@ngatay.store: #ngatayboutique #moingaymotoutfit #aosomi

Nga Tây
Nga Tây
Open In TikTok:
Region: VN
Friday 24 July 2026 02:46:50 GMT
4164
94
3
0

Music

Download

Comments

khongtangai123
Có vợ rồi :
quay kiểu nào cùng thấy đẹp
2026-07-24 07:19:45
0
trungvipok
Trungvipok :
👍
2026-07-24 02:52:22
0
minh.x7152
Minh Xỳ :
🥰🥰🥰
2026-07-24 03:00:23
0
To see more videos from user @ngatay.store, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

የ«ጥሩ ሙስሊም» እና የ«መጥፎ ሙስሊም» ፍረጃ ፖለቲካ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በአሕመዲን ጀበል ፣ ክፍል 1 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስለ ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው፣ ስለእኩልነትና እኩል ተጠቃሚነት፣ ፣ስለሀገራዊና መንግስታዊ ዉክልና፣ስለታሪክና ትርክት አካታችነት፣ መጅሊሱና መስጂዶቻቸው ነፃነት፣ እንዲሁም ስለ ፍትሐዊ ሀገራዊ ውክልና ድምፃቸውን ባሰሙ ቁጥር ጥያቄያቸው ከመፈተሹ አስቀድሞ እነርሱን የመክሰስ ዘመቻ ይቀድማል።  ባለሥልጣናትና የፖለቲካ ልሂቃን «ጥያቄያቸው ሕጋዊ ናቸው? በማስረጃስ ተደግፏል?» ብለው ከመጠየቅ ይልቅ ይህንኑ የፍረጃ ስልትን በመጠቀም «አክራሪዎች ናቸው! ከፋፋዮች ናቸው! የውጭ አስተሳሰብ ተሸካሚዎች ናቸው!» የሚል የስም ማጥፊያ ውርጅብኝ ያወርዱባቸዋል። ቀጥለውም ሕዝብን አንገት ለማስደፋት የቀመሯቸውን «ጥሩ ሙስሊም» እና «መጥፎ ሙስሊም» የሚሉ የፍረጃ ታፔላዎች ይለጥፋሉ። የአሁኑ የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ አባት የሆኑት ታዋቂው ምሁር ማሕሙድ ማምዳኒ እ.ኤ.አ. በ2004 ባሳተሙት መጽሐፋቸው (Good Muslim, Bad Muslim: America, the Cold War, and the Roots of Terror)፣ ከመስከረም 11 ጥቃት በኋላ በምዕራቡ ዓለም ሚዲያና የፖለቲካ መድረኮች የተስፋፋውን ይህንኑ መርዛማ ክፍፍል አጋልጠዋል።  ከውጭ የተቀዳው ይህ በአክራሪነትና በአሸባሪነት የመፈረጅ ስልትና ትርክት በሀገራችንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎችን ለማፈን ዋነኛ መሣሪያ ሆኖ ቆይቷል።አሁንም እየዋለ ነው። በዚህ ሥሌት አንዳንድ ሙስሊሞች «ሚዛናዊ ሙስሊም» ወይም «እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት የሚታይሸት»፣
የ«ጥሩ ሙስሊም» እና የ«መጥፎ ሙስሊም» ፍረጃ ፖለቲካ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በአሕመዲን ጀበል ፣ ክፍል 1 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስለ ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው፣ ስለእኩልነትና እኩል ተጠቃሚነት፣ ፣ስለሀገራዊና መንግስታዊ ዉክልና፣ስለታሪክና ትርክት አካታችነት፣ መጅሊሱና መስጂዶቻቸው ነፃነት፣ እንዲሁም ስለ ፍትሐዊ ሀገራዊ ውክልና ድምፃቸውን ባሰሙ ቁጥር ጥያቄያቸው ከመፈተሹ አስቀድሞ እነርሱን የመክሰስ ዘመቻ ይቀድማል። ባለሥልጣናትና የፖለቲካ ልሂቃን «ጥያቄያቸው ሕጋዊ ናቸው? በማስረጃስ ተደግፏል?» ብለው ከመጠየቅ ይልቅ ይህንኑ የፍረጃ ስልትን በመጠቀም «አክራሪዎች ናቸው! ከፋፋዮች ናቸው! የውጭ አስተሳሰብ ተሸካሚዎች ናቸው!» የሚል የስም ማጥፊያ ውርጅብኝ ያወርዱባቸዋል። ቀጥለውም ሕዝብን አንገት ለማስደፋት የቀመሯቸውን «ጥሩ ሙስሊም» እና «መጥፎ ሙስሊም» የሚሉ የፍረጃ ታፔላዎች ይለጥፋሉ። የአሁኑ የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ አባት የሆኑት ታዋቂው ምሁር ማሕሙድ ማምዳኒ እ.