@musictube369: አንድ ኢትዮጵያ 😇 ✍️ከሙዚቃ መሳሪያዎች ክራርን፤ ማሲንቆን፤ ጊታርና ኪቦርድ ትጫወታለች፡፡ ክራርና ማሲንቆ የተማረችው ኢትዮጵያ እያለች ከሙዚቃ መምህሩ ከአለማየሁ ፋንታ ዘንድ ነው፡፡ አለማየሁ ፋንታ ጋር ያገናኟት ደግሞ የሙዚቃ ፍቅሯ ሀያል መሆኑን የተገነዘቡት አባቷ ናቸው፡፡ አባቷ በመጀመሪያ ድምፃዊ እንዳትሆን በንስሐ አባት ሁሉ አስመክረዋት ነበር፡፡ አሻፈረኝ ማለቷን በማየት ነው የጉዞዋን መንገድ ማቅናት የጀመሩት፡፡ ለሷ የሙዚቃ ስብዕና መሟላት ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ካደረጉላት ሰዎች መካከል አንዷ እናቷ ናቸው፡፡ በቤት ውስጥ የሚያነቡላት ግጥም እና ልዩ ልዩ የሥነ-ፅሁፍ ስራዎች የዛሬዋ ጂጂ እንድትፈጠር ማድረጉን ራሷ ትናገራለች፡፡ እናቷ ከዓመታት በፊት የፃፉትን የራሳቸውን ረጅም ልቦለድ አሳትመዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው የጥበብ ተሰጥኦው ከእናቷ ዘንድ መሆኑንም ጭምር ነው፡፡ ታዲያ ስለሙዚቃ ስትጠየቅ "ሙዚቃ ለሕዝብ የምሰጠው ውዱ ስጦታዬ ነው። ለምትወጂው ሕዝብ ደግሞ የማትወጂውን ነገር አትሰጪውም" ትላላች የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን የዚህ አንድ ኢትዮጵያ አልበም ባለቤት እንቁዋ ኮከብ ባለቅኔዋ ተወዳጇ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የተወለደችው ቻግኒ ጐጃም ውስጥ ነው፡፡ አባቷ እናቷን ከአዲስ አበባ ጠልፈውና በፍቅርም ጭምር ወደ ቻግኒ ሄዱ፡፡ እዚያም ገጠር ውስጥ ገብተው በእርሻ እና በንግድ መተዳደር ጀመሩ፡፡ የእጅጋየሁም የሙዚቃ እና የስነ-ፅሁፍ ንቃት የጀመረው በዚሁ አካባቢ ነው፡፡ እናቷ መፃህፍት ለልጆቻቸው ያነቡላቸዋል፡፡ ይሄ የነ እጅጋየሁን የጥበብ ተፈጥሮ ይበልጥ ጐልቶ እንዲወጣ አድርጐታል፡፡ እህቶቿም ድምፃዊያት ናቸው፡፡ ከዚህ ሌላ የሚኖሩበት አካባቢ የቤተ-ክህነት ሊቃንት የተሰባሰቡበት ደብሮች አካባቢ ስለሆነ ልዩ ልዩ መንፈሳዊና ባህላዊ ዜማዎችንም በአእምሮዋ ስታዳብር አድጋለች፡፡ እቤታቸው ውስጥ ወደ ስምንት እህቶች እና ሁለት ወንድሞችም አሏት፡፡ ቤተሰቧ ትልቅ ቤተሰብ ነው፡፡ እዚህ ቤተሰብ ውስጥ እርስ በርሱ እንዲዝናና እነ ጂጂ ይዘፍኑለታል፤ ቴአትር ይሰሩለታል፡፡ በዚህም ሳቢያ የጂጂ የጥበብ ተሰጥኦ እየዳበረ መጣ፡፡ ከዚህ በኋላ የሙዚቃ ፍቅሯ እየገዘፈ ሄደ፡፡ ሙዚቃን እስከ ጥግ ድረስ የምታውቅበትና በነፃነት የምትዘፍንበትን መንገድ ሁሉ ትፈልግ ጀመር፡፡ ቤተሰቦቿ በባህር ዳር ከተማም ጥሩ መተዳደሪያ እና ኑሮ ቢኖራቸውም እሷ ሙዚቃን ፍለጋ ትዞር ጀመር፡፡ አዲስ አበባ መጣች፡፡ ሴንት ሜሪ የሴቶች ት/ቤት ገባች፡፡ ግን ትምህርቷን እያቋረጠች ሙዚቃን ማሠስ ጀመረች፡፡ በየቦታው መዝፈን ጀመረች፡፡ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስም አማካኝነት ወደ ውጭ ሀገር እየተዘዋወረች ሙዚቃዎች አቀረበች፡፡ በብርሃነ መዋ ፊልም ላይም በትወና ተሳተፈች፡፡ እውነተኛዋን ጂጂ ልታገኝ ግን አልቻለችም፡፡ ሙዚቀኛዋ ጂጂ ጠፋች፡፡ ኬንያ ሄደች፡፡ እዚያም ጂጂን ለማግኘት የሙዚቃ ባንድ አቋቋመች፡፡ አሁንም ጂጂ አልተገኘችም፡፡ ኬንያን ጥላ ወደ አሜሪካ ሄደች፡፡ የጂጂ መስመር የተሳካ ሆነ፡፡ የሙዚቃ ሊቆች ደብር ውስጥ ገባች፡፡ ባለቤቷንም ያገኘችው በምድረ አሜሪካ ነው፡፡ የድምፅ ኢንጅነር ነው፡፡ ከአንድ ሺ ያላነሱ የተለያዩ ድምፃዊያንን ሙዚቃዎች ሰርቷል፡፡ ከዚህ ሰው ጋር የመሰረተችው ጥምረት የዛሬዋን ስመ ገናና ጂጂን እንዳስገኘ ራሷ ጂጂ አዲስ አበባ የመጣች ሰሞን ነግራን ነበር፡፡ ጂጂ ዘንድ ያለው የስነ-ግጥም፤ የድምፅ፤ የዜማ እና የታሪክ እውቀት ከባለቤቷ የሙዚቃ ቅንብር ሊቅነት ጋር ተዋህደው የኢትዮጵያን የሙዚቃ ስልት ሀገርኛ ለዛና ውበት ሰጡት፡፡ የኢትዮጵያንም ስም በትልልቅ ቦታዎች ማስጠራት ጀመሩ፡፡ ታዲያ እውነተኛዋ ጂጂ ከተገኘች በኋላ እስከ አሁን ድረስ ወደ ስድስት አልበሞች ታትመዋል፡፡ በሁሉም ስራዎቿ የተዋጣላቸው ሙዚቃዎች እንደሆኑ በሰፊው ይወሳል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሥነ-ፅሁፍ ሰዎች የጂጂን የዘፈን ግጥሞች በተደጋጋሚ ሲመዝኗቸው ቆይተዋል፡፡ ኢትዮጵያዊ ለዛ እና ስሜት በስፋት የሚንፀባረቁባቸው እንደሆኑ ያወሳሉ፡፡ ለምሳሌ “ካህኔ” በሚለው ዘፈኗ የኢትዮጵያን ቤተ-ክርስትያን “ጉባኤ ቃና” የሚመስል ስልት ይዞ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡ 📌በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ፅሁፍና የፎክሎር መምህር የሆኑት ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ በአጋጣሚ የጂጂን ካሴት ማታ ሰምተውት ነበር፡፡ ጠዋት ሊያስተምሩ ወደ ተማሪዎቻቸው ዘንድ መጡ፡፡ እንዲህም አሉ፡- “ዛሬ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነው ያደርኩት” ተማሪዎቻቸውም “ምነው? ምን ሆንክ?” አሏቸው፡፡ እርሳቸውም “ፍቅር እየራበኝ” እያለች የምትዘፍን ልጅ እጅግ እየደነቀችኝ ደጋግሜ ስሰማት ነው ያደርኩት” አሉ፡፡ ልጅቷን ግን ያወቃት የለም፡፡ እሳቸውም ስሟ እጅጋየሁ ነው፤ የሚያውቃት አለ ከናንተ ውስጥ? አሉ፡፡ የሚያውቃት ጠፋ፡፡ እርሳቸውም ሲናገሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ26 ዓመት በኋላ በሙዚቃ ስልቷ ነፍሴን የገዛችው ይህች ድምፃዊት ናት፡፡ በእኔ ግምት የኢትዮጵያን ሙዚቃ ትልቅ ደረጃ ታደርሰዋለች ብዬ የምተማመነው በዚህች ልጅ ነው፡፡ ጉድ ነው ዘፈኗ.. እያሉ በስሜት ሲናገሩ ሰምቻቸው ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው ዶ/ር ፈቃደ፤ ተስፋ የጣሉባት ጂጂ ሙሉ በሙሉ እንደተገመተችው የኢትዮጵያን ሙዚቃ በተለየ መንገድ ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳደረሰችው በልዩ ልዩ መድርኮች ተመስክሯል፡፡ በ1995 ዓ.ም ደግሞ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ አድዋ የሚሰኘውን ፊልማቸውን ለማሳየት ወደ አዲስ አበባ መጥተው ነበር፡፡ ቃለ-መጠይቅ ላደርግላቸው በወቅቱ ባልደረቦቼ ከነበሩት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አያሌው እና ከአብይ ደምለው ጋር ሆነን ከኃይሌ ገሪማ ጋር ውይይት አደረግን፡፡ ኃይሌ ገሪማ በጨዋታቸው መሐል እንዲህ አሉ፡፡ “አሁን ባለው ትውልድ ውስጥ አንድ ነበልባል ትውልድ ብቅ ብሏል፡፡ እነዚህም እጅጋየሁ ሽባባው እና ቴዲ አፍሮ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ባልተጠበቀ ፍጥነት እያመጠቁት ነው፡፡ እድሜ ሰጥቶኝ የነርሱን ተደጋጋሚ ስራዎች ማየት እፈልጋለሁ” አሉን፡፡ በጂጂን ከሎሬቱ ፀጋዬ ገ/መድህን ጋር እያነፃፀሩ ማቅረብ ተዘውትሮ ነበር፡፡ ጂጂ የፀጋዬ ተፅእኖ ያደረባት ድምፃዊት ናት ተብላለች፡፡ ለምሳሌ ፀጋዬ ዓድዋ ላይ የፃፈው ሥነ-ግጥሙ ሌላው ተጠቃሽ ስራው ነው፡፡ እጅጋየሁ ሽባባውም ዓድዋ ላይ የዘፈነችው ዘፈን እንደ ፀጋዬ ዓይነት እጅግ ጥልቅ ስሜትን የሚያስተጋባ ሥራ እንደሆነ ተመስክሮላቸዋል፡፡ ፀጋዬ በኢትዮጵያ ፍቅር ላይ የወደቀ ገጣሚ ነው በሚል ኢትዮጵያዊነት የተላበሱ ሥነ-ግጥሞቹ ተዘርዝረዋል፡፡ እጅጋየሁ ሽባባውም እንዲሁ ኢትዮጵያዊነት” በሰፊው የምታስተጋባ ድምፃዊት እንደሆነች ባለፉት ጊዜት በልዩ ልዩ መድረኮችና ጥናቶች ቀርቧል፡፡ ጂጂም ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገችው ቃለ-ምልልስ የሥነ-ግጥም አድናቂ መሆኗን እና እነ ፀጋዬ ገ/መድህንን በስራዎቻቸው እጅግ እንደምትወዳቸው ገልፃለች፡፡ 📌ጂጂ አንቺ ሰዎች መልክሽን አይተው ብቻ ሊመዝኑሽ እንዳይችሉ እጅጉን የረቀቀ ዜማ ሰርተሽ ጠበቃ አቁመሻል። ዛሬም ድረስ እንደ ጥንቱ ለሁላችን ውብና ተናፋቂ ነሽ። ባለሽበት የእግዚአብሔር ጥበቃ አይለይሽ። እንወድሻለን!!!🤗 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #ጂጂ #fyp #አንድኢትዮጵያ #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 26 July 2026 19:45:06 GMT
11063
926
28
49

Music

Download

Comments

abcd764211
Teddy Afro :
Thank you 🙏
2026-07-28 19:39:27
1
surafelog
Surafel Getu :
golden voice
2026-07-28 22:07:13
0
abrhm84
abrham lg :
yemayeteka sew best album
2026-07-28 17:26:44
1
olitisirabizuj
Oliti :
Thank you but should have mentioned Dereje mekonnen
2026-07-27 12:05:53
2
hirapiko24
✨piko👑 astu🎸 :
እንኳን ዘፈኗን ጩኸቷንም አደንቃለሁ ምክንያቱም ብትጮህ እንኳን የለምክንያት ስለማትጮህ🥰
2026-07-27 14:25:40
3
mitshye
Jerusalem :
The Queen 🥰
2026-07-27 19:18:36
1
habibemam619
habibemam619 :
አመሰግናለሁ በጣም
2026-07-26 22:08:44
2
habte7016
habte ♎ :
2026-07-26 19:51:27
2
user6121959700041
ኢትዮጲያ ትቅደም :
ጃጂያችን
2026-07-27 12:01:08
2
user4154295034472
ታደሠ :
ጥንቅቅ አድርገህ ሙዚቃን ስለምታውቅ በጣም ታስደንቀኛለህ
2026-07-26 19:56:38
3
wenda2258
wenda :
💚💛❤️💚💛❤️🎹🥁🎷🎺🎤
2026-07-27 03:50:04
1
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-27 11:25:22
1
ruthesilase7
ሩት :
❤️❤️❤️
2026-07-27 07:56:13
1
zuzu..kingo.user23
Abdi Abrar ka Hirna or dire da :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-26 19:47:46
1
ermiyas_t
Ermiyas_t :
🥰👍🙏
2026-07-26 20:13:35
1
habetugirmay
Habetu Girmay :
👏👏👏👏👏👏💯💯💯💯💯
2026-07-28 19:30:38
1
user9305811716361
burte@ :
🥰👌
2026-07-27 11:17:19
1
user6634103576306
tade :
🥰🥰🥰
2026-07-27 18:16:36
1
mekasha277
@mekasha.27 :
❤️❤️
2026-07-28 17:47:20
1
surafelog
Surafel Getu :
🥰
2026-07-28 22:06:31
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About