@.7312873: ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው!😭 እስኪ ቆም ብለን እናስተውል… ከዛሬ 80 (ሰማንያ) ዓመታት በኋላ፣ አሁን በዚህች ሰከንድ በምድር ላይ ካለን ሰዎች መካከል አንዳችንም በሕይወት አንገኝም። ዛሬ ቀንና ሌሊት የምንደክምላቸው፣ የምንጨነቅላቸው፣ የምንጣላባቸውና ሰላማችንን የምናጣባቸው የዚህች ዓለም ትግሎች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ80 ዓመት በኋላ ፈጽመው ይጠፋሉ፤ ለምልክት እንኳ አይገኙም። ሁሉም ነገር ታሪክ ሆኖ ያልፋል፣ ይረሳልም። ትናንት የነበሩት ዛሬ የታሉ??? ወደ ኋላ 80 (ሰማንያ) ዓመታት ገደማ እንመለስ… ወቅቱ በ1930ዎቹና 1940ዎቹ ማብቂያ አካባቢ ነው። ያኔ በየአቅጣጫው ለሥልጣን፣ ለዝናና ለቁስ ይፋለሙ የነበሩ፣ ዓለምን ያጨናነቁ ኃያላንና ባለጸጎች ዛሬ የታሉ? እኛስ ዛሬ የምንሮጥለት ሩጫ ነገ አፈር ስንሆን ምን ዋጋ ይኖረዋል? “ሰውስ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” (ማቴዎስ ፲፮፥፳፮) ዛሬ የታበይንበት ዝናና ስም ነገ የት ይገባል??? በዓለም ላይ ታላቅ ዝናን አትርፈው የነበሩትን ማይክል ጃክሰንን እና ሌሎች ታዋቂዎችን እስኪ እናስታውስ። ከሞቱ ገና ጥቂት አሥርት ዓመታት እንኳ ሳይሞላ ስማቸውና ዝናቸው ቀስ በቀስ እየተረሳ መጥቷል። ከ80 (ሰማንያ) ዓመታት በኋላማ እነዚህ ታዋቂ ሰዎች የሚባሉት ስሞች ፈጽሞ ከሰው ልጅ አእምሮና ትውስታ ይጠፋሉ። ዛሬ ልትሞትለትና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት፣ ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለትና ደም አፍስሰውለት አልፈዋል። ዛሬ ግን እነዚያ ሰዎች ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል። ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች፣ ነገ አንተ መቃብር ስትገባ ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ብቻ ይሆናሉ። ዓለምና ምኞቷ ይልፋሉ፤ መቃብርም ሰውን ሁሉ በእኩልነት ያስተናግዳል። ንጉሡም፣ ደሃውም፣ ኃያሉም፣ ደካማውም ጎን ለጎን አፈር ለብሰው ይተኛሉ። በመቃብር ፊት ስምና ሥልጣን አቅም የላቸውም፤ ሀብትና ንብረት አብረው አይወርዱም፤ ውበትና ጉልበትም ከዕድሜ ጋር ይረግፋሉ። ይህ እውነት ልብን ይሰብራል፣ ዓይንን በእንባ ይሞላል። ነገር ግን መቃብር ፍጻሜ ሳይሆን ወደ ዘላለማዊ ሕይወት መሻገሪያ በር ነው። ከእኛ ጋር ወደ መቃብር የሚወርደውና በፈጣሪ ፊት ዋጋ የሚሆነን በምድር ላይ የሠራነው በጎ ሥራችን፣ ለሰዎች ያሳየነው እውነተኛ ፍቅር እና የያዝናት ቅድስት እምነታችን ብቻ ናት። "ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።" (፩ ዮሐንስ ፪፥፲፯) ሸር ፣ repost copy link አድርጉልኝ ወንድማችሁ (((ኤፍታህ))) ነኝ #መንፈሳዊሕይወት #ምድራዊ_ሩጫ #ዘላለማዊነት #ፍቅርና_በጎነት #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_
