@official9235: ለፍቅር......... ፀሀይዋ በከተማዋ ላይ ቂም የቋጠረች ይመስል ገና 3 ሰዓት ሳይሆን ሙቀቷን ትረጫለች ። ሰለሞን ግን የፀሀይዋን ሙቀት ከምንም ሳይቆጥር በሰው መሀል እየተሹለከለከ ወደፊት ያመራል ሲያዩት ቀጠሮ ያለበት ነበር የሚመስል ቢጠሩትም አይሰማም ። በጣም ከመቸኮሉ የተነሳ ወደ ኋላው እንኳን ዞሮ አያይም ። ቀጥ ብሎ ነበር የሚሄድ መናሀሪያውን ካለፈ በኋላ ወደ አደባባዩ የሚወስደውን መንገድ ተያያዘው ። የለበሰው አሮጌ ጅንስ ሱሪ ከማለቁ የተነሳ ተቀዳዷል ከላይ የለበሳት ቢጫ ቲሸርት በጣም ከመቆሸሿ የተነሳ ውሃ ነክቷት የሚያውቅ አይመስልም ። የፀጉሩ ነገርማ አይነገርም በጣም ከመንጨፍረሩ የተነሳ የጃርት እሾህ መስሎ ቆሟል ። አደባባዩ ከደረሰ በኋላ ወደ ቀኝ ታጠፈና ወደ ገበያው ገባ ። የህዝቡ ብዛትና ጫጫታ ግራ ያጋባው ሰለሞን መሀል ላይ ቆሞ ከወዲያ ወዲህ ቢያማትር ተሸካሚ ( ወዛደር ) የሚፈልግ ሰው በአይኑ ቢያስስ አጣ ። “ በቃ ዛሬም ሳልሰራ ልውል ነው ? " አለ በውስጡ ። ትንሽ ከጠበቀ በኋላ ወደ ጤፍ መሸጫው መካዘን አመራ እዛም ወዛደር የሚፈልግ ሰው አጣ ። አንድ ከተዘጋ ሱቅ ገደፍ ብሎ እንደቆመ በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄደ ። ከእጅ ወደ አፍ የሆነው ኑሮው ይበልጥ ያስጨንቀው ጀመር ። ሰው ሁሉ በሰው ከማሸከም ይልቅ ለፍጥነቱ እያለ በእሽኩኒታ ማስጫኑ የወዛደሮች ኑሮ ወደፊት ምን ሊመስል እንደሚችል እያሰበ እያለ ነበር ድንገት “ የኔ ልጅ " የሚል ድምፅ ብዙ ርቀት ከሄደበት ሀሳቡ ያነቃው ። ገና ከእንቅልፉ እንደነቃ ሰው አይኑን እያጨላሞሰ ድምፁን ወደሰማበት አቅጣጫ ሲዞር ከአንድ እናት ጋር አይን ለአይን ተጋጩ ። ትሸከማለህ ? አለችው በማዳበሪያ የሞላውን ጤፍ በአገጯ እየጠቆመች ። አዎ...ብሎ ጣድፎ ስለ ክፍያ ሳይነጋገሩ ተወተርትሮ አንስቶ ተሸከመው ። በክፍያ አለመስማማት ይመጣል ብሎ ስላሰበ ነበር ስለ ክፍያ ሳይጠይቅ ለመሸከም የተገደደው ። ሰሞኑን ሳይሰራ በመሰንበቱ ነበር የሰጠችውን ክፍያ ለመቀበል የወሰነው ። የህዝቡን ጋጋቴ ቀስ እያለ ካለፈ በኋላ ። ከፊት ሆና ሴትዮዋ በምትመራው ወደ ዋናው ንግድ ባንክ ከሄዱ በኋላ እንደገና ወደ ስታዲየሙ በሚወስደው መንገድ ጉዞውን ጀመረ ። ሴትዮዋን ከዚህ በፊት አይቷት የማያውቅ ቢሆንም ከተማው ውስጥ በደግነት አንቱታን ያተረፉ የቤት እመቤት ናቸው ። ወ/ሮ ሙሉነሽ ይባላሉ ። ከጨፍራራ ፀጉሩ የሚፈሰው ላበት ፊቱን አልብሶ ወደ አንገቱ መፍሰስ ጀምሯል ። ከፀጉሩ ላይ ላበት እያጠበ የሚያመጣው እድፍ አይኑን ስለሚቆጠቁጠው ቆም ይልና ፡ በአንድ እጁ ዣዱ ላይ የተሸከመውን ጤፍ እንዳይወድቅበት ይይዝና በሌላኛው እጁ ደግሞ ሁለቱንም አይኑን ጠራርጎ ፡ እንደ ወጣት በፍጥነት የሚጓዙትን ወ/ሮ ሙሉነሽን በፍጥነት ጉልበቱ ከጉልበቱ እየተጋጨ እና እየተወላገደ አሊያም በማቸልቸል ይደርስባቸዋል ። ቀጥ ያለውን የስታዲየሙን መንገድ ጨርሰው የመጨረሻ መታጠፊያ ሲቀር ወ/ሮ ሙሉነሽ ቆመዉ ጠበቁትና " አይዞህ የኔ ልጅ ደርሰናል " አሉትና ወደ መታጠፊያው ገቡ ። ልምድ ሆኖባቸው ወጣቱን በሙሉ " የኔ ልጅ " ማለት ይቀናቸዋል ። ትንሽ ከተጓዙ በኋላ ሰፊ በር ያለውን ግቢ ሲያንኳኩ ጥበቃቸው እየተጣደፈ በሩን ከፈተላቸው ። ሰለሞን ጤፉን በረንዳው ላይ ካወረደ በኋላ " ደከመህ የኔ ልጅ ? አልደከመኝም.... አላቸው ቁና ቁና እየተነፈሰ ። በዚህ ሰዓት ወ/ሮ ሙሉነሽ ወደ ውስጥ ገቡ ። ሰለሞን ቁጭ እንዳለ አጥር ግቢውን ይቃኝ ጀመር ።.... ይቀጥላል.... ክፍል 2 ቶሎ እንዲደርሳችሁ like👍🏼 ዮናስ ✍️
ነይ ልቀፍሽ ከኔ እደሪ..📚
Region: ET
Sunday 26 July 2026 19:54:40 GMT
Music
Download
Comments
Ñâfእናቴ :
please ketay🙏🙏🙏
2026-07-29 12:10:25
2
Merga Daba :
gin algebangm
2026-07-30 12:35:23
1
ሠው ለሠው :
የሚገርም ፎቶ
2026-07-30 13:31:52
1
abitti_sigma03 :
አረ በማርያም ቀጣይ🙏
2026-07-30 07:44:45
2
D&A :
part 3
2026-07-29 18:27:38
2
Tmy D :
33333
2026-07-30 10:49:36
1
CR7 :
አረ ወይኔ ቀጣይ
2026-07-29 15:12:09
1
ወልዴ ብሩ (282828) :
ቀጣይ
2026-07-29 04:49:33
1
𝔀𝓮𝓻𝓴𝓾 𝔀𝓮𝓻𝓴𝓾 :
22222
2026-07-28 19:16:28
1
አብዲሻ አዛኙ :
እንደዚህ አይነት ፍቅር ውሸት ይመስለኝ ነበር።
ግን በኔ ደርሶ አየሁት እውነት ነው ፍቅር አለ ያውም እድሜ ተቀንሶ ቢሰጥ ኖሮ ከእድሜህ ላይ የምትሰጥለት ፍቅርማ አለ!!
2026-07-29 22:52:23
2
haymie :
2222
2026-07-27 18:00:10
1
Newi Newi :
ይሄ የእዉነተኛ አፍቃሪ ታሪክ ነዉ
2026-07-27 12:36:55
2
ፍቅሬናት ህይወቴ :
ቀጣይ
2026-07-29 17:38:12
1
WORKISHA💊 :
er cheresulin
2026-07-27 05:59:58
1
Gech_VIP :
part 3 🙏
2026-07-29 09:19:34
1
𝑎𝑠ℎ𝑢 𝑢𝑚𝑚𝑖 𝑘𝑖𝑛𝑔𝑜 :
2
2026-07-27 05:49:48
1
Yusuf Yuzersif :
22
2026-07-28 06:10:54
1
D&A :
ቀጣይ 🙏🙏
2026-07-28 04:00:36
1
football :
በማርያም አንጠለጠላቹኝ
2026-07-27 11:03:57
1
♥♥♥ነዉ :
🥰🥰🥰
2026-07-29 15:29:01
1
tedaaaa :
🥰🥰🥰
2026-07-29 12:20:44
1
Benyam Temesgen :
👌👌👌
2026-07-27 09:44:38
1
Aarif[H🫀] :
🥰🥰🥰
2026-07-30 13:20:31
1
ilyas abdi :
🥰
2026-07-30 08:43:32
0
blackpoint52 :
😳😳😳
2026-07-30 08:53:01
1
To see more videos from user @official9235, please go to the Tikwm
homepage.