@beti123ab: ባል ስጠኝ ብዬማ እግዚአብሔርን አለምንም አንብቡት በእመቤቴ ዛሬ ያገኘኋት ወጣት እህቴ ስለ ግል ሕይወቷ በግልጽነትና በፍጹም በራስ መተማመን ስታወራኝ ቆየች። እናም እንዲህ በማለት ጠየቀችኝ "እውነቴን ነው የምልህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ለትዳሩ ክብር ያለው ባል ባገኝ ደስ ይለኛል። በተለይ በቁርባን ባገባ በጣም ደስ ይለኛል። ነገር ግን ይኼን ማግኘት በጣም ከባድ ነው። የሚታመን ወንድ የለም አለች። እኔም እጅግ መልካም ነገር ተመኝተሻል። ምኞትሽ እንዲሳካ ለምን ታዲያ እግዚአብሔር የምትመኚውን መልካም ሰው እንዲሰጥሽ በጸሎት አትጠይቂውም አልኳት። እርሷም ኸረ እንደ ደግሞ እግዚአብሔርን ወንድ ስጠኝ ባል ስጠኝ ብዬ ልለምነው እንዴ? ኸረ በፍጹም! እግዚአብሔርን እማ ባል ስጠኝ ብዬ አለምንም" ስትል አጽንኦት በመስጠት አቋም" በሚመስል ድምጸት ነገረችኝ። ይህ አይነት አረዳድ የእርሷ ብቻ ሳይሆን የብዙ እህቶችና ወንድሞች አረዳድ ነው። ለዛ ነው በአንድ ወቅት አንዲት ልጂ ባል ትፈልግና ሃይማኖቷ በሚፈቅደው ሕግና ስርዓት መሠረት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች። ዳሩ ግን አንድም ቀን እግዚአብሔርን በቀጥታ ጥሩ ባል ጥሩ ትዳር እንዲሰጣት ለምናው አታውቅም። ለምን ቢባል ታፍራለች። "እግዚአብሔር እንደት ስለ ባል ይጠየቃል? የሚል ደካማ አመለካከት አላት። እግዚአብሔርንም ጥሩ ባል ስጠኝ ብላ መለመን ያሳፍራታል። እንዳትተወው ደግሞ ባል ያስፈልጋታል ታዲያ አንድ ቀን ሲጨንቃት እንዲህ ብላ ጸለየች፤ ፈጣሪዬ እባክህን ለእናቴ ጥሩ አማች ስጣት" የምባረክበት፣ አንተም የምትከብርበት መልካምና አንተን የሚፈራ ሃይማኖቱን የሚወድ ባል ስጠኝ ላለማለት "አማች ስጣት ያለችው። እህቴንም የገጠማት ይኸው ነበር። ብዙ ጊዜ ገንዘብ፣ ሥራ ወዘተ የመሰሉ ነገሮችን ስጠኝ ብለን ለመለመን አናፍርም። ወንዱ ሚስት ሴቷ ደግሞ ባል ስጠኝ ብለው መለመን እግዚአብሔርን ያፍራሉ። ይኼ ፍጹም ስሕተት ነው። ጋብቻ ክቡር ነው መኝታውም ንጹሕና ቅዱስ ነው። እግዚአብሔርን የምትፈራ ሚስት በጸሎት ካልሆነ ከየት ልትገኝ ትችላለች? ባልም እንደዛው። ጋብቻ ታላቅ ምስጢር ነው። ጋብቻ ለቤተ ክህነትም ለቤተ መንግሥትም የሚሆኑ ልጆች የሚፈሩበት ነው። ጋብቻ ትልቅ አቋም ነው። ሚስት የእስከ ሕይወት ፍጻሜ የሀዘንም የደስታም ተካፋይ የሕይወት አጋር ናት። ባልም እንዲሁ። ታዲያ ይኼን ትልቅ ጉዳይ እግዚአብሔር አባታችንን ካልጠየቅን ማንን ልጠይቅ ነው? መልሱ ማንንም ነው። ባል የሚሆን ወንድ የለም ከማለት ሚስት ሆኖ ተገኝቶ ባል እንዲሰጥሽ እግዚአብሔርን መለመን። አንተም ወንድሜ እንደዛው። ከእህቴ ጋር ብዙ ተወያይተንበት በመጨረሻም "ኸረ እንዲያም እንዲህ ከሆነማ በጸሎት ብቻ ሳይሆን በሱባኤም ጭምር ነው የምጠይቀው ብላኝ ተለያየን። በእርግጥ እግዚአብሔርን ስንለምን "የምትለምኑትን አታውቁምን" ተብለው እንደተወቀሱ ሰዎች እንዳልሆን መጠንቀቅ አለብን። ለብዙዎች ግን የሚያሳፍረው ሳያሳፍራቸው ፤ የማያሳፍረው ያሳፍራቸዋል። ወሰብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን

ቤቲ ነኝ የድንግል ማርያም ልጅ☦️🤗
ቤቲ ነኝ የድንግል ማርያም ልጅ☦️🤗
Open In TikTok:
Region: SA
Wednesday 15 July 2026 18:28:39 GMT
239752
13255
415
919

