@tesemamukura: “ወንዝ ሲፈስ አነስተኛ የመቋቋም ብቃት ወዳለው አቅጣጫ እየተጣጠፈ ነው የሚዘልቀው” ይባላል፡፡ አቅሙ የሚፈቅድለት ቁልቁለቱ እያለለት ወንዝ ከአቅሙ በላይ ወደሆነው ወደዳገቱ አይፈስም፡፡ እንደ አቅሙ የሆነው እያለለት ወንዝ ከአቅሙ በላይ የሆነውን፣ “ለምን አያሳልፈኝም” እያለ አይታገልም፡፡ አሁን ስለቀለለው ወደቀኝ ታጥፎ፣ ወዲያው ሲከብደው ወደግራ ሊታጠፍ ይችላል፡፡ በዚህ የፍሰት ባህሪይው የወንዝ መጨረሻው የአካባቢው ዝቅተኛው ስፍራ ነው፡፡ የወንዝ ባህሪይ ግን ከላይ የተገለጸው ብቻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኮ ወንዝ ወደከፍታም የሚፈስበት ጊዜ አለ፡፡ ወንዝ አቅሙን ሲያጠራቅም፣ ሲበረታና ኃይል ሲኖረው በፊቱ ያለውን ከፍ ያለ ነገርም ቢሆን ሞልቶና አልፎ ይሄዳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወንዝ ሲበረታ ከፍተኛውን ስፍራ እስኪሞላ ድረስ “ወደ ላይ ይፈስሳል”፡፡ ከወንዝ ተማር፡፡ ከአቅምህ በላይ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህ ለምን መንገድ አይለቁም ብለህ እስክትደማ አትታገል፣ ወይም ደግሞ ወደኋለ አትመለስ፡፡ ብልሃት ፈልገህ ዘወር ብለህ እለፍ፡፡ ሆኖም ያንን እያደረክ ሳለህ፣ አቅምህን አጠራቅም፡፡ አቅም በጨመርክ ቁጥር መንገድ እየቀየርክና ጠመዝማዛ ጎዳናን በመጓዝ መድከምህ ያበቃና ቀጥ ብለህና በፊትህ የሚቆመውን እየገረሰስክ ማለፍ ትጀምራለህ፡፡ • የስሜት ጽንአት አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያ ግን የወቅቱን የስሜት ጽንአት ባገናዘበ ሁኔታ ተራመድ፡፡ • የገንዘብ አቅምህን አጠራቅም፣ ለጊዜው ግን ኑሮህን ካለህ የገንዘብ አቅም ጋር በማገናዝ ተንቀሳቀስ፡፡ • የግንኙነት መረብህ (Network) አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያው ግን አጠገብህ የሚገኙ ሰዎች በሚደግፉህ ደረጃ ተራመድ፡፡ • የእውቀት አቅምህን አጠራቅም፣ እስከዚያው ግን ባለህ እውቀት የምትችለውን ስራ በመስራት ኑሮህን ግፋ፡፡ ልክ እንደ ወንዝ ሁን!!! (ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
tesema
Region: ET
Saturday 18 July 2026 13:58:02 GMT
Music
Download
Comments
Kk adama :
amemgne🥰🥰🥰🥰
2026-08-13 18:45:34
1
EME Power :
ትክክል ብሮ
2026-07-18 18:30:40
1
ahmmedmohammed :
እናመሰግናለን
2026-08-11 05:22:37
0
gech :
እውነትነው ብሮ👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍
2026-07-28 14:32:42
0
farxiyaxashi3 :
በትክክል 🥰🥰🥰
2026-07-21 14:18:59
0
siraj :
ትክክል
2026-07-27 07:26:03
0
MTS :
❤️
2026-07-27 17:11:48
0
user7212436223750 :
correct
2026-07-21 10:30:55
0
𝑏𝑖𝑛,🇮🇱🇮🇱🇪🇷🇪🇷 :
ewenete new
2026-08-01 07:00:47
0
mola kabew :
እውነት ነው 🙏🙏🙏🙏
2026-08-06 14:48:31
0
Daniel :
እውነትነው
2026-08-01 22:17:38
0
nivana :
አልቻልኮም
2026-07-18 16:17:25
1
@sis06 :
ልፋቴስ
2026-08-01 09:28:12
0
zelalem hayilu :
🥰🥰
2026-08-04 21:02:32
0
Alazar :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-03 13:44:08
0
dagi & atu :
👍👍👍👍👍👍👍👍
2026-08-29 14:20:58
0
endash :
💚💚💚
2026-07-25 15:36:49
0
m sis :
🥰🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤️❤️
2026-07-25 12:55:47
0
Alexander fikrsew :
❤️🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-21 12:36:44
0
enda asmare :
🥰🥰🥰
2026-07-18 16:41:43
0
Kk adama :
🤲🤲🤲🤲🤲🤲
2026-08-13 18:45:11
1
To see more videos from user @tesemamukura, please go to the Tikwm
homepage.