@(((ኤፍታህ)))ማ/ር፥፯፣፴፬
Region: ET
Thursday 16 July 2026 06:35:40 GMT
Music
Download
Comments
ቼ ጉቬራ🇧🇴 :
ሁሌም እሚያሳስበኝ እና እሚገርመኝ ነው ማሪያምን አይደለም 70 አመት 200 አመት ኖረን ብንሞትም ያ 200 አመት በጣም ትንሽ ነው እንላለን የሰው ልጅ ፍላጎቱ unlimited ነው
እና በጣም እሚገርመኝ ነገር 70 አመት ለማንቆየው እድሜ በሃጢአት እምንዘፈቀው ነገር😭😭 ሲቀጥል 70 አመትም እኮ ከኖርን ነው ምክንያቱም አሁን እኔ 25 አመቴ ነው ሰባ ስትደምሩበት 95 ነው አስባችሁታል ይህንንም እግዚአብሔር ፈቅዶልኝ ከኖርኩ ነው 😭😭😭😭 ስለዚህ ከዚህ በኋላ እንኳን 80 አመት አልኖርም ስለዚህ ለምን ግን ይህን ወደ ህሌናችን አምጥተን በተግባር ላይ አውለን ከሀጢአት አንቆጠብም
በጣም እሚገርመኝን ልንገራችሁ ይህን video ሳይ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ እተወዋለሁ እልና አንዴ scroll ሳደርግ ሀሳብ እቀይራለሁ 😭😭😭😭😭 አይ አንች አለም😭😭😭😭
2026-07-16 17:00:44
122
✨ 𝐁𝐢𝐫𝐞 ✨ :
ግን ምን አይነት ፍጥረት ነን ሁሌም ለስጋ ፍላጎት ለይ እንደፈጠጥኩ
2026-07-16 17:33:40
13
Getahun Mekonnen :
ሁሉንም ማለት አይከብድም እኛ ምን እናውቃለን ማን 70 አመት ይኑር ማን ከዚያ በላይ መወሰን የሚችለው አሱ የዘላለም አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው ስለዚህ መደምደሙ ተገቢ አይመስለኝም ይልቅ ሁለችንም ሞት የሚባል ነገር እንዳለ ሁሌም እያሰብን መኖር እንዳለብን ብናውቅና ሁሌም ተዘጋጅተን በንኖር መልካም ነው !!!
2026-07-16 13:36:16
11
Yalemzewd Bizuneh :
የሰው ዘር ይህንን ማስተዋል ተስኖን ተባልተን አለቅን።
2026-07-17 04:22:23
14
biniam Assefa :
እግዞዎ መሀረነ ክርስቶስ እንበል ቤተሠብ
2026-07-16 19:13:30
12
DEREJE Getachew :
አቢቱ ልጂ ወዳጀ በለን በዝች አለም እንድኖር የሠጠኸን አጪር የኩንትራት ጌዜ ፈፃመን ሰንመጣ በገነት አሰታውሰን
2026-07-16 16:36:48
10
muluembet :
እውነት ነው ፈጣሪ ለንስሀ ያብቃን።
2026-07-16 12:48:36
15
mimi01012 :
ኡፍፍፍፍ ግልግል
ግብር የለብን
ቤት ኪራይ የለብን
ስራ ማጣት የለብን
የሰው ክፋትና ምቀኝነት የለብን
ጭቅጭቅ የለብን ለጥጥ
2026-07-17 14:29:01
9
mesi yemrayam lij❤❤❤ :
እሱንም እድሜ ማግኘት እራሱ በጣም ትልቅ ነገር ነው
2026-07-16 15:13:43
5
ዲ/ን..ኃይሌ...ዘደብረ. ገነት... :
አቤቱ ጌታ ሆይ ከእቅፍህ አታውጣኝ
2026-07-16 12:40:18
25
𝔻𝕖𝕁𝕖 𝔹𝕠𝕊𝕊 :
እውነት ነው ፈጣሪ ለንስሀ ያብቃን።
2026-07-16 18:04:54
7
user7673498398335 :
እውነተኛ እና የማስተዋል ምክር አዘል እንዲኖረን የሚለግሥ ነው። ወንድሜ እግዚአብሔር ይባርክህ።
2026-07-16 13:11:05
20
fikiru ku :
በእውነቱ አስተማሪ ነገር ነው እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅልን
2026-07-16 13:04:55
1
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው!!!!!!!!!!! :
ወንድሜ ፀጋ ይብዛልህ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
ከሁሉ አስቀድም ሰው የዘላለም መኖርያውን ማወቅ አለበት!!!!!!!!!!!!!ማቴ16:36
2026-07-17 12:40:32
2
one day(desu) :
ለንስሀ ሞት ያብቃን🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-18 10:48:38
2
ግሩም ግእዝ :
ኧረ በየት ታልፎ ሰባ ዓመት ይደረሳል በኛ ዘመን😭😭😭
2026-07-16 14:46:09
1
🌺ብሶተኛው🍉 :
ቃለህይወት ያሰማልን የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክልን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-18 10:10:34
1
Hirut Addisu :
ፈጣሪ ማረን ይቅር በለን
2026-07-16 13:44:01
1
Zinu :
geeta yibarik hiywotin yimiyadis mikir newu tebarek 👍👍
2026-08-01 07:01:02
1
netsa bizu :
@The B🇧🇴:ሁሌም እሚያሳስበኝ እና እሚገርመኝ ነው ማሪያምን አይደለም 70 አመት 200 አመት ኖረን ብንሞትም ያ 200 አመት በጣም ትንሽ ነው እንላለን የሰው ልጅ ፍላጎቱ unlimited ነው
እና በጣም እሚገርመኝ ነገር 70 አመት ለማንቆየው እድሜ በሃጢአት እምንዘፈቀው ነገር😭😭 ሲቀጥል 70 አመትም እኮ ከኖርን ነው ምክንያቱም አሁን እኔ 25 አመቴ ነው ሰባ ስትደምሩበት 95 ነው አስባችሁታል ይህንንም እግዚአብሔር ፈቅዶልኝ ከኖርኩ ነው 😭😭😭😭 ስለዚህ ከዚህ በኋላ እንኳን 80 አመት አልኖርም ስለዚህ ለምን ግን ይህን ወደ ህሌናችን አምጥተን በተግባር ላይ አውለን ከሀጢአት አንቆጠብም
በጣም እሚገርመኝን ልንገራችሁ ይህን video ሳይ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ እተወዋለሁ እልና አንዴ scroll ሳደርግ ሀሳብ እቀይራለሁ 😭😭😭😭😭 አይ አንች አለም😭😭😭😭
2026-07-24 18:21:56
2
መለያየት ባይኖር መተዋወቅ ጥሩ ነበር❤❤ :
በጣም ትክክል
2026-07-16 16:28:21
1
solomonbekele56 :
ማሪያምን ለምን እደወነ አላቅም እያነበብኩት እትባዬ እርግፍ ሲል ታየኝ አይ ስው ከንቱ ስናዛዝን ግን
2026-07-20 06:25:40
4
RAS DJ BUSY :
ፈጣሪዬ ሆይ ይህን ስላሳየከኝ እጅግ በጣም አመሠግንካለው አምላኬ ሆይ ባለቺኝ ጊዜ በጎ ነገር እንድሰራ እርዳኝ ተመስገን🥰🥰🥰
2026-08-02 21:12:01
2
መለስ፡የፍቅር፡ሰው :
ኦሪቶዶክሰ፡ጸንታ፡ትኑር
2026-07-18 21:09:08
1
mekuant :
70እና80 የሚደርስ ፈጣሪ የመረጠው ነው
2026-07-16 15:06:43
1
To see more videos from user @.7312873, please go to the Tikwm
homepage.