@sililsh: የስልጤ ባህል አምባሳደር፦ ድምጻዊ ኑርታታ አማን አዲስ “ኮላሎሬ” የተሰኘ ነጠላ ዜማ ተወዳጅነትን ካተረፉ ሥራዎች አንዱ ሆኖለታል፡፡ በባህላዊ የሙዚቃ ሥራዎቹና በመድረክ ብቃቱ የተመሰከርለት ድምጻዊ ኑርታታ አማን፣ በረጅቶ ዜማ የተሠራውን “ኮላሎሬ” የተሰኘ አዲስ የስልጥኛ ነጠላ ዜማ ለታዳሚዎቹ አድርሷል። ይህ ድንቅ ሥራው በከድር ሁሴን የተገጠመ ሲሆን፣ በታዋቂው አቀናባሪ አማኑኤል የተቀናበረ ነው። በአሁኑ ወቅት የሙዚቃው የተወሰነ ክፍል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቆ በርካታ ተመልካቾችንና አድናቆትን እያገኘ ይገኛል። ኑርታታ አማን (ኑርቴ) እጅግ ከፍተኛ የጥበብ ተሰጥኦና ድንቅ ብቃት ያለው ድምጻዊ ነው። በ1997 ዓ.ም የስልጤ የባህል አምባሳደር የሆነውን “ፈረጃት ባንድ”ን ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ፣ በበርካታ መድረኮች ላይ በመገኘት የስልጤን ባህልና ወግ በሙዚቃ ሥራዎቹ ለማስተዋወቅና ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፤ ብዙም ደክሟል። የድምጻዊው አዲሱ የ“ኮላሎሬ” ሙዚቃ የቪዲዮና የድምጽ ቅንብር (Audio & Video Production) ጥራትና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተሠርቶ መጠናቀቁን ኑርቴ ገልጿል። በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጥራትና አቀናባሪነት ከተሠሩ ነጠላ ዜማዎች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ሥራ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈ ይገኛል። ድምጻዊው በዜማው ውስጥ ወቅታዊና ጠቃሚ መልዕክቶችን እንዲህ እያለ ያስተላልፋል፦ ሀረሽ አቦት እንጃ ድበል ወክት ዬዳን ዛንዜ አትበል የዳንኩለክ ጅግ በባሀ ገዳ ያልፈን ጃዴ በልባሃ የስልጤ እንደት ጠራት ዎልደሽ የጬኜተይ ሊቄር ደውሰሽ ሀየእ ድበል ትታትባዳ እዝነ ዋብ ለስድባዳ ይህ ወቅቱን የጠበቀ የጥበብ ሥራ አርሶ አደር አባቶችና እናቶች ወቅታቸውን ጠብቀው በእርሻ ልማት ላይ እንዲረባረቡ ጥሪ ያቀርባል። በወቅቱ ያልሠራና ጊዜውን በአግባቡ ያልተጠቀመ ሰው መጨረሻው ከንቱ ሆኖ እንደሚቀር በማስገንዘብ ስንፍናን አጥብቆ ያወግዛል። በተጨማሪ ኮላሎሬ ሙዚቃው የተጀመረውና ግጥሙ የተቀናበረው በስልጤኛ ቋንቋ ሲሆን፣ ይዘቱ ከባህላዊው የግብርና ሕይወትና ከስልጤ ማኅበረሰብ ማንነት ጋር የተያያዘ ነው። ኑርታታ ድብቅ ችሎታና አስደናቂ ብቃት ያለው አርቲስት ቢሆንም፣ የኢኮኖሚና የአቅም ጉዳይ ፈተና ሆኖበት እንጂ ከዚህ ቀደም በድምጽ ብቻ የሠራቸውን በርካታ ተወዳጅ ሥራዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል፦ • “አሳዋይ አይን አጄጄሺ ቴ ጣማይ ምንን ጀዋባሽ” • “ነይ የባቦ” • “አሩሺ” • “ነይ ውረጂ አዳናሽ” ቀደም ሲል የመጀመሪያው የዜማ ስብስብ በ1997 ወራቤ ከተማ የስልጤ ልማት ማኅበር (ስልማ) ሆስፒታል ለመገንባት ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ወቅት ከፈረጃት ባንድ ጋር በጋራ በማቀንቀን ህዝቡን ለልማት በማነሳሳት በርካታ ስራዎች መስራቱን ኑርቴ ይናገራል፡፡ የስልጤን ሙዚቃ ፣ማሳደግ፣ በዓለም መድረክ ማስተዋወቅና ሁሉም ሰው እንዲሰማው ማድረግ የኑርቴ የወደፊት ራዕይ መሆኑን ይናገራል፡፡ሁላችንም እናበርተው፡፡ በቅርቡ የሙዚቃው ዜማና ቅንብር በሙሉ ተጠናቋል። አቀናባሪው ሥራውን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ የቪዲዮና bዩቱዩብ ይለቃቃል ተብሎል፡፡
ሄራታጆ ደነብ ስልልሽ
Region: SA
Saturday 11 July 2026 16:56:48 GMT
Music
Download
Comments
የበሪመ፣ :
🥰🥰
2026-07-11 20:07:24
0
መሃማድአማን 🙏 :
ኑርቴ🥰🥰🥰
2026-07-11 20:35:01
0
Tawfiq❤🔐 :
❣️❣️
2026-07-11 17:26:21
0
እቲዮ ስልጤ :
2026-07-11 18:59:52
0
H 5 :
🥰🥰🥰
2026-07-12 10:44:31
0
አብድ :
❤️❤️❤️❤️
2026-07-11 17:20:11
0
አ/ሃድ ሰለም ለሀገሬ :
❤️❤️❤️
2026-07-11 16:59:15
0
ማሜ.ቢቸኛዉ🐆😭🐅21 :
😍😍😍
2026-07-12 11:41:30
0
To see more videos from user @sililsh, please go to the Tikwm
homepage.