@menordegu121921: አውቃለሁ… አሁን ላይ ፊቴን ማየትም ሆነ ድምፄን መስማት እንደማትፈልጊ። ግን አንድ እውነትን ስላሳወቅሺኝ አመሰግንሻለው። ማንም ሰው ካለ አቅሙና ካለ ልኩ ሲወድ መጨረሻው ይሄው ነው። ልብሽ ዛሬ በኔ ላይ የቆረጠው፣ ካንቺ ጥፋት የተነሳ አይደለም። ፍቅሬ ስለበዛ፣ መውደዴ ልክ ስላጣና ፍቅሬ ስለሰለቸሽ ነው። እስኪ አስቢ የትኛው ጥፋቴ ነው እንዲህ ጨካኝ ያደረገሽ? በየደቂቃው ደህንነትሽን ለመጠየቅ መባከኔ? ያንቺን ደስታ ለመፍጠር ስል የራሴን ሰላም አሳልፌ መስጠቴ? ወይንስ አንቺን ላለማጣት ስል ሁልጊዜ እራሴን ዝቅ አድርጌ ይቅርታ መጠየቄ? አዎ! በጣም ማፍቀሬ አሳጣኝ። ላንቺ ያለኝ ቦታ ከፍ እያለ ሲሄድ በልብሽ ውስጥ ያለኝ ክብር ግን እየቀነሰ መጣ። እኔ ሙሉ ህይወቴን ላንቺ ስሰጥ አንቺ ግን እንደ ቀላልና ሁልጊዜም እንደማይጠፋ ዋስትና አድርገሽ ቆጠርሽኝ። ሰው የሚገርም ፍጡር ነው፤ በጣም ሲወዱት እና በፍቅር ሰይዙት፣ የሚወደውን ልብ ጥሎ መሄድ ይቀለዋል። አንቺም ያደረግሽው ይሄንኑ ነው። ትላንትና አንቺን ላለማስከፋት ስል የከፈልኳቸው መስዋዕትነቶች ሁሉ ዛሬ ተመልሰው እንደ ሹል ጦር ልቤን እየወጉት ነው። አንቺ ከአንገትሽ በላይ "አልፈልግህም" ስትይ እኔ ግን ከልቤ አልቅሼ "ለምን?" እያልኩኝ እጠይቃለሁ። ይሁን… ልብሽ ከቆረጠ አይመለስም። ነገር ግን አንድ ቀን የዚህ ሁሉ ዝብርቅርቅ ዓለም ጩኸት ፀጥ ሲል እኔ ላንቺ የሆንኩልሽኝ የሚሆን ሰው ስታጪ የኔን ፍቅር ማስታወስሽ የማይቀር ነው። ያኔ ግን እኔ በፍቅርሽ የተሰበረውን ልቤን ጠግኜ ካንቺ ርቄ የትም ደርሻለሁ። አሁን የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው ። ልብሽ በኔ የቆረጠው እኔ ስላስቀየምኩሽ ሳይሆን፣ ካለሽ አቅም በላይ ስላፈቀርኩሽና ፍቅሬ ስለበዛብሽ ነው! ማለቂያ ለሌለው ፍቅሬ የሰጠሽኝ ስጦታ ይሄ ከሆነ… በሰላም ሂጂ!
ትላንት ዛሬ አይደለም
Region: ET
Tuesday 21 July 2026 05:05:20 GMT
Music
Download
Comments
~ናፍቆት ለካ ትልቅ ህመም ነው~ :
2026-07-26 16:02:12
1
Zebiba Shelema :
ደስ የሚል ታሪክ በዉነት ደስ ሲል👌👌👌👌👌
2026-07-30 09:29:28
0
🌿MG ❤❤🌿🌿🌿🌿 :
🥰
2026-07-25 13:09:57
1
Habto Cr7 የማንቸው :
🤟
2026-07-30 08:19:50
0
ለራሴ ይቅርታ 🙏🙏 :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-27 08:56:16
1
ትላንት ዛሬ አይደለም :
❤
2026-07-23 10:22:01
1
mula :
😔😔😔😔😔
2026-07-27 14:01:29
1
እኔ እኔ ነኝ✝️ :
🥰🥰🥰
2026-07-21 13:35:43
1
ትላንት ዛሬ አይደለም :
🥰🥰🥰
2026-07-28 09:59:24
1
To see more videos from user @menordegu121921, please go to the Tikwm
homepage.