@.man2383: የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ ሲኖር ከሚፈራቸው ነገሮች ሁሉ ግንባር ቀደሙ "መለያየት" ነው። አንቺን ካገኘሁ በኋላ አለሜ በደስታ ብርሃን ሲሞላ የልቤ ምት ካንቺ ጋር ሲዋሃድ  ይህ አረመኔ ቃል ከእኛ ታሪክ ውስጥ ፈፅሞ የሌለ ይመስለኝ ነበር። ጊዜ ይቆማል  ፍቅራችንም እንደተገመደ ገመድ ዘላቂ ይሆናል ብዬ አምኜ ነበር።  "መለያየት ባይኖር...ብዬ ከልቤ ተመኘሁ። ነገር ግን ምኞቴ ከንቱ ምኞት ብቻ ነበር። አብረን ያሳለፍናቸውን ጊዜያት ሳስታውስ እያንዳንዱ ደቂቃ የዘላለም ይመስል ነበር። አብረን ከልብ የሳቅናቸው ጣፋጭ ሳቆች በዓይኖቻችን የተለዋወጥናቸው  ቃላት አልባ ንግግሮች ነገን አስበን አብረን የገነባናቸው ተስፋዎች እነዚህ ሁሉ መቼም እንደማያልቁ መቼም እንደማይፈርሱ አስቤ ነበር። ፍቅር ሲይዝ አይንን ይጋርዳል ይባላል  እኔም የተጋረደብኝ የህይወትን መራራ እውነት ላለማየት ነበር። እውነት ግን የቱንም ያህል ብንሸሸው መምጣቱ አይቀርም። ያ ያልጠበቅኩት ቀን መጣ፣ እናም ያ ሁሉ ያማረ ህልም እንደ ጉም በነፋስ ተበተነ። መለያየት ፊቱን ሲያዞርብኝ ዓለም በአንድ ጊዜ ቀለሟን ቀየረች። ትናንት ሞቃት የነበረው ፀሀይ ዛሬ አቀዘቀዘኝ ትናንት ያማረውና አብረን የተራመድንበት መንገድ ዛሬ ባዶ እና አስፈሪ ሆነብኝ። ያኔ ነው የተረዳሁት... መለያየት አካልን ከአካል ብቻ ሳይሆን ነፍስን ከነፍስ የሚነጥል ጥልቅ ቁስል መሆኑን። "አብረን የጀመርነውን መንገድ ብቻዬን እንድጨርሰው ተገደድኩ። ትዝታዎችሽ እያሳደዱኝ ድምፅሽ በጆሮዬ እያቃጨለ ግን ደግሞ በአጠገቤ እንደሌለሽ እያወቅኩ በናፍቆትሽ መኖር እጅግ ይከብዳል። ይህ ስሜት ምን ያህል ልብን እንደሚያደማ አንጀትንም እንደሚበላ ቃላት ሊገልፁት አይችሉም። ሰውነትህ እያለ ነፍስህ የሌለች ያህል ሆኖ መሰማት የመለያየት ትልቁ እርግማን ነው። አዎ መለያየት ባይኖር ብዬ ተመኘሁኝ። የሰው ልጅ ሁሉ በነፃነት የሚያፈቅረውን ሰው አቅፎ የሚኖርበት "ደህና ሁኚ" የሚለው ቃል ከመዝገበ ቃላት ውስጥ የሚጠፋበት ዓለም ቢኖር ብዬ አለቀስኩ። ግን ምኞቴ ከንቱ ነበር። ህይወት የራሷ የሆነ የማይጣስ ህግ አላት መገናኘት እንዳለ ሁሉ መለያየትም የዚሁ ህግ አካል ነው። ምንም እንኳን ዛሬ በአካል ብንለያይም  እናም ምኞቴ ከንቱ ሆኖ ቢቀርም አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት አውቃለሁ፡-   ትዝታችን መቼም አይሞትም። በልቤ ውስጥ ሁሌም ያንቺ የሆነ ልዩ ቦታ ይኖራል። መለያየት አካልሽኝ ከኔ አራቀው እንጂ ፍቅርሽን ከልቤ ሊነቅለው አይችልም። ምናልባት ህይወት የየራሳችንን መንገድ እንድንሄድ አስገድዳን ይሆናል ነገር ግን ያሳለፍነው እውነተኛ ፍቅር ሁሌም በልቤ ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል። ተለያይተን ብንኖርም፣ በትዝታዬ ውስጥ ሁሌም አብረሺኝ ነሽ። MAN✍️ #personalthoughts #📸 #foryou #deepthoughts #ethiopianmusic

MAN
MAN
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 12 July 2026 19:41:42 GMT
27352
1261
26
154

Music

Download

Comments

kidusboy4
Kidus :
የሰው ልጅ ሁሉ በነፃነት የሚያፈቅረውን ሰው አቅፎ የሚኖርበት "ደህና ሁኚ" የሚለው ቃል ከመዝገበ ቃላት ውስጥ የሚጠፋበት ዓለም ቢኖር ብዬ አለቀስኩ This part so hart 😭💔
2026-07-14 20:49:14
8
enate61
hass :
ግን ለምን🥺🥺
2026-07-13 18:02:03
5
abeltesfay21
abel :
worth reading 🥰
2026-07-13 10:29:31
3
.man0866
ጥቁር 💘😭ፍቅር💞 /tikur 😭fiker❤️ :
gin eko yenen hiwot new yetsafjew... egizabher yisteh.. lemiwodat lemafkrat lije. share adergewalehu.... yemar.. ewodishalehuuu🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-14 20:21:18
0
ahmi_j90
Ahmed_werjiw :
lmn
2026-07-13 19:14:23
0
kalebeva
ካሌብ :
2026-07-13 17:40:44
0
user.kal.kal1
user kal kal :
uff yasfral🥺🥺
2026-07-20 11:56:36
0
desta_687
@heroine :
መለያየት.... በውለት መንታ መንገድ መጋዝ 🥺🥺🥺
2026-07-14 19:58:04
0
m12121u94
Addisu :
እኔነቴ
2026-07-14 08:28:31
0
barklign3
BARBAR :
2026-07-13 07:17:58
0
abel272112616
abel272112196 :
😭
2026-07-13 18:13:14
0
kele.dire
kelil Babula :
àhhhhhhhh
2026-07-13 22:14:17
0
user6139800773569
21 :
አሁን እኔም በዚህ ህመም እለት በእለት አየሞትኩኝ ነዉ
2026-07-13 19:00:03
0
alexo2187
Alex 70 🇮🇩💊 :
Mechem bihon aresashm 🥺
2026-07-13 03:34:26
0
seid34960
seid :
🥰🥰🥰
2026-07-12 20:26:45
1
berhanuabiye
Berhanu A. MD :
💔
2026-07-14 17:45:49
0
ma.messi10
🤴🎧 :
@liyura🌺 🥺🙌
2026-07-13 20:40:37
1
tedy.sky.light
tedy sky light :
😭😭
2026-07-13 16:54:13
0
ani762336
@𝖉𝖆𝖓𝖎. :
✍️🤝.
2026-07-14 05:28:01
0
kibromina
ክብሮሚና :
🥰🙏🙏
2026-07-17 18:07:47
1
To see more videos from user @.man2383, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About