@titi.16.2026: ❖ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው⁉❖ ••✥ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን✥አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ✥ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ይህ ✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ ✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ ✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ ✥ገብርኤል ነው✥ የአሸናፊና የኃይል መልአክ ✥ገብርኤል ነው✥ ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ ✥ገብርኤል ነው✥ "የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን" ❖አሜን❖ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር
Titi Ze Tewahedo✝️📚🇨🇦
Region: SA
Saturday 25 July 2026 17:56:01 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @titi.16.2026, please go to the Tikwm
homepage.