@zinabugirma: 1. አዕምሮ (Brain) አዕምሮ የስው ልጆችን ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ እንዲያስቡ የሚያስችል የስውነት ክፍል ሲሆን ውስጡ ከ98 % ድረስ ስብ (ፋት) ነው ። ከአካል 0.2 % ክፍል ቢሆንም ወደ 20% የሚሆነውን ሃይል ደግሞ ለተለያዩ ስራዎች አዕምሮ ብቻውን ይጠቀመዋል ። በዚህ ብቻ አያበቃም አዕምሮ ምንም ህመም አስተላላፊ ተቀበባዮች (Receptors ) የማይገኙበት የስውነት ክፍል ነው ። ህመምን ግን ከሌሎች ከክፍሎች በሚደርስው መልዕክት እየመዘገበ ያስቀምጣል። አዕምሮ በጭንቀት ፣በድባቴ ፣ በጫና (Stress) ሲወጠር ስራው ይቀንሳል ስለዚህ ይህንን ለማስወገድ አመጋገብ ወሳኝ ነው ። ከላ የተጠቀሱት የእንጆሪ ቤተስብ ምግቦች ፣ ቅባታማ እህሎች የበለጠ እንዲስራና እንዲተሳስር ያደርጉታል ። 2. ልብ (Heart ) ከአዕምሮ አሰቀድሞ ሁሉም በልብ በኩል ያልፋል ይለናል የኒውሮ ሳይንስ ። ልብ ሃሳብን ፣ስሜትን ፣አስተውሎትን ፣ ቃላትን ፣ መግነጢሳዊ ማንነትን የሚፈጥር የስውነታችን ክፍል ሲሆን ከ40, 000 በላይ የሚሆኑ የአዕምሮ ሴሎች እንደተሸከመ በነሱም ከአዕምሮ አስቀድሞ እንደሚያስተውል የስነ አዕምሮ ጥናቶች ያስረዱናል። ልብን መጠበቅ የህይወትን መፍለቅያ መጠበቅ ነው ። ያንን ለማድረግ ከራሳችሁ ጋር ስትነጋገሩ ለምትሉት አሉታዊነት ተጠንቀቁ ፣ ለሌሎች ለምትመኙት ክፋት ተጠንቀቁ ፣ ልባችሁን ይቅርታና ፀሎት አብዝቶ ይጠብቀዋል አዘውትሯቸው ። ከዚህ በተጨማሪ ከላይ የተጠቀሱትን የደም ፍስትን የሚጨምሩትን የአመጋገብ ስርዓት ተከተሉ ። 3. ጉበት ( Liver የፅዳት ማዕከል) ይኸ ቦታ በውስጣችን ባይኖር ውድቀታችን የፈጠነ ነው የሚሆን የነበረው ። ግን እግዚአብሔር ያገኘነውን የምንውጥ መሆናችንን ስላወቀ መርዝ ማጣርያ ፋብሪካ ገጠመልን። ጉበት The center of Detoxification ነው ። ፈንጅ አምካኝ ። ብሎም የፍጭት ስርዓትን የሚያቀላጥፉ የጣፍያ ስሮችን የሚመግብና የሃሞት ከረጢትን የሚሞላ የስውነት ክፍል ነው ። ይህንን ለመጠበቅ ከብዙ ቡና ፣ አልኮል ፣ የታሸጉ መጠጦችና የተቀነባበሩ አመጋገቦች እራሳችሁን ጠብቁ ። በተጨማሪም ከላይ የተጠቀሱትን የአመጋገብ ስርዓቶች ብትከተሉ የተሻለ የስውነት አወቃቀር እንዲኖራችሁና የመርዝ ክምችት በዉስጣችሁ እንዲጠፋ ይረዳችኋል። 4. አጥንት (Bone ) ይኸ ማዕከል የማንነትን ቁልፍ ማስቀጠያ ስንሰለት የያዘ የአካል ክፍል ሲሆን ትውልድን የማስቀጠያ ስርዓቶች ከዚህ ስር እንደሚፈልቁ የዘርፉ ጠበብት ያስተምሩናል ። አጥንት (Spermatogenesis ) የዘር ፍሬ እድሳትና ምርት የሚካሄድበት ማዕከል ነው በተጨማሪም የአካልን ህብራዊ አወቃቀር የሚጠብቅ (Harmonizer) ነው። ስለዚህ አጥንት የሚያሳሱ ነገራትን ከማድረግና ወደ ውስጣችሁ ከማስገባት ታቀቡ ። ለምሳሌ ፖርኖግራፊ ፣ ስክሪን ላይ ትኩረት፣ ሴጋ (ግለ ወሲብ) ፣ የአለልኮል መጠጥ ማዘውተር ፣ የታሸጉ መጠጦችን ማብዛት ፣ ስኳር ማብዛትና የተቀነባበሩ የአመጋገብ ስርዓቶችን መከተል ። ስለዚህ አጥንታችሁን ጠብቁ ዘራችሁን አሰቀጥሉ ። 