Music

Download

Comments

.12306329
mylove{🍋🍋}&<> :
የኔን ኮሜት የነካ እግዚአብሔር ይጠብቀዉ ቃለ ህይወት ያሰማልኝ🙏🙏🙏
2026-07-16 22:49:28
107
www.ttt.co
🌈✍️ :
ቃለ ህይወትን ያሰማልን እህታችን አንቺንም በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን እኛንም ያነበብነዉን ፈጣሪ በልቦናችን ያሳድርብን🤲🥰🥰🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-16 03:30:56
61
lij.azimeraw
Lij Azimeraw :
መልካም ሚስት ለመንግስተ ሰማያት ታበቃለች እኮ ምክንያቱ አንድ ለአንድ በትዳር ጸንተው መልካም ስራ እየሰሩ እንዲኖሩ ትመራለች ሰለዚህ እግዚአብሔር መልካም ትዳር ስጠኝ ብሎ መለመን አያሳፍርም ያስከብራል እንጅ !ለሁላችንም እግዚአብሔር ላለን ያጽናን ለሌለን ይስጠን መልካም ትዳር።
2026-07-16 14:34:24
20
feven.berhe1
𝐅𝐞𝐯𝐞𝐧 𝐛𝐞𝐫𝐡𝐞👸🏻 :
ኣረ የኔ ብቻ ነው በኢንግልዘኝ የሆነው ፅህፉ🥺መልሰልኝ እህቴ ኣማርኝ ኮሆነ ፅህፉ ላንብብ እንደዚ ኣይነት የሂወት ታሪክ በጣም ነው ምወደው😔💚
2026-07-16 11:23:25
12
lydiadesalegn
፲፯ሊዲያ✝️ወይኩን ፈቃድከ ⛪💕 :
እንደኔ ከዚህ ቤት በዙ ትምህርት የምትወስዱ ላይክ ቃለ ህይወት ያሰማልን የኔ እንቁ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-16 13:55:11
53
user2521687150177
Mubarke :
ወአለሂ ጨአሪሼ አነአበአብኩት ኢንዴት የአሚየአሰደአሲት መክር ነአው👌👌
2026-07-17 18:16:23
14
alem30410
Alem :
2026-07-23 08:22:42
1
user6783670438856
እማ በፆለትሽ😘🙏 :
በፈጣሪ ስም ህይወት የሆነ ትምህርት ነው ፈጣሪ ይጠብቅሽ እህቴ🥺🥰🥰
2026-07-15 18:41:54
10
seat.werk.new
seat werk New :
እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለህይወት ያሰማልን በናተ ያደር መንፈስ በኛም ይደርብን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-16 08:49:17
5
user9579230787224
ዲ/ን ዘለዓለም ጥጋብ :
በጣም ትልቅ ነገር ነው እግዚአብሔር ይስጥልን
2026-07-15 20:11:15
15
user832675885261
የድግል ማርያ ምልጅ⛪⛪⛪💝💝 :
እግዚ አብሔር ለሁላችንም ልቦናይሥጠን🙏🙏🙏🙏
2026-07-16 04:47:47
6
haregtilahune
Haregtilahune :
ቃለህወት ያሰማልን🙏🙏🙏
2026-07-16 08:51:16
1
.my.father.is.my.life
(ያምላክ እርቅ አዲሴ (⛪ እኔ ክርስቲያን ነኝ :
እግዚአብሔር ያክብርሽ🙏🙏🙏🙏
2026-07-15 23:38:04
4
user5148711729169
ርብቃ ነኝ ✝️✝️የተዋህዶ ልጅ ✝️❤️‍🔥⛪⛪ :
እንቁይየ
2026-07-15 19:16:49
4
mhret.aychlu
𝐌𝐡𝐫𝐞𝐭 🎀 :
ቃለ ሂወት ያሰማለን 🤌🙏😘❤️✝️
2026-07-18 09:33:41
1
user2367875099769
ፀግሽ :
ኧራ ይህን ኮሜት ያነካ እንጅ ያተበሪከ እጅ ነው🥰🥰🥰
2026-07-17 09:16:19
2
hilu8238
ባለ ማህተቧ🙏☦️🕊 :
ቃለ ሂወት ያሰማልን ትልቅ ትምህርት ነዉ ፀጋዉን ያብዛልሽ 🤲🙏 የኔ ሴት🤌👸🙏✝️🕊
2026-07-16 16:11:32
4
asres.as
Asres ደባርቄዋ :
እናመሰግናለን እህቴ ቃለሂይወት ያሰማልን የሁላችንም መጨረሻ ፈጣሪ ያሳምርልን🙏🙏🙏
2026-07-16 11:19:03
0
user5216128230504a
እረስቴ :
💐
2026-07-16 12:35:52
0
user1981945398446
user1981945398446 :
ቃለ ሂወት ያሰማልን እህታችን እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥሽ መልካም ትምህርት ህርት አስተማርሽ እኛንም እግዚአብሔር ከትምህርቱን ልቦና ሰጥቶን የምንማርበትያድርግልን🤲🙏🙏🙏
2026-07-16 09:19:32
4
user983133541029
t :
እ/ጥሩ ነገር ያሰማሽ
2026-07-16 06:46:56
1
bezatadese4
ቤዚ የኪዳ ነምሕረት ልጅ🙏🙏🙏👌👌👏💚 :
ቃለሒወትን ያሰማልን
2026-07-18 07:49:33
1
tigst.kindu4
Tigst Kindu :
በእዉነት ከሳይጣን ወጥመድ ይጠብቅሽ እግዚአብሔር 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-16 11:29:31
1
www.ttt.co
🌈✍️ :
ቃለ ህይዎት ያሰማልን እህታችን በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን ለኛም ያነበብነዉን በልቦናችን ዉስጥ ያሳድርብን🥰🥰🙏🙏
2026-07-16 03:27:59
1
etalem014
ማርታ ነኛ ወሎየዊ :
ቃለሂወት ያሰማልን በቢቱ ያፅናልን የሜግረም ትመህረትነዉ
2026-07-16 12:12:16
1
To see more videos from user @beti123ab, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About