@3in1liy: ከትንሽ ደቂቃ በፊት በስልኬ ላይ አንድ ልቤን የነካ አጭር ሐረግ አነበብኩ፦. "እንደሚሞት ሰው እንኑር።" የሚል😔 አነበብኩት... ከዚያም ዝም አልኩ። ምክንያቱም ያ አጭር ሐረግ ዓይኖቼን ሳይሆን ነፍሴን ነካ። ስንቶቻችን ነን ሞትን እንደ ሌላ ሰው ታሪክ የምናየው? በድንገት የምንወደውን ሰው ማጣት ምን ያህል እንደሚያም እያየን፣ አንድ ቀን እኛም እንዲሁ ሊንሞት እንደምንችል፣ ወይም እኛም ለምንወዳቸው ሰዎች ትዝታ ብቻ ልንሆን እንደምንችል... ለምን አናስብም? ዛሬ አብረን የምንስቅበት ሰው፣ ነገ በፎቶው ላይ ብቻ ልንፈልገው እንችላለን። ዛሬ "በኋላ እደውልልሃለሁ" ያልነው ሰው፣ ነገ "በሰላም እረፍ" ብለን የምንሸኘው ሊሆን ይችላል... እኛ ግን እንደማንሞት ሰዎች እንኖራለን! ቂምን እንሸከማለን፤ ይቅርታን እናዘገያለን፤ፍቅርን "በኋላ" እንላለን፤ ንስሐን "ገና ጊዜ አለ" ብለን እናራዝማለን!! ግን... ማን ነገን ቃል ገብቶልናል? መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወታችንን "ለጥቂት ጊዜ ታይቶ የሚጠፋ ጭጋግ" ይለዋል። እኛ ግን ጭጋጉን እንደ ተራራ እንቆጥረዋለን፤ ለዘላለም የምንቆይ ይመስለናል። አንድ ቀን የልባችን የመጨረሻ ምት ይመታል...የመጨረሻ ትንፋሻችን ይወጣል። በዚያ ቀን የሰበሰብነው ሀብት፣ የጠበቅነው ዝና፣ የተከራከርንበት ቂም፣ ያልተናገርነው ፍቅር... ሁሉም ከኋላችን ይቀራሉ!!😑 ከእኛ ጋር የሚቆመው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው... ከክርስቶስ ጋር የነበረን ግንኙነት። ስለዚህ... ዛሬ ከምትወደው ሰው ጋር ጊዜ አሳልፍ። ዛሬ ይቅር በል፤ዛሬ ይቅርታ ጠይቅ፤ዛሬ ጉልበትህን አጥፈህ ወደ ጌታ ቅረብ! ምክንያቱም ዛሬ የምትተነፍሰው ትንፋሽ የአንተ መብት ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረት ነው። ሞትን ማሰብ ሕይወትን መጥላት አይደለም፤ ሕይወትን በጥበብ መኖር ነው። ዛሬን እንደ መጨረሻህ ቀን ኑር፤ ነፍስህን ግን ዛሬ ከጌታ ጋር አስታርቅ። ምክንያቱም ሞት ቀጠሮ አለው... ግን ለእኛ አያሳውቀውም😔 እወዳችኋለሁ!❤ . . . . . . . . . . . #ethiotiktok #fypシ #life #chirstiantiktok

liy🪺
liy🪺
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 17 July 2026 18:22:46 GMT
20873
3213
93
534

Music

Download

Comments

dui25kasdo
dui cr7✌️💥 :
እንኩዋንም አነበብኩ
2026-08-11 20:02:41
22
johngrace275
John Grãcé :
dnk ababal "mot ale" tebareki
2026-07-25 08:53:26
11
netsanet1765
freedam ❤❤ :
ማንበቡ የረዳው ላይክ
2026-08-21 21:49:11
4
geni45133
Geni🍫♊ :
wow lik nahi
2026-08-05 19:37:38
3
yezasewlij4
ye bismar teraw lij negn :
bezi alem mindes yemiyasegn neger kante gar lemenor ewedewalew menoren when mezmur
2026-08-06 03:35:14
2
lina.bahiru
𝕳𝖎𝖑𝖑𝖎𝖓𝖆★ :
እግዚአብሔር በምህረቱ ያስበን
2026-08-05 19:44:41
4
abeni3623
abeni ✝️💎✝️ :
ፈጣር ለካ በብዙ ነገር ያስተምረናል
2026-08-23 13:55:56
3
ruhama2136
Ruhama ✝️✝️ :
wow ewneti new bzuwochachin bezih menged nen yezarewn sansmamabeti sle nege metarek enasbaleni. yene wud geta ybarkshi🥰🥰🥰
2026-07-17 18:32:19
3
forlast1234
Nahi :
geta birik yargish 🥰🥰🙏
2026-07-29 20:33:09
3
sif2979
sif :
Yesss🙏
2026-08-23 12:57:04
0
yiso9616885122310
Yiso ✝️ :
በጣም ❤️‍🩹
2026-07-25 21:28:44
3
tanii9820
Tanii :
awo 🥹 sewu gin kifatun maseb bicha inji melkam neger titoal igizihabiher be mihiretu yasiben be iwenet 🙏🙏
2026-07-28 16:32:05
5
dursit2estephen
Durse✝️ :
Thank you 🙏🥰
2026-07-18 08:29:56
1
ashunazrawi
Ashu ናዝራዊ ✝️ :
ተባረክ የኔ አባት አመሰግናለሁ😳
2026-07-18 07:28:58
1
user18141962390793
ነፃነት :
እግዚአብሔር ይባረክህ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-07-19 14:55:38
1
eyasu_1747
Ey_e♣️✨ :
ምን ማለት እንዳለብኝ አላቅም ግን ጌታ ይባርክሽ 🥰🙏
2026-08-30 18:35:35
0
loftyrooney67
loftyŘoone¥🌨 :
ewnet new 🤝
2026-08-16 07:44:34
3
selam.tefera2
🫧єꪑυƚ𝗂 ✝️🎧 :
Thanks 😊
2026-08-13 13:06:30
3
username00004456853
🎀්‍රර්‍.. :
Ewnet nw ሟቾች endehonen zenegetan nw yhe hulu kentu negr west menegabaw geta ማስተዋላችንን yemeles🙏
2026-08-20 19:22:47
1
abeni53521
@𝖆𝖇𝖊𝖓𝑖. :
በትክክል 👌👌👌wow አገላለፅ 😕
2026-08-30 19:00:49
0
dursit2estephen
Durse✝️ :
ayizon😁
2026-07-18 08:39:58
1
To see more videos from user @3in1liy, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About