ ነበር። ልጅነቷን በሙሉ በቻይና ባህል ተከባ ያሳለፈች እንዲሁም በቻይና ውስጥ በቻይና ኢን ላንድ ሚሽን አገልግሎት ስራዎች ተከባ ያደገች በመሆኗ፣ ቤቲ ከሌሎች ወጣት አሜሪካውያን ሚስዮናውያን በተለየ ከተልእኮው ሥራ ጋር ጥልቅ ትውውቅ እንዲኖራት አስችሏታል። የሚሲዮን አገልግሎት ጥሪ ቤቲን ወደ ሙሉ ግዜ የሚስዮናዊነት አገልግሎት የመራት መንገድ ወደ ቺካጎ፣ ወደ ሙዲ የመጽሐፍ ቅዱስ ተቋም (Moody Bible Institute) ለሕይወት ዘመኗ አገልግሎት የሚያዘጋጃትን ትምህርት በተከታተለችባቸው አመታት ነበር። ቤቲ ጆን ስታምን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘችው በዚያው በሙዲ ተቋም ለቻይና ሕዝብ ይካሄድ በነበረው የቻይና ኢን ላንድ ሚሽን ያካሂዳቸው በነበሩ የጸሎት ስብሰባዎች ላይ ነበር፤ ጆን ከእሷ በአንድ ዓመት የሚያንስ ተማሪ ነበር። ግንኙነታቸው በኋላ ላይ ለሁለቱም ሕይወትና ሞት ማዕከላዊ ሚና ቢጫወትም፣ ቤቲ ወደ ቻይና የመጓዝ ጥሪዋ ግን ገና ከልጅነቷ ጀምሮ በራሷ እምነትና ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ነው። እግዚአብሔር ወዴት እየመራት እንዳለ ለማወቅ የጆንን ምሳሌ አልፈለገችም ነበር። ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ቤቲ ወደ ሻንጋይ አቀናች፤ በ1931 ዓ.ም. ደግሞ ከቻይና ኢንላንድ ሚሽን አገልግሎት ጋር በመሆን እንደ ሚስዮናዊ ወደ ቻይና ገባች፤ ይህም ጆን ከመድረሱ አንድ ዓመት ቀድሞ ነበር፤ በሚቀጥለውም ዓመት ጆን በመርከብ ተጉዞ ደረሰ ሆኖም መጀመሪያ ላይም የተመደበው በተለየ አካባቢ ነበር። ወደ ትዳር የገባችውም በተለመደው መንገድ ሳይሆን ባልታሰበ የእግዚአብሔር ምሪት የተከናወነ ነበር። ቤቲ መጀመሪያ እንድትሠራበት ታስቦ በነበረው ክልል ውስጥ አንድ ከፍተኛ ልምድ ያለው ሚስዮናዊ በኮሚኒስቶች ተይዞ ነበር። በዚህ ምክንያት የሚሲዮን አገልግሎቱ መሪዎች ቤቲን በጊዜያዊ ጣቢያ እንድትቆይ ወሰኑ፤ በኋላም የጤና እክል አጋጥሟት ወደ ሻንጋይ እንድትሄድ ተደረገች። ከእርሷ ባልሆኑ ተከታታይ ሁነቶችና ባልታቀዱ ክስተቶች ምክንያት ነበር ጆን ወደ ቻይና የደረሰው። በደረሰበትም ወቅት ቤቲ በአጋጣሚ በሻንጋይ ነበረች። ሁለቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንኙነታቸው አድጎና በመካከላቸው ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከአንድ ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከጠበቁት ጊዜ ፈጥነው ተጋቡ። ጆንና ቤቲ የተጋቡት ጥቅምት 25፣ 1933 ዓ.ም. ሲሆን፣ ቤቲ ከጆን በግምት ሁለት ዓመት ያህል ቀደም ብላ በቻይና ውስጥ አገልግላ ስለነበር፣ የቻይና ኢን ላንድ ሚሽን ለጋብቻቸው ፈቃድ ሰጥቷቸዋል። በቻይና የነበራት አገልግሎት ቤቲና ጆን በጋራ የተመደቡት በደቡብ አንዋይ ግዛት በምትገኘው ጂንግደ (ቺንግተህ) ተብላ በምትታወቀው ጣቢያ ነበር፤ ይህችም ጣቢያ ከሻንጋይ 225 ማይል ርቀት ላይ የምትገኝ ስትሆን፣ ለመድረስ ብቻ በጀልባና በየብስ ለሳምንታት የፈጀ አድካሚ ጉዞ ይጠይቅ ነበር። ቺንግተህ ገለልተኛ ከተማ ስትሆን፣ ወደ እርሷ መድረስ የሚቻለው በአስቸጋሪ ተራሮች ጉዞ እና ድንጋያማ መንገዶች ብቻ ነበር፤ ከከተማ ውስጥ ካሉ ምቹ የተልእኮ ጣቢያዎችም እጅግ የራቀች ነበረች። በመስከረም 1934 ዓ.ም. ቤቲ በዉሁ በምትገኝ የሜቶዲስት ሆስፒታል ውስጥ ሔለን ፕሪሲላ የተባለችውን ሴት ልጇን ወለደች—ይህም በእርስ በርስ ጦርነት ስጋት እየተባባሰ በሄደበት ክልል ውስጥ በኑሮ አለመረጋጋት መካከል የተገኘ የደስታ አጋጣሚ ነበር። ከሁለት ወር በኋላ ግን ትንሿ ቤተሰብ ከዉሁ ተነስታ ወደ ቺንግተህ ጣቢያዋ ተመለሰች፤ በዚያም ገና ከሁለት ሳምንት በፊት በደቡብ አንዋይ ለተጀመረ አዲስ የሚስዮናዊነት ሥራ አመራርን ተረክበው ነበር። ይህ አገልግሎትም በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎች ለብዙ ዓመታት ፍሬያማ አገልግሎት እንደሚያስገኝ ተስፋ የጣሉበት ነበር። ይህ ተስፋ ገና እንደ ጀመረ ማለት ይቻላል በአሰቃቂ ሁኔታ ተቋረጠ። በአንድ ጠዋት ቤቲ የሦስት ወር ሕፃኗን ሔለንን እያጠበች ሳለ፣ የቺንግተህ ከተማ ዳኛ ደርሶ የኮሚኒስት ኃይሎች እየተቃረቡ መሆኑን አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው፣ ቤተሰቡም እንዲሸሽ አሳሰበ። ጆን ግን ራሱ ሁኔታውን ለማጣራት ወጣ። ታኅሣሥ 6፣ 1934 ዓ.ም. ቤተሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ጂንግደ እስር ቤት ተወሰደ፤ እዚያም የኮሚኒስት ገዥዎቻቸው ጆንን በግድ አስገድደው ለሻንጋይ የቻይና ኢን ላንድ ሚሽን(CIM) ዋና መሥሪያ ቤት የካሳ ገንዘብ የሚጠይቅ ደብዳቤ አስጻፉት—ይህ ግን ሚሲዮን አገልግሎቱ ካሳ ገንዘብ ላለመክፈል ጽኑ አቋም ስለነበረው፣ ሁለቱም ቤቲና ጆን ፈጽሞ እንደማይሳካ የሚያውቁት ጥያቄ ነበር። የተከፈለ መስዕዋዕትነት ከዚያ በኋላ የተከሰተው ነገር ቤቲ እንደ እናት ያሳየችውን ጽኑ ድፍረት የገለጠ ነበር። እርሷም ባለቤቷም 15 ኪሎሜትር ወደ ምያኦሾ ከተማ በእግር እንዲጓዙ ተገደዱ። በዚያ ምሽት ቤቲ ለሔለን የመጨረሻውን እንክብካቤ እንድታደርግ ተፈቀደላት። በዚያች ቅጽበት ሕፃኗን በማዘያ ውስጥ በድብቅ ደበቀቻት ይህም በኋላ የልጇን ሕይወት ያተረፈ የፍቅርና የእምነት ተግባር ሆነ። በማግስቱ ጆንና ቤቲ ልብሳቸው ተገፎ በምያኦሾ ጎዳናዎች እየተዘባበቱባቸው ወደ ኢግል ሂል ወደተባለው የግድያ ቦታ ተወሰዱ። እጆቻቸው ታስረው ለአጭር ጊዜ አብረው ቆይተው እንዲንበረከኩ ተደረጉ። ጆን መጀመሪያ ተገደለ፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ቤቲ ተከተለችው። ለነፃነታቸው ሲማጸን የነበረው ዣንግ ሹይሸንግ የተባለ ቻይናዊ ክርስቲያንም አብሮ ተገደለ። ሁለቱም በክርስቶስ እምነታቸውና በዘላለም ተስፋ እየመሰከሩ አብረው ሞቱ። ቤቲ ስትሞት ዕድሜዋ ሃያ ስምንት ነበር። እናትነት፣ የተከፈለ መስእዋትነት እና ፍሬ ለሁለት ቀናት የአካባቢው ክርስቲያኖች በምያኦሾ ከተማ ኮረብቶች ተደብቀው ቆዩ። ከእነሱ መካከል ሚስተር ሎ የተባለ ቻይናዊ ወንጌላዊ ነበር፤ የተያዙት ሁለት የውጭ አገር ሰዎች ከእርሱ ጋር ይሠሩ የነበሩት ጆንና ቤቲ መሆናቸውን ቀስ በቀስ አወቀ። ቤቲ ሔለንን ደብቃት ስለነበር፣ ሕፃኗ በፓስተር ሎ ጥረት በተአምር ዳነች፤ ሔለንም አድጋ ታማኝ ክርስቲያን ሆነች የእናቷ የመጨረሻ ጥበቃ ሕያው ውጤት ነበር። ቤቲና ጆን ጥር 2፣ 1935 ዓ.