@zegedamat: ስዕለት ሰሚው ቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል → ዘወትር ብዙ ድንቅ ገቢረ ተአምራት የሚፈጸምበት መካነ መንክራት፤ → በቅዱስ ገብርኤል ምልጃ ተማምነው በመድኃኔዓለም ቸርነት አምነው የለመኑት በጎ መሻት ሁሉ ፈጥኖ የሚፈጽምበት የብዙዎች መካነ ጸሎት፤ → ጥንታዊውን ተአምረኛ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በ፱ኛው መ/ክ/ዘ ከዝዋይ ወደ ቦታው ይዘው የመጡትና በቦታው ላይ ለብዙ ጊዜ ተጋድሎ ያደረጉት የታላቁ ጸሎተኛ አባት የአባ ሌዊ ዘገዳመ ሲሐትና የሌሎችም ቅዱሳን የቃልኪዳን በረከት የሚገኝበት መካነ ቅዱሳን፤ → በርካታ ስውራን ዘወትር የሚጸልዩበት መካነ ግኁሣን፤ → ከጥንት ነገሥታትና ሹማምንት ጀምሮ በርካቶች በቦታው ላይ የተሳሉት ስዕታቸው እየሰመረላቸው "እሰይ ስዕለቴ ሰመረ!" እያሉ መባቸውን በደስታ የሚያገቡለት ስዕለት ሰሚ ነው። ★ እግዚአብሔር በልብ የመከረውን፣ በቃል ያስነገረውን እርሱ በወደደና በፈቀደ ጊዜ ያከናውናልና የእርስዎም ከእኛ ጋር ተጉዘው ስእለትዎ ሰምሮ እንዲመለሱ እንሻለን። "ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው" (መዝ ፻፲፰፥ ፻፳፮) እንዲል። ★ የጉዞ ምዝገባ ልናጠናቅቅ ጥቂት ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን ከማኅበራችን ጋር ለመጓዝ አስቀድመው እንዲመዘገቡ እናሳስባለን። * መነሻ፦ ሐምሌ 17 ጠዋት 10፡30 * መመለሻ፦ ሐምሌ 20 * የጉዞ ዋጋ ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 👉🏾 በመደበኛ ደረጃ 1 አውቶቡስ 5000 ብር ምግብን ጨምሮ 6500 ብር 👉🏾 በልዩ ባስ 8000 ብር 👉🏾 በባቡር 12000 ብር * ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877 * ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ኑ አብረን እንጓዝ! 👉 "ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን አስታሰው ለወዳጆችዎ ያካፍሉት። #ቅዱስገብርኤል #ቅዱስ_ገብርኤል_ከክፉ_ነገር_ይጠብቀን #ቁልቢ_ገብርኤል #habeshatiktok #fyp @አንተነህ ዘዋልድባ @መቅረዝ ሚዲያ MEKREZ MEDIA @@ sami - asbot 7 ዘ ደብረ ወገግ @Miki Miko

ይሩማሊስ ገዳማዊ - እመጓ እመ እጓል
ይሩማሊስ ገዳማዊ - እመጓ እመ እጓል
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 20 July 2026 14:59:59 GMT
2074
419
4
48

Music

Download

Comments

mekoreta
መኮሬታ የገዳማት ትሩፋት :
አዝኛለሁና ባንተ ልጽናና ናና ገብርኤል ናና 🙏🥰🙏
2026-07-20 16:35:57
0
betewali
አንተነህ ዘዋልድባ :
ገብርኤል ናና 🥰🥰🥰🙏🙏🙏🥰🥰🥰
2026-07-20 16:25:04
0
etaferahu21164
@etaferahu2116 :
🙏🙏🙏
2026-07-20 23:36:53
0
bereket32315
B ር K ት ❤️‍🩹 :
👌👌👌
2026-07-24 16:28:29
0
To see more videos from user @zegedamat, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About