@kiya_ko11: የኔ ሰዎች we all remember አይደል እውነተኛ ማንነቱንና የአባቱን ቤት ክብር ዘንግቶ፣ የዓለምን ደስታ ፍለጋ ወደ ሩቅ አገር የኮበለለው ያ የጠፋው ልጅ! የያዘውን ሁሉ አባክኖ፣ በራብና በችግር ተመትቶ፣ በአሳማዎች መካከል ተጥሎ መኖሩ የዕለት ተዕለት ሕይወቱ በሆነ ጊዜ ነበር... to his senses የተመለሰው። "በአባቴ ቤት እኮ ሰራተኞች እንኳ ይተርፋቸዋል፤ እኔ ግን እዚህ በራብ ልጠፋ ነው" ብሎ ወደ አባቱ ቤት ለመመለስ ወሰነ። ገና ንስሐውን ሊናገር፣ "ልጅህ ልባል አይገባኝም" ሊል እየተለማመደ while he was still a long way off ግን... አባቱ አየው። አባቱ አልተቆጣውም፣ አልገፋውም፤ he was filled with compassion፣ እየሮጠም ሄዶ አንገቱ ላይ ወደቀ፣ ሳመው፣ አቀፈው። የሰባውን ጥጃ አርዶ፣ ምርጡን ልብስ አልብሶ፣ the ring and shoes መለሰለት። ያቺ የጠፋች ነፍስ አባቷ ጋር ስትደርስ ክብሯ ተመለሰላት፤ አረፈች:: አባቴ ሆይ እኔም እንደዚሁ የጠፋሁ ልጅህ ነኝ። ካንተ ፍቅር ርቄ፣ የዓለምን ምድረበዳ ፍለጋ ስንከራተት፣ በገዛ እጄ ሕይወቴን ሳበላሽና ስጠማ ዝም ያላልከኝ አምላክ ነህ። ዛሬም እንደዚያ ልጅ ወደ ልቤ ተመልሼ፣ በበደሌ ተጸጽቼ ወደ አንተ እመጣለሁ። "ልጅህ ልባል አይገባኝም" ብዬ ብደነግጥም፣ አንተ ግን አሁንም በሩቅ ሳለሁ with your open arms በፍቅርህ እቅፍ ልትቀበለኝ ትሮጣለህ። አባቴ ሆይ የጠፋችውን፣ የዛለችውንና የኮበለለውን ነፍሴን ፈልገህ ስለምታገኛት፣ ክብሬንና ሰላሜን ስለምትመልስልኝ አመሰግንሃለሁ። Without you, I am nothing... ካንተ እቅፍ ውጪ ሌላ መጠጊያ የለኝምና ሁልጊዜም በአንተ ቤት ውስጥ አሳርፈኝ። ተባረኩልኝ🤗
K I Y A🍁
Region: ET
Wednesday 22 July 2026 09:36:10 GMT
Music
Download
Comments
selina🌺 :
caption 🥺🥺
2026-07-22 12:31:22
1
abigiya💫 :
🥰🥰
2026-07-22 16:11:10
1
𝑮𝒂𝒅𝒊𝒔𝒂🎭 :
🥰🥰🥰
2026-07-22 13:24:55
1
To see more videos from user @kiya_ko11, please go to the Tikwm
homepage.