ም. በዉሁ በተከበረ ሥነ ሥርዓት ተቀበሩ፤ ቻይናውያንና የውጭ አገር ክርስቲያን መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የአሜሪካ ቆንስል ተገኝተው ነበር። እነሱም የቻይና ኢን ላንድ ሚሽን ሰባ ሦስተኛና ሰባ አራተኛ ሰማዕታት ሆኑ፤ በመቃብር ድንጋያቸው ላይም መስቀል ተቀርጿል። የአገልግሎት ዘመኗ አጭር ቢሆንም፣ የቤቲ ሞት ከጆን ሞት ጋር ተያይዞ በክርስቲያኑ ዓለም መንፈሳዊ ንቅናቄ ቀሰቀሰ። ዜናውም በፍጥነት ተሰራጨ፤ አንድ የተልእኮ መሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቤቲ እና ጆን ስታም ሞት ምክንያት ለሚስዮናዊነት ሕይወታቸውን እንደሰጡ መሰከረ። አንድ ባልደረባቸውም ለቤቲ ወላጆች በጻፈው ደብዳቤ፣ ለብዙ ዓመታት የተዘረጋ ሕይወት እንኳ ቤቲና ጆን ለክርስቶስ በአንድ ቀን ያከናወኑትን ያህል ማድረግ እንደማይችል ገለጸ። በ1944 ዓ.ም. ወይዘሮ ሃዋርድ ቴይለር "የጆንና የቤቲ ስታም ድል" የተባለውን መጽሐፍ ጻፉ ታሪካቸውንም ለወደፊት ትውልድ አቆዩት።
Mission Mobilization Ethiopia
Region: ET
Thursday 09 July 2026 12:02:26 GMT
Music
Download
Comments
mameda :
2026-07-10 05:28:35
2
kiyu :
2026-07-10 05:13:26
1
BIKU :
🙏🙏🙏🙏 geta legnam endezi aynet zemen yamitalin le wongel arbegna mehon efeligalehugn .
2026-07-21 17:02:54
0
ruhama :
እኔው ነኝ
2026-07-10 08:35:58
1
Tesfansh gizaw :
🙏🙏🙏🙏
2026-07-10 07:55:49
1
Dr. Eshetu E. Tadesse Anjajo :
🥰♥️🥰
2026-07-12 06:49:56
0
Israel :
🥰🥰🥰
2026-07-10 07:07:54
1
Hebrew Elias :
🔥🔥🔥🔥🔥🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-10 00:29:12
1
Mihiret Mihiret :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-10 04:31:29
1
NEW💡LIGHT0911084852APO ESHETU :
🥰🥰🥰🥰🥰🔥
2026-07-10 04:18:10
1
Endirias Yishak :
🥰🥰🥰
2026-07-10 03:11:35
1
Mesay wiz Tona :
🥰🥰
2026-07-09 18:16:25
1
peniel(ጵንኤል) :
🥰🥰🥰🥰
2026-07-09 23:19:02
1
God is love :
🥰🥰🥰
2026-07-09 21:13:47
1
faith and love :
🥰🥰🥰
2026-07-09 22:15:38
1
abrish4jesus :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-09 13:57:48
1
Matusal Churuko :
🙏🙏🙏
2026-07-09 20:48:44
1
ድነት ልጁን በማመን :
🥰🥰🥰
2026-07-09 13:12:46
1
meku me :
🥰🥰🥰
2026-07-09 19:59:53
1
@tameT💙💙💙 :
😭😭😭🙏🙏💪
2026-07-09 15:25:18
1
Dream&success :
🥰🥰🥰
2026-07-21 10:34:10
1
To see more videos from user @mme20252017, please go to the Tikwm
homepage.