@addisababacodeenforcemen: በከተማዋ በቅንጅት በመሰራቱ ከተማዋን ለቱሪስት መዳረሻ በማድረግ በርካታ ሁነቶች ያለ ምንም የጸጥታ ችግር ማከናወን መቻሉ ተገለፀ 07/11/2018 ዓ.ም ****አዲስ አባባ**** በበጀት አመቱ የሰላም፣ጸጥታና ደህንነት ስራዎች በመሰራቱ በከተማዋ ትላልቅ ሐይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ኩነቶች በሠላም መጠናቀቃቸውን በመግለጽ ከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶች ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲያልፉ በቅንጅት ተሰርቶ ከተማዋን ለቱሪስት መዳረሻና የስበት ማእከል ማድረግ መቻሉን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ክብርት ሊዲያ ግርማ ገለፁ። በበጀት ዓመቱ የተቋም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር የአመለካከትና የክህሎት ስልጠና በመስጠት ሁለንተናዊና መዋቅራዊ ሥራዎች በትኩረት የተሰሩበት ዓመት መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ ገልፀው ፣ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ የሚረዳና የአገልግሎት አሰጣጥን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚያቀላጥፍ ሰራተኛ በመፍጠር ረገድ በዓመቱ ስኬታማ ሥራ መሠራቱ ተገልጿል። የጸጥታ መዋቅሩ ከህዝቡና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ አዲስ አበባ ከተማ ፍጹም ሰላማዊ እንድትሆንና የደንብ መተላለፎችና ወንጀል ምጣኔን በመቀነስ ህዝቦቿ በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ማስቻል ተችሏል ብለዋል። ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የፀጥታ ስራዎች በስኬት የታጀቡና በከተማዋ የተካሄዱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች፣ የአደባባይ በዓላትና ሌሎች ዝግጅቶች በሰላም መጠናቀቃቸው ተናግረዋል። በተቋም ግንባታ ስራ የደንብ መተላለፎች ለመቆጣጠር ብቁ የሆነ አመራርና ሰራተኛ ማፍራት መቻሉን አንስተው ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን መሰራቱን ገልፀው አክለውም በደንብ ማስከበርና የደንብ ጥሰቶን ከመመከት አኳያ መሬት የያዘ ተጨባጭ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል። ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በሁለቱም ተቋማት በበጀት አመቱ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በመከወን የደንብ ጥሰትን የሚጸየፍ ህብረተሰብ መፍጠር መቻሉና የተቋም ግንባታ ስራ ላይ በልዩ ትኩረት በመሰራቱ አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል መቻሉ ፤ የህግ የበላይነትና ወንጀል መከላከል ስራዎችን ፈር በማስያዝ የህገ-ወጥ መሬት ወረራ፣ ህገ-ወጥ ግንባታ የደንብ ጥሰቶችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉ በቀረበው ሪፕርት ተመላክቷል። የመረጃን እውነታ ከስሩ በማጥራት ብልሹ አሰራርን መከላከልና ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ከተለያዩ የፀጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት እንዲሁም ዘመናዊና ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስኬታማ ሥራ የተሰራበት ዓመት እንደነበርም የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። በህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማው የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት በተለያዩ ዙሮች በንድፈ ሀሳብና በመስክ የአካል ብቃት በማሰልጠን ዘላቂ ሰላም በመገንባት በበጀት አመቱ 44ሺ አዲስ የሰላም ሰራዊት ብቁ በማድረግ ከነባሩ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ተደርጓል፤ መረጃው:-የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
አዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Region: ET
Tuesday 14 July 2026 18:13:31 GMT
Music
Download
Comments
user800547282461 :
ጥሩ መድረክ ነበር። ውይይቱ ለ2019 ዓ.ም ዕቅድ ጥሩ መነሻ ነበር
2026-07-14 18:26:58
1
Naol WDG :
:በርቱ ጀግኖች ጥሩ ስራ እየሰራችሁ ነው 👍👍👍👍👍እኛም ከጐናችሁ ነን
2026-07-15 15:18:02
0
AMIR ጁነዲን :
በርቱ ጀግኖች ጥሩ ስራ እየሰራችሁ ነው 👍👍👍👍👍
2026-07-15 05:14:56
0
Abdi zagiret :
🥰🥰🥰
2026-07-14 18:16:55
0
F.J :
🥰🥰🥰🥰
2026-07-15 09:29:12
0
To see more videos from user @addisababacodeenforcemen, please go to the Tikwm
homepage.