ኤ.አ. በ2004 ባሳተሙት መጽሐፋቸው (Good Muslim, Bad Muslim: America, the Cold War, and the Roots of Terror)፣ ከመስከረም 11 ጥቃት በኋላ በምዕራቡ ዓለም ሚዲያና የፖለቲካ መድረኮች የተስፋፋውን ይህንኑ መርዛማ ክፍፍል አጋልጠዋል። ከውጭ የተቀዳው ይህ በአክራሪነትና በአሸባሪነት የመፈረጅ ስልትና ትርክት በሀገራችንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎችን ለማፈን ዋነኛ መሣሪያ ሆኖ ቆይቷል።አሁንም እየዋለ ነው። በዚህ ሥሌት አንዳንድ ሙስሊሞች «ሚዛናዊ ሙስሊም» ወይም «እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት የሚታይሸት»፣ "ነባሩ ሙስሊም"ተብለው ሲወደሱ፣ ሌሎች ደግሞ «ጽንፈኛ» "አክራሪ ሙስሊም" ፣«አደገኛ» ተብለው ይፈረጃሉ። ማምዳኒ ያጋለጡት ሰዎችን በተጨባጭ ድርጊታቸው ከመመዘን ይልቅ ከሚያሳዩት ሁኔታና በሃይማኖታዊ ማንነታቸው የመክፈሉን ሴራ ነው። የፖለቲካ ባህሪን በሃይማኖት ሽፋን ማብራራትም ከጀርባ ያለውን ታሪካዊ በደል ለመደበቅ የሚውል ዘዴ መሆኑን አስገንዝበዋል። ከእምነት ይልቅ ታዛዥነትን መመዘን 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በዚህ የፖለቲካ አፈና ውስጥ «ጥሩ» የሚባለው ሙስሊም እምነቱን በቤቱ አጥር ውስጥ ብቻ ቀብሮ እንዲያቆይ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አፉን እንዲዘጋና ነባሩን የተዛባ የሥልጣን አሠራር እንዳይጠይቅ ይገደዳል። ለገዥው ሥርዓት ወይም ትርክት ያጎበደደና ራሱን አሳልፎ የሰጠ ሰው ብቻ ተቀባይነት ያገኛል። በሀገራቺንም በዚህ መልኩ የሌላው ካምፕ ዉዳሴን በመሻት አንዳንዶች ግልጽ በወጣ የመብት ጥሰትና አድሎ ላይ ጭምር ዝምታን የሚመርጡ አሉ።ጥቂቶች ደግሞ እነርሱ አባል ነን ከሚሉበት ማህበረሰብ ጎን ከመቆም ራሳቸውን ከተቀናቃኝ ጎራ አሰልፈው "ጥሩ ሙስሊም" የሚለውን ስያሜ ለማግኘት የሚተጉም አሉ። በእስልምና እሴቶች ላይ የተመሠረተ ነጻ አቋም የሚያራምድ፣ የመንግሥትን የተሳሳተ ውሳኔ የሚተች፣ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ ያሉ የአድሎ አሰራር እንዲቀየሩ፣ተገቢውን ዉክልና እንዲያገኙ ድምጻቸውን የሚያሰሙ፣የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ወይም ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እኩል የዜግነት መብት እንዲከበር የሚጠይቅ ባለመብት ሁሉ በተቀነሰቃኝና በአፋኞች ዘንድ «መጥፎ» ተብሎ ይፈረጃል። ሕገ-መንግሥታዊ መብት የዜግነት መገለጫ እንጂ ለታዛዥ ባሪያዎች የሚታደል የገዥዎች ችሮታ አይደለም። መብት መጠየቅ ፈጽሞ ጽንፈኝነት ሊሆን አይችልም። ጥያቄው በማስረጃና በሕግ መመርመር ሲገባው በጠያቂው ሃይማኖታዊ ማንነት ብቻ መፍረድ ሆን ተብሎ የሚፈጸም የመብት ነጠቃ ነው። ፖለቲካዊ በደልን በሃይማኖት ካባ መሸፈን ❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌ ውስብስብ የፖለቲካ፣ የታሪክና የማኅበራዊ ግጭቶችን በሃይማኖት ብቻ መሸፈን ትክክለኛ ምክንያቶችን ከውይይቱ ሆን ብሎ የማስወገድ ዘዴ ነው። የመንግሥትን ብልሹ አሠራር፣ የፖለቲካ በደልን ወይም ያልተመጣጠነ የሥልጣን ግንኙነትን ከመመርመር ይልቅ እስልምናን የችግሩ ምንጭ አድርጎ ማቅረብ ለበዳዮችና የበዳይ ስርዓት ናፋቂዎች ይቀላቸዋል። በተመሳሳይ መልኩ በነበረው አጼያዊ በዳይ ስርዓት ከሚገባው በላይ ያገኘ አካል የእኩልነት ጥያቄ ሲነሳ ጥያቄውን ሳይሆን ጠያቂዎችን በመጥፎ ሙስሊምነት በመፈረጅ የተለያዩ ታርጋዎችን ይለጥፍባቸዋል። የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ሀገር በቀል የመብት ጥያቄ «የውጭ አስተሳሰብ» እያሉ መፈረጅም ዜጎችን ከሀገራዊ ባለቤትነት የማግለል ስልት ነው። በዚህም ሙስሊሞች ሕጋዊ መብታቸውን ከመጠየቃቸው በፊት ራሳቸውን ከተፈጠረባቸው የሐሰት ጥርጣሬ እንዲያጸዱ በአንገት ላይ የሚንጠለጠል ገመድ ይጣልባቸዋል። «ታማኝነታችሁን አስመስክሩ!» 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 «ጥሩ ሙስሊም» እና «መጥፎ ሙስሊም» በሚለው የፐለቲካ ፍረጃ ፣ ሙስሊሞች ተቀባይነት ለማግኘት ታማኝነታቸውን ደጋግመው እንዲ ያስመሰክሩ ይጠበቅባቸዋል። በሙስሊም ስም ወንጀል ሲፈጸም፣ ከድርጊቱ ጋር ያልተያያዙ ሙስሊሞችም ጭምር በአደባባይ እንዲያወግዙት እና ራሳቸውን ከፈጻሚዎቹ መራቃቸውን ደጋግመው እንዲናዘዙ ይጠየቃሉ። ዝም ካሉ ከጥፋቱ ጋር እንደተባበሩ ሊቆጠሩ ይችላሉ፤ ጉዳዩ በማስረጃ ይመርመር ቢሉም ተጠርጣሪ ሊሆኑ ይችላሉ። ታማኝነታቸውን በተግባር ካረጋገጡ «ጥሩ ሙስሊም»፣ ካላረጋገጡ ደግሞ «መጥፎ ሙስሊም» ይባላሉ። መከፋፈልና ውክልናን መቆጣጠር ⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕ «ጥሩ» እና «መጥፎ» በሚሉ መለያዎች ሙስሊሞችን ለሁለት መክፈል የማኅበረሰቡን አንድነት ለመናድና ማን እንደሚወክለው በገዥዎች ፈቃድ ለመወሰን የሚጠቀሙበት ሴራ ነው። ለመንግሥት ያደሩ የሃይማኖት መሪዎችና ተቋማት «የሰላምና የመቻቻል ተምሳሌት» ተብለው ሲወደሱና ሲሸለሙ፣ ገለልተኛ ሐሳብ የሚያቀርቡ ምሁራን፣ የመብት ተሟጋቾችና ተቋማት ግን «አክራሪ»፣ «ሃይማኖትን ወደ ፖለቲካ የሚያስገቡ» ወይም «የውጭ ተላላኪ» ተብለው ይፈረጃሉ። ልብ ብለህ ካየህ ጨቋኞቹና የበዳይ ስርዓት ናፋቂዎች «ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ ናቸው» የሚለውን መርሕ ትዝ የሚላቸውና የሚያነሱት ሙስሊሞች መብታቸውን ሲጠይቁ ብቻ ነው፤ በተግባር ግን በሃይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ እጃቸውን ከመክተት አይመለሱም። እንዲያውም የናንተን የሃይማኖት መሪዎች ጉዳይ የኛ ጉዳይ ነው ሲሉም ታያለህ። በዚህ ሴራ የመብት ጥያቄው ይታፈናል፤ ጠያቂዎቹም ከሕዝባዊ መድረክ ይገለላሉ። ዝም ብለው ሲኖሩ «ጥሩ» እየተባሉ ሲወደሱ የነበሩ ሙስሊሞች መብታቸውን በጠየቁ ቅጽበት «መጥፎ» የሚል ስም ከተለጠፈባቸው፣ ይህ የሚያጋልጠው የሙስሊሞቹን የእምነት ደረጃ ሳይሆን የጨቋኞችን የአፈና ስልት ነው። ልብ ብሎ ያስተዋለ ሰው የሚረዳው እውነት ይህ ነው። ሙስሊሞች በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ ትንኮሳና ጥቃት እየደረሰ፣ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ቀጥሎ ሳለ ሙስሊሞች ዝም እስካሉ «ጥሩ ሙስሊም» ናቸው፤ መብታቸውን ሲጠይቁና ነባሩን አሠራር ሲተቹ ግን «መጥፎ ሙስሊም» ተደርገው "ወሃቢያ"፣ "አክራሪ" ወዘተ ይባላሉ። ይቀጥላል...

About