@luna.3012.81: cốc tạo bọt sữa rửa mặt #taobotsuaruamat #coctaobot #lunashop

Tạp hóa Luna
Tạp hóa Luna
Open In TikTok:
Region: VN
Thursday 16 July 2026 08:45:36 GMT
146
0
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @luna.3012.81, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል……የየካ ደብረ ሣህል  ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን        part 1 ዋሻ ሚካኤል (Washa Mickael) ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ በኩል የካ ከፍለ ከተማ ውስጥ ያለ ጥንታዊ እና በከፊል ወጥ ከሆነ ዓለት ተፈልፍሎ የተሰራ ቤተ-ክርስቲያን ነው:: አዲስ አበባ ከሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ በስተጀርባ ቲንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ከፍታማ ቦታ ላይ ይገኛል:: ቤተክርስቲያኑ የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያን አይነት ስልት የያዘ ነበር። ምንም እንኳ የህንጻው አወቃቀር ባልታወቀ ምክንያት ሳይጠናቀቅ የቀረ ቢሆንም ስራው ቢገባደድ ኑሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የአለት ውቅር ቤተክርስቲያኖች በትልቅነቱ ሁለተኛ ይሆን እንደነበር ተመራማሪዎች ይዘግባሉ (ታላቁ የላሊበላ መድሃኒ ዓለም ነው) ። ከትውፊት አንጻር፣ ቤተክርስቲያኑ የተሰራው በዓፄ አፅብሐትዕዛዝ እ.ኤ.አ በ380 ዓ.ም. ነው። ታሪክ አጥኝው ኤ.ኤፍ.ማቲው ግን ቤተክርስቲያኑ ከላሊበላ ዘመን በኋላና ከግራኝ መነሳት በፊት እንደተመሰረተ ያስረዳል። የቤተክርስቲያኑ ስራ መቋረጥም አካባቢው በግራኝ በመወረሩ እንደሆነ ያስረዳል። 30% የሚሆነው የዋሻ ሚካኤል ህንጻ ሳይጠናቀቅ የቀረ ነው። ከዚያ በላይ ህንጻው የጣሪያና የግድግዳ መፍረስ አጋጥሞት በአሁኑ ዘመን ከሞላ ጎደል የመፈራረስ መልክ ይዞ ይገኛል። ለመፍረሱ ብዙ ምክንያት ይሰጣል፣ አንድ አንዶች በኢጣሊያ ወረራ ወቅት በቦምብ ተደብድቦ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ በግራኝ ተቃጥሎ ነው ይላሉ። አንድ አንድ ተመራማሪዎች ግን ከራሱ ከቤተክርስቲያኑ ባገኙት መረጃ ተነስተው ህንጻውን ሲያንጹ የነበሩ ሰዎች ባደረጉት የሥነ ህንጻ ስህተት ጣሪያው እንደፈረሰ ያስረዳሉ።  ምንም እንኳ የአካባቢው የቀደሙት አባቶች ካህናት በአፈ ታሪክ በ4ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ቢናገሩም በፅሁፍና አንዳንድ የታሪክ ተንታኞች ደግሞ በ12ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ነው:: ለዚህም አንዱ ማሳያ አብርሃና አጽብሃ የአክሱም መንግስትን በጋራ ይገዙ እንደነበር የተለያዩ መጽሃፍት ይገልፃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጽሁፍም ይሄንን በተለያዩ መረጃዎች ይጠቅሳል፡፡ ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላ እንደተፃፈ በሚነገረው የድንጋይ ላይ ፅሁፍ አብርሃና አፅብሃ የሚያስተዳድሩት አገር ግዛት ዝርዝር ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ዝርዝር እንደምንረዳው ግዛታቸው ሳባን /የመንን/፣ ኑባ /ሱዳንን/ እና ቤጃ /ደቡብ ግብጽ/ ድረስ ይደርሳሉ፡፡ ይህም እጅግ ሰፊ ግዛት እንዳላቸው ያስረዳል፡፡ ከየካ ሚካኤል የተገኘው /ያልታተመ/ መረጃ ይህንን ሀሳብ እንደሚከተለው ያጠናክራል:: “በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ወሰን በጣም ሰፊ ስለነበር ሁሉቱ ወንድማማቾች አክሱም ላይ ሆነው ሕዝባቸውን በቅርብ ለማስተዳደር ስለተቸገሩ እጣ ተጣጥለው ንጉስ አብርሃ አክሱም ላይ በመሆን ሰሜን ኢትዮጵያን፣ ንጉስ አጽብሃ ደግሞ ደቡብ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ሸዋ ውስጥ የረር ተራራ ላይ ቤተ መንግሥቱን ሰራ፡፡ በወቅቱ ቤተመንግሥቱን ለመሥራት ሲመጣ ማዕቀበ እግዚእ በሚባል ካህን ታቦት ሚካኤልን አሸክሞ አስመጥቶ ነበር፡፡ ይህንን አሸክሞ ያስመጣውን ታቦት ከየረር ተራራ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ባስፈለፈለው ዋሻ ውስጥ እንዳስገባው ይገልፃል፡፡” በትግራይ ክልል በአብርሃና አፅብሃ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ከጅማ የአፅብሃ ሬሳ የመጣበት ነው የሚባለው የጠፍር አልጋ ይገኛል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ደቡብ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው አፅብሃ እስከ ጅማ መድረሱን ነው፡፡ ውቅር ቢተክርስቲያን መስራት ለአጽብሃ አዲስ አይደለም፡፡ በትግራይ ከውቁሮ ከተማ 20 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ገረአልታ ውስጥ ገማድ በተባለ ስፍራ አብርሃና አጽብሃ ያሰሩት ነው የሚባል አብርሃ አጽብሃ በመባል የሚታወቅ ውቅር ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያኑ ገዳም ነው፡፡ ከየካ ሚካኤል የተገኘው /ያልታተመ/ መረጃ እንደሚገልፀው በትግራይ ውቅሮ አካባቢ የሚገኘው የአብርሃና አፅብሃ ውቅር ቤተክርስቲያን ከዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው በመግለጽ ታሪኩን እንደሚከተለው ዘርዝሯል፡- “ከንጉስ አጽብሃ ጋር የመጣው ታቦት የገባበት ዋሻ የተፈጥሮ ዋሻ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ እንደሚገኙት ከአንድ ቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍለው ከታነፁት ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ዓይነት በኢትዮጵያ ፊደል “ሀ” ቅርጽ የታነፁ ሲሆን በቤተክርስቲያን የፊደል ትርጉም “ሀ” ማለት “ህልዎቱ ለአብ እምቅድም ይትፈጠር ዓለም” ወይም “የአብ መኖር ከአለም አስቀድሞ ነው” ማለት ነው የሚለውን አባባል ለማስረዳት ተብሎ የታነፀ ነው ይላል፡፡” በሌላ በኩል አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን በደቡብ ሸዋ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ በአለምገና ቡታጅራ መንገድ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 66 ኪሎ ሜትር አካባቢ ከምትገኘው አዳዲ ማሪያም ውቅር አብያተ ክርስቲያን ጋር በመመሣሠሉና ይህ ደግሞ በንጉስ ላሊበላ ዘመን እንደ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዚያ ዘመን የተሰራ ነው ይላሉ፡፡ በአዳዲ ማርያም የሚገኘው የታሪክ ማስታወሻ ንጉስ ላሊበላ የአዳዲ ማሪያምን ከቋጥኝ ድንጋይ እንደፈለፈለውና ሥራውን ሲጨርስ በራዕይ ተመርቶ ወደ ላሊበላ እንደተመለሰና እዚያ ሲደረሰ እንደሞተ ይተርካል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየሶስት ወሩ በሚያሳትመውና ሰላምታ ተብሎ በሚጠራው ቋሚ የበረራ መፅሄት ዊሊያም ዴቪድሰን የተባሉ የታሪክ ተመራማሪ የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስትያን የ700 ዓመት እድሜ እንዳለውና አሰራሩም ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አሰራር ጋር እንደሚመሳሰል ይገልፃሉ፡፡ በየትኛው ዘመን እንደተሰራ ለማወቅ የአርኪዎሎጂ ጥናት መደረግ ስላለበት የነሱን የወደፊት የጥናት ውጤት መጠበቁ ወሳኝ ቢሆንም ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ያገኘነው ያልታተመ ፅሁፍ የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስትኑ ከላሊበላ ጋር በማመሳሰል ማቅረብ የኢትዮጵያን ሀይማኖት ጥንታዊነት በሚፃረሩ ሀይሎች የሚወራ ነው በማለት ይቃወማሉ፡፡ አብርሃና አፅብሃ ከአባታቸው ታዜር ከእናታቸው ሶፍያ (አይዋል) ታህሳስ 19ቀን 312 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ አባ ሰላማ (አባ ከሣቴ ብርሃን) በ28ኛ ዓመታቸው አጠመቁዋቸው፡፡ አብርሃና አጽብሃ ከአባ ሰላማ ጋር በመሆን ክርስትናን በግዛታቸው አስፋፍተዋል፡፡ በዘመናቸው 6ዐ አብያተ ክርስቲያናትን እንዳሳነፁና ከዚህም ውስጥ 44 ቤተክርስቲያናት ፍልፍል ቤተክርስቲያናት ናቸው፡፡ በስማቸው ቤተክርስቲያን ታንፃል፡፡ በየወሩ በ4ኛው ቀንና በየዓመቱ ጥቅምት 4 በአክሱም ፅዮንና መርጦ ለማርያም ቤተክርስትያናት በዓላቸው ይከበራል፡፡ እንደ ነገሥታቱ ገድል በ32ዐዎቹ ንጉስ አጽብሃ በየረር ተራራ ላይ የገነባው ቤተ መንግሥትና ከቤተመንግሥቱ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የተገነባው ውቅር ቤተክርስቲያን በአባ ከሣቴ ብርሃን የመጀመሪያው ጳጳስ ተባርኮ ተመረቀ፡፡ አብርሃና አጽብሃ የጀመሩትን ክርስትናን የማስፋፋት ሥራ በተከታዮችም ነገሥታት የቀጠለ ሲሆን በ6ተኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ካሌብና በአፄ ገ/መስቀል የንግስና ዘመን በበለጠ ተስፋፍቷል፡፡ በ6ተኛው ክ/ዘመን በተለይ ዘጠኙ ቅድሳን ከመጡ በኋላ ክርስትናን የማሠራጨቱ ሥራ ይበልጥ ተስፋፍቷል፡፡ በአክሱም ዘመነ መንግስት ዮዲት ጉዲት የተባለች በአክሱም ግዛት ያሉትን አብያተ ክርስቲያናትና ቄሶችን ማጥፋት በጀመረች ጊዜ የአክሱም ፅዮንን ጨምሮ አንዳንድ ታቦታት ወደተለያዩ ቦታዎች ተሰደዋል፡፡  ይቀጥላል

About