@sewadam0: ግንቦት 16/1983 ማለዳ 12፡15 የፖለቲካ ክፍል አጠገብ ለውበት የተተከለው የአበባ እርሻ የመረጥነው አመቺ ስፍራ ነበር። ድቅድቅ ያለ ጨለማ በመሆኑ በሰማይ ላይ ተዘርተው ቁልቁል የሚሆነውን ሁሉ በትዝብት የሚመለከቱ ከሚመስሉት ክዋክብት በቀር ማንም አያየንም ነበር። ግማሾቻችን እየጠበቅን፣ ሌሎቻችን እያሸለብን አስጊውንና አደገኛውን ሌሊት በሰላም አሳለፍን። ገና ከሌሊቱ 11፡00 ሰዓት ገደማ ወገግ ሲል ሁላችንም ተነሳን፤ በፍጥነት ተጸዳዳንና ከተዘጋጀን በኋላ በእቅዳችን መሠረት ወደ ሚኒስቴር ቤቱ አመራን ሚንስ ቤቱ መስሪያ ቤቱን ከተከፈተ በፍቅር፣ ካልተከፈተ ደግሞ በግድ ሰብረን ለመግባት ወስነናል። ተፍተፍ እያልኩ ስዘጋጅ ሳለ ሌላኛው የክፍላችን የወደቁ መኪና ማንሻ ባራንኮ (የወደቁ መኪናዎች ማንሻ ክሬን የጫነ) ተሽከርካሪ በርካታ የሠራዊቱ አባላት እንደ ንብ ወረውት ግቢውን በከፍተኛ ፍጥነት እየበረረ ጥሎ ሲወጣ እንደ ዘበት አየሁት፤ የመጨረሻው መሰለኝ። ይህን ማስታወሻ የምጽፈው የሚንስቤቱ የምግብ ጠረጴዛ ላይ ሻይ እየጠጣሁ ነው። ይህ ዕለት ለእኛ እንደ ማንኛውም ቀን አይደለም፤ ይልቁንም ለሕይወታችን ወሳኝ የሆነና ገና ያልተረዳነውን አዲስ ምዕራፍ የያዘ ነው - ሕይወት መቀጠል ወይም መሞት ሚለው የሚወስንበት ነው አብዛኛው ሠራዊት ሌሊቱን ባገኘው ተሽከርካሪ እየታጨቀና እየተንጠላጠለ ሲበር ነው ያደረው። ወገግ ሲል የቃኘውን ግቢ ተዘዋውሮ የተመለከተው ሰው አስገራሚ ትዕይንት ነበር የተለያዩ ወረቀቶችና ቁሳቁሶች በየሜዳው ተበትነዋል፤ ቢሮዎች፣ ሱቆችና ቤቶች በሮቻቸው ወለል ብለው ተከፍተዋል። እንደኛ ጥቂት ወታደሮች ውር ውር ከማለታቸው ውጭ ግቢው ባዶ ሆኗል። የገረመኝ የሚንስ ቤቱ ሠራተኞች ሌሊት ምን እንደተፈጠረ የሚያውቁ አይመስሉም አብዛኞቹ የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለመከወን ወዲያ ወዲህ ይላሉ። ምግቤቱ በሰዓቱ ተከፍቶ የቁርስ ተመጋቢዎችን እየጠበቀ ነው። እኛም እንደ ግሩፕ በእቅዳችን መሠረት ኮዳዎቻችንን በውሃና በሻይ ሞልተን እንዲሁም የተለያዩ ምግቦችንና ስኳር የቻልነውን ያህል ይዘን ለጉዞ ተዘጋጅተናል። ችግር ወይም ተቃውሞ እንዳይገጥመን የምግቤቱ ሠራተኞች ሁሉም ነገር ማብቃቱን መንገር በቂ ነበር። እነርሱ ገና ተደናግጠው ሲርበተበቱ እኛ የምንፈልገውን ለማዘጋጀት ችለናል። አሁን ከዚህ በኋላ ተመካክረን በምንመርጠው አቅጣጫ እንጓዛለን። የአብዛኛው ምርጫ የሆነውን የከረን ሱዳን መንገድን ግን አልፈለግነውም፤ ምክንያቱም ከባድ ግርግር እንደሚበዛበትና ለመኪናም አመቺ እንዳልሆነ ገብቶናል። ከዚህም በላይ የሻዕቢያዎች ትኩረት በዚያ በኩል እንደሚሆን ገምተናል፤ ስለዚህ በአጠቃላይ ለአደጋ የተጋለጠ ነው ብለን አስበናል። የመቀርካው - ጎንደር መንገዱ ደግሞ ዘላቂ አይደለም፤ የሆነ ቦታ ላይ ይቆማል። ስለዚህ ምርጫችን ወደ ትግራይ ነው፤ ምክንያቱም ሰው ላይበዛበት ይችላል። ከምናውቀው ሻዕቢያ የማናውቀው ወያኔ ይሻለናል በሚል ዋዝ ጂፕን ተጠቅጥቀን ለመብረር ወስነናል። # ከቀኑ 07፡00 ሰዓት ጉዞአችንን ከአስመራ ወደ ደቡብ አቅጣጫ በማድረግ ረዥምና ምን ሊገጥመን እንደሚችል ወደ ማናውቀው አስጊና አጠራጣሪ ጉዞ ከጀመርን ከስድስት ሰዓት በላይ ሆኖናል። መኪናው ላይ ተጠቅጥቀን በጎዳይፍ በኩል የመንደፈራን መንገድ ይዘን እየተጓዝን ነበር። ከተማውን ጥለን እስክንወጣ የሻዕቢያ ኃይል አልነበረም፤ የእኛ ሠራዊት ግን በእግርም በመኪናም ይጓዝ ነበር። ሻዕቢያዎቹ ሠራዊቱ ከአስመራ ከተማ እንዲወጣና በበረሃ ላይ ለማግኘት እንደወሰኑ ገባን። ከፊታችንም የተኩስ ድምፅ እየሰማን ስለነበር መኪናውን አቁመን በእግራችን መጓዝ አማራጭ እንደሌለው ስለተረዳን ወርደን የእግር ጉዞ ተቀላቀልን። የግንቦት ፀሐይ ግለትና የአካባቢው በረሃማነት፣ በአእምሮ ውስጥ ያለው ስጋት ተጨምሮ ሰውነታችን ድካም ቢሰማውም ተገቢውን እረፍት እየወሰድን ለከብቶቹ ሳር ፍለጋ እንደሚጓዝ ዘላን መንገዳችንን ቀጠልንበት። ሐሳባችን እንደ ምንም ትግራይ ክፍለ ሀገር መግባት ነው። ይህችን ማስታወሻ የምጽፈው ካረፍኩባት አንዲት ቁጥቋጦ ሥር ሆኜ ነው። እስቲ በማለዳ ከአስመራ ስንወጣ የነበረውን ሁኔታ ጥቂት ላስታውስ፤- ቀኑ ለሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት የከፋ ጨለማ ቢሆንም ጥርት ባለ ሰማይ ላይ በሞገስ የምትወጣውን የግንቦትን ፀሐይ ፍንትው ከማለት ግን አልከለከላትም። ለአንዱ መጥፎና የንዳድ ቀን፣ ለሌላው ደግሞ የእረፍትና የደስታ ቀን ነው። ይህች ዕለት ለአንዱ የድል ቀን፣ ለሌላው ደግሞ የሽንፈት ቀን መታሰቢያ ናት። በቃኘው ሦስተኛ በር በኩል በጥንቃቄ እያሽከረከርን ስንወጣ ከማለዳው አንድ ሰዓት ገደማ ነበር። የከተማው ሕዝብ በየአጥሩና በየበሩ ቆሞ ሁኔታዎችን በመገረምና በመደነቅ ይመለከታል። ግማሹ በደስታ ይሁን በሐዘን ባላውቅም የሚያለቅሱ ነበሩ፤ "አይዞአችሁ በሰላም ግቡ" የሚሉም ነበሩ። ባሉበት ሆነው ምራቅ የሚተፉና የሚሳደቡም ነበሩ። ሻዕቢያዎቹ ከተማ ውስጥ አንድ ጥይት እንኳ እንዲፈነዳ እንዳልፈለጉ በደንብ ያስታውቃል። እዚህ ከተማ ውስጥ ውጊያ ቢቀሰቀስ በመጨረሻ አላስፈላጊ ዋጋ ከመክፈልና ከተማዋን ከማውደም ውጪ ምንም ጥቅም እንደሌለው የተረዱ መሆናቸውንም ያሳያል፤ ምክንያቱም ለተቃውሞ የሚሆን አንድ ጥይት እንኳ አልተተኮሰም። በርግጥ የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት በተለያየ ምክንያት ይተኩሱ ነበር። በደቡብ አቅጣጫ በጎዳይፍ በኩል ስንወጣ ከርቀት አስመራ ከተማን እየተወ የሚወጣው ሠራዊት ቅጠልያውን ለብሶ ሲርመሰመስ ላየው ከዛፍ ላይ እየተመለመለ እና እየተራገፈ የተጣለ ቅጠል ይመስላል። ምርጫ ስለሌለን መኪናውን ባገኘንበት ትተን ከሠራዊቱ ጋር በእግር ተቀላቀለን፤ በዚህም አስቸጋሪ የሆነውን የኤርትራ ክፍለ ሀገር መልከዓ ምድር ጉዞ ያለምንም ፍላጎት በእግራችን ተያያዝነው። በግሩፕ መሆናችን በጣም ጠቅሞናል። እየተጫወትን ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ቤታችን እንደምንደርስ ያህል እየተሰማን ሐሳባችንን እንረሳለን። አስፈላጊ ሲሆንም ነጠል ብለን ሰብሰብ እያልን እንመካከራለን። በርግጥ በርካታ አሳዛኝ ሁኔታዎችን ተመልክተናል። ከሆስፒታል እንደምንም የወጡ ቁስለኞች፣ በሽተኞችና አቅመ ደካሞች በየበረሃው ወድቀው ሲያቃስቱና ሲጮሁ መስማትና በተስፋ መቁረጥ ራሳቸውን ሲገድሉ ማየት እየለመድነው እስከሄድን ድረስ የሚዘገንንና እጅግ ልብን የሚሰብር ነበር። በጉዞ ላይ በርካታ ክስተቶችም ነበሩ። ሠራዊቱ ከከተማው ሲወጣ በተበታተነ ሁኔታ የወጣ ቢሆንም በኋላ ላይ ግን ማን እንዳሰለፈው ሳይታወቅ እንደ ጉዳን ተደርድሮ ሲጓዝ ማየት አስገራሚ ነበር። ከፊት ማን እንደሚመራውና ጫፉ የት እንደደረሰ ባይታወቅም ብቻ እንደ ጎርፍ ወደ አንድ አቅጣጫ ይጎርፋል። በርካቶች በሞራልና በተስፋ ይጓዛሉ፤ መሣሪያቸውን በትከሻቸው ተሸክመው በዝምታ የሚጓዙ እንዳሉ ሁሉ እርስ በርዕስ እያወሩ ተፍተፍ የሚሉም ብዙ ናቸው። ጆሮአቸው ላይ ከአብዛኛው ወታደር ኪስ ውስጥ የማትጠፋውን ትንሽ ሬዲዮ ለጥፈው የሚሰሙም አሉ። የተሰደደው ሠራዊት ብዛት ይህ ነው ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፤ በጣም ብዙ ነው ይህ ያጓጓቸውና ከፊት ያለው ሁኔታ ያሰጋቸው አንዳንዶች ጦሩ ልብ ባይሰጣቸውም ሠራዊቱ እንዲቆምና በተደራጀ መልኩ እንዲጓዝ ከፍ ባለ ድምፅ ሲወተውቱ ይታያሉ.. የቀድሞው ብሔራዊ ወታደር #ደርግ #የኢትዮጵያታሪክ #creatorsearchinsights
የቀድሞው ብሔራዊ ወታደር
Region: ET
Sunday 26 July 2026 09:51:23 GMT
Music
Download
Comments
@Dessalegn M Tolesa :
ወንድሜ እናቴ እንደ ነገረችን አባቴ ሁአሰ ጥገና ክፍል ነበር ሙላቱ ቶለሳ ይባላል ሻእብያ አስመራ ስገባ እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ቃኘው ነበር ከዛ ሱዳን እንደ ገባ የሱ የስራ ባልደረቦች ለናቴ ነገሯት ሱዳን አይተነዎል ብለው ቢነግራትም ይሄው እስከ አሁን ድረስ ይሙት ይኑር ምናቀው የለም
2026-07-28 16:38:32
0
mulubirhan deribe :
ወንድሜ 19ኛ ተራራ የአባቴን ሁኔታ ማወቅ ብፈልግም ሚያውቅ አልተገኘም
2026-07-26 17:58:17
1
Dereje Ylima :
ክብር ለቀድሞ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያ ትቅደም
2026-07-26 10:04:50
5
Amare :
ከአስመራ ወደ ደቀመሀሪ 16 km ላይ ነበርኩ 18ኛ
2026-07-27 07:15:12
0
Endo hase :
በዕለቱ አስመራ ትራክብ ሠፈር ነበርኩ የማይረሳ የሞራል ውድቀት የተሰማኝ ዕለት 16 ሠንጥቅ ብርጌድ
2026-07-26 23:10:15
1
user9476906191728 :
ደቀማራ ነበርኩ
2026-07-28 18:16:08
0
pinolope GGUM :
ወይኔ ትዛታ
2026-07-28 17:48:15
0
Tilahun Zegeye :
2026-07-28 06:03:59
0
Bekele :
ይሕን ገጽ ሳይ የሚሰማኝን ትዝታዎች እነ የነበረው የአገር ፍቅር ስሜት በውስጤ እንደእሳት ይነዳል /የእድሜ መነጎድ የአገር ሰላም ጉዳይ መች ታርፍ ይሆን አገሬ ?ፈጣሪ ጣልቃ ይግባልን !
2026-07-28 11:10:45
0
nesro :
607ኛ ኮር ቀሪ ክፍል ከ12ኛ በርጌድ ቀሪ ክፍል ግንቦት 16ቀን1983ዓ ም ለሊት ተነሰተን ጉዞ ወደ ከረን ተንቀሳቅሰን ግንቦት 20ቀን1983ዓ ምተሠኔን አቋርጠን ላፋ ገባን
2026-07-28 06:42:42
0
Assefa Degefa :
ኢትዮጵያ ትቅደም 🙏🙏🙏🙏
2026-07-27 09:15:34
0
Wendiye Ethio :
በጣም አሳዛኝ ነው እንባዬ ነው የፈሰሰው የወታደር ሂይዋት
2026-07-28 03:56:19
0
nahoowa :
"አይዞአችሁ በሰላም ግቡ" የሚሉም ነበሩ✌️
2026-07-26 23:03:31
0
Solomon :
yemigerm tezeta des bemil sefe yetzegage yebarkhe
2026-07-27 18:14:17
0
get8982 :
በቀን 16 ጠዋት በሁአሰ ሬዲዩ ጣቢያ የተላለፈ መልእክት ነበር እኔ በቀኑ መራራ ላይ ኦፒ ነበርኩኝ የቅኝት ስራችንን አቁመን ነበር የሰማነው ከፍቼ መራራ ላይ ሁነን ነገሩን ስንከታተል ከኮር ማዘዣ ጣቢያ አንድ መልእክት ደረሰኝ ወደ ሆላ እንድመለስ ግን ነገሩን አላመንኩበትም ነበር ዉረድ የሚለውን ትእዛዝ ሳልቀበል ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ ነበር ግን ያን ቀን ዋ
2026-07-26 18:35:40
1
Tilahun Zegeye :
እንዲህ ነበርኩ
2026-07-28 06:04:16
0
Tilahun Zegeye :
19 ነኛ ተራራ ክ/ "ጦ ነበርኩ
2026-07-28 06:01:32
0
Bekele :
አይ ትዝታ!ከወሎ አስከ አርሲ የግር ጉዞ 9አንድ ጓድ ይዞ ! ተመስገን አምላኬ ብዙ ጓዶቼ ን ባጣም አንተ ከኔ ጋር ነህ!!!
2026-07-26 13:14:07
1
fekede moges :
የምታውቁት 18ኛ ተራራ37ኛ ብርጌድ 372ኛ ሻለቃ
2026-07-27 17:56:43
0
Tilahun Zegeye :
ደቀመሀሪ ኢላ በረድ
2026-07-28 06:00:28
0
Eyasu Ejigu :
16ኛ ክ/ጦር ነበር ወንድሜ በፍት አየር ወለድ ነበር አሉ እስከ ዛሬ ድምፁ የለም ይሙት ይኑር አናዉቀዉም
2026-07-27 16:10:51
1
Chernet Wakjira :
😳😳😳
2026-07-27 05:50:26
0
Yared Berhanu :
🙏🙏🙏
2026-07-27 11:19:30
0
Abu Emran :
🙏
2026-07-28 18:35:56
0
To see more videos from user @sewadam0, please go to the Tikwm
homepage.