@2abdella2022: ሰበር ዜና #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ሀገሬlove #ethiopia Ethiopia federal police #ethiopianforean minister የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በውጭ ሀገር ተደብቀው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ እና ደስታ ተገኝ አበጋዝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በውጭ ሀገር ተደብቀው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ እና ደስታ ተገኝ አበጋዝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። ሁለቱ ዋና ተጠርጣሪዎች የተለያዩ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም 105 ዜጎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ በመውሰድና ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ ከተጎጂዎች በመሰብሰብ፣ በበርካታ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ የቆዩ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዱባይ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ሥር ውለው ለሀገራችን ተላልፈው እንዲሰጡ አድርጓል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በደረሰው ጥቆማ፣ ተጠርጣሪዎቹ ዱባይ ተቀምጠው ሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው አማካኝነት ወጣቶችን በመመልመል ወደ ዱባይ በመላክ፣ በተዘጋጀ የማገቻ ቦታ በማቆየት፣ በተለይ በሴቶች ላይ ጥቃት በማድረስና በማሰቃየት ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽሙ የቆዩ መሆናቸው ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስም ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ሆነው በተቀናጀ መንገድ ወንጀሉን ሲፈፅሙ በቆዩ ዳውድ ተፈሪ ለገሰ እና ደስታ ተገኝ አበጋዝ እና በግብረአበሮቻቸው ላይ የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት፣ ውጭ ሀገር ያሉትን ከዱባይ ፖሊስ ጋር በትብብር በመስራት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሀገራችን ተላልፈው እንዲሰጡ አድርጓል። ተጠርጣሪዎቹ ምንም ዓይነት ሰውን ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል ሕጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው፣ በሀገር ውስጥ ያለው ቡድን ከውጪ ካለው ቡድን ጋር ትስስር በመፍጠርና በተቀናጀ መልኩ "በተለያዩ ካምፓኒዎች ስራ እናስቀጥራችኋለን’’ በማለት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ዜጎችን ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመመልመል፣ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና ያልተገባ ተስፋ በመስጠት ከአንድ ሰው ከ320,000 እስከ 600,000 ብር በመቀበል ማታለያ የቱሪስት ቪዛ አዘጋጅተው በመላክ፣ በሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው በተከፈተ የባንክ አካውንት ገንዘቡን በኢትዮጵያ ብር፣ በድርሃም እና በሪያል ገቢ የሚያስደርጉ መሆናቸውን ፖሊስ ደርሶበታል። ገንዘቡን የከፈሉ ተጎጂዎች ዱባይ እንደገቡ በጉልበት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ፣ ከተጎጂዎች "ኮሚሽን" በሚል ተጨማሪ ገንዘብ በማስከፈል እንዲሁም የሁለት ወር የቱሪስት ቪዛ ሲያልቅ "የሁለት ዓመት የመኖሪያ ፍቃድ እናሰጣችኋለን፤ ካልከፈላችሁ ግን ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳላችሁ" በማለት በአንድ ሰው 1 ሺህ 200 ድርሃም እንዲከፍሉ በማድረግ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ግፍና ስቃይ ሲያደርሱ ቆይተዋል ብሏል ፖሊስ። ተጠርጣሪዎቹ ተጎጂዎችን ከዱባይ ኤርፖርት ከተቀበሉ በኋላ ሰዎችን የሚያከማቹበት ቦታ በመውሰድ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ በርካታ ወንዶችንና ሴቶችን በማገት፣ ምግብ በስምንት ቀን አንድ ጊዜ ደረቅ ሩዝ በመስጠት ለከፍተኛ ርሃብ እና እንግልት እንዲሁም ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት ሲያደርሱባቸው መቆየታቸው ተደርሶበታል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተጨማሪ ባደረገው ክትትል፣ በሀገር ውስጥ ሆነው ዱባይ ካሉት ግብረ-አበሮቻቸው በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ሰዎችን መልምሎ በመላክና የባንክ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያሰባሰቡ የነበሩ 1ኛ ብዙአየሁ አውግቸው በሀይሉ እና 2ኛ ራህመት አበበ እሸቴ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራውን በስፋት በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጿል። ፖሊስ ምርመራውን ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች ተጠቅሞ ይህንን ውስብስብና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀል ለማጣራት እንዲሁም በእነዚህ ተጠርጣሪዎች አማካኝነት ከሀገር ወጥተው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸው ከነበሩ ግለሰቦችና ተጎጂዎች ካሉበት ዱባይ የቀጥታ ቨርቹዋል የምስክርነት ቃላቸውን በመቀበል ላይ ይገኛል። ፖሊስ ሕጋዊ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ ከሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር በመመሳጠር ሕገ-ወጥ ተግባር የሚፈጽሙና በዜጎች ከፍተኛ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙ ኤጀንሲዎችም መኖራቸውን ማረጋገጡን ጠቅሶ በቀጣይ ምርመራውን በእነዚህ አካላት ላይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዚህ ውስብስብ ወንጀል ውስጥ በህጋዊ ሽፋን ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ አካላትን ለመያዝ ከዱባይ ፖሊስና በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቅንጅት በመስራት ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንካራ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጾ፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናውን እያቀረበ፤ ኅብረተሰቡ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፣ 991 ነፃ የስልክ መስመር እና ሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ (SPS)ን በመጠቀም መረጃ በመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፏል። ቀጥለው ያሉትን ሊንኮች በመጫን ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ፦ የአማርኛ ቋንቋ ገፅ https://web.facebook.com/EthiopianFederalPolice1/ አፋን ኦሮሞ የፌስቡክ ገፅ፦ https://www.facebook.com/share/17XCJoHbNy/ እንግሊዝኛ የፌስቡክ ገፅ፦ https://www.facebook.com/share/17YzrnrEVk/ ዌብሳይት www.federalpolice.gov.et ቴሌግራም https://t.me/efpmedia ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianfederalpolice... የዩቲዩብ ገፅ https://youtube.com/@ethiopianfederalpolice...
Abdallah 🇶🇦🫶🇪🇹
Region: QA
Saturday 18 July 2026 07:50:48 GMT
Music
Download
Comments
Ethiopia :
this good news
2026-07-18 12:51:55
1
Alex :
thank Ehiopla poilce
2026-07-18 13:49:11
0
ሰሎሜ :
ነገ ይወጣሉ ባለ ጊዜ ናቸው
2026-07-18 13:01:12
1
~ወሎየዋ❣️🔥🇪🇹🤝🇦🇪🔐 :
እባካችሁ እኛም ተበልተናል ካአድቤት ሁለሰው የተበላነውስ
2026-07-18 13:33:56
1
user7380599528104 :
Tikikil 😢
2026-07-18 15:17:49
0
mikc :
2026-07-18 14:15:16
0
fekedu :
🙏🏽🙏🏽🙏🏽😭💪💪💪💪
2026-07-18 13:34:41
0
Mekdi :
Abso qatar lalu delaloch hg hay malet alebet ???
2026-07-18 13:25:16
0
Farus Farus :
💪💪💪💪💪💪💪
2026-07-18 09:07:32
0
Aeminu :
yegezeb sew nahew yiwetalu
2026-07-18 13:23:18
0
user42324435575954fetiya :
❤️❤️❤️አዎ ወላሂ መቀጣት አለባቸው
2026-07-18 07:55:20
1
@ Rawaan,21🇪🇹🇬🇧👩🏽🤎 :
yes
2026-07-18 09:30:14
0
❤💚 :
አደራ እንዳይወጡ 🙏
2026-07-18 13:44:32
0
aminh :
እባካቹ ተጎድቸሀሌሁ
2026-07-18 13:27:15
0
Farus Farus :
2026-07-18 09:07:14
0
obbsee 🇶🇦 😘🇪🇹✅️💯 :
as wr wb akkm abdla basibortii ji.a 3 hanga harosuuf garuu naaf hin dawalee
2026-07-18 13:02:08
0
salame :
Er Enem Tababrugn Ebskchu400 Tablichlhu
2026-07-18 12:53:15
0
BE Strong 🫂 :
are sra felguln Qater
2026-07-18 14:20:15
0
🇪🇹🇶🇦 مفتاخሚፈታህQat 🇪🇹🇶🇦 :
🥰🥰🥰
2026-07-18 13:24:35
0
Abi. A... 🇦🇪 🇦🇪 :
👍👍👍
2026-07-18 14:44:11
0
Abduu shashee :
🥰🥰🥰
2026-07-18 14:44:11
0
wanshat :
🥰🥰🥰
2026-07-18 09:01:41
0
To see more videos from user @2abdella2022, please go to the Tikwm
homepage.