5. አንጀት (The second brain) ይኸ አስገራሚው ወፍጮ ቤት ነው የትኛውንም ያገኘውን ነገር ያልመዋል ፣ ያስራጨዋል (The center of Bio battery ) ይለዋል የኒውሮ ኢንዶ ክሮኖሎጂ ሳይንስ። ሃይል ሁሉ ማዕከሉ አንጀት ነው ። አንጀት ከተወዛገበ ሌሎችም ማዕከላት ይወዛገባሉ ። በተለይም ሙድ ሲጋጭ ማዕከሉ የአዕምሮ ሳይሆን የአንጀት መሆኑን ልብ ይለዋል። ለምን ሙድን የሚያቀናጀው (Seratonin ) የተባለው ንጥረ ውህድ የሚመነጨው አንጀት ውስጥ ነው ። ይኸም 90 % Mood Adjuster ነው። ይኸንን ለማስተካከል ዋናው ምግብ ነው ። አመጋገብ ከተቀናጀ የኬሚካላዊ ኡደቱ የተሳለጠና ቀላል ይሆናል ። ስለዚህ አሰበልጣችሁ ተፈጥሮአዊ ተዋፅኦዎችን ተመገቡ ። ከተቻላችሁ የካርብ መጠን ቀንሱ ። ከላይ የተመለከተውን የአመጋገብ ስርዓት ተከተሉ ። 6. ቆዳ (Derma / Skin ) ቆዳ ከአካላዊ አወቃቀር ስርዓቶች ውስጥ ቀዳሚው ነው ። በዚህ ስርዓተ ቀመር የስውነትን ልባስ የሸፈነው ይኸ ነው ። ይኸ አሸፋፈን ደግሞ ዝም ብሎ ሳይሆን ልክ እንደ አንቴና ነው (Bio Antena)። ከውጭም መልዕክት ይቀበላል ከውስጥም ያስተላልፋል ።ይኸንን ማዕከል የሚገልፅና የሚሸከም (Lymph order) አለ በዚህም ውስጥ facia የሚባል ጄል ይገኛል ። ስርዓቱም ልክ እንደ ኢንተርኔት ግንኙነት እንዲቀለውና በየሚሊና ናኖ ስከንዱ የሚወናጨፈውን የትዕዛዝ ስርዓት ማስፈፀምያ ነው ። አሰከትሎም ስሜትን ፣ ትራውማን ፣ የረዠም ጊዜ እተውሎታዊ ኑባሬን ይይዛል ። ቆዳችሁን ለመጠበቅ አመጋገብ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል በተለይም የቫይታሚን ኢ (E) ስርዓት አቀላጣፊ ንጥረ ነገር ተሸካሚዎችን ፣ የማግኒዝየምና ፖታስየም የሚይዙ አመጋገቦችን ማዘውተር የተሻለ የቆዳን አተነፋፈስን ብሎም ጠረንን የማሻሻል ስርዓትን ያቀላጥፋሉ ። ስላነበባችሁ አመሰግናለሁ 🙏🙏 አሰተያየታችሁን ፃፊልኝ ፀሃፊና አዘጋጅ ዝናቡ : ግርማ Lec @Eitex, NLP, CBT , REBT Certified Counselor (አማካሪ ) ለተጨማሪ አገልግሎት +251 916548774 ☎️ #Fitness #coaching #Foodie #fyyypppppppppppppp #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Zinabugirma
Region: ET
Thursday 16 July 2026 15:55:41 GMT
Music
Download
Comments
ⒷⓄⒷⒶ🙏🙏💲 :
ይመችህ ኣምበሳየ ቀጥልበት
2026-07-16 19:16:51
1
ሪች ቡና Rich Coffee :
❤️❤️❤️🥰🥰🥰
2026-07-16 16:03:25
1
To see more videos from user @zinabugirma, please go to the Tikwm
homepage.