@kealemgallery0: "ሌሎች የሸሹትን ሰው እሷ በፈገግታ አገለገለችው… ከሞተ በኋላ ግን ያልጠበቀችው ሽልማት ጠበቃት!"❤🔥🔥🔥🔥 ሜሊና ሳላዛር ትባላላች...በአሜሪካ በቴክሳስ ግዛት ብራውንስቪል በሚገኘው ሉቢስበሚባል ካፌቴሪያ ውስጥ ለ7 ዓመታት ያህል አስተናጋጅ ሆና ሠርታለች። በነዚያ የሥራ ዘመኗ ውስጥ በየቀኑ የሚመጣ አንድ ደንበኛ ነበር፤ 89 ዓመቱ ነው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተሳታፊ ዋልተር "ባክ" ስዎርድስ ይባላል። ባክ በምንም ነገር በቀላሉ የማይደሰት በቀላሉ ተናዳጅ አምባገነነሰ ከንግግሩ ቁጣ የሚቀድመው ሰው ነበር ። ምግቡ እጅግ ሞቃት ካልሆነ አይቀበልም፤ አንዳንድ ጊዜ እስኪቃጠል/ እስኪያር ድረስ ምግብ እሳት ውስጥ እንዲቆይ ይፈልግ ነበር። ፈገግታ በፊቱ ላይ አይታይም፣ ብዙ ጊዜም በቁጣ የተሞላ ፊት አለው። ከምግብ በኋላም ቲፕ ማስቀመጥ ፈጽሞ አይወድም ነበር። በዚህ ምክንያት አብዛኞቹ ሰራተኞች እሱን ለማገልገል/ማስተናገድ ይሸሹ ነበር። ነገር ግን ሜሊና የተለየች ነበር። የባክ ...ባህሪ ፈጽሞ አልቀየራትም። ሁልጊዜ በትዕግሥት፣ በአክብሮት እና በፈገግታ ታስተናግደው ነበር። ወደ ሬስቶራንቱ በመጣ ቁጥር በሙሉ ልብ ሰላም ትለው ነበር። የእሱ ንዴት የእሷን ሰብእና አልለወጠውም። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 2007 ዓ.ም. በሐምሌ ወር ባክ አረፈ። ሜሊና ይህን የሰማችው በጋዜጣ ላይ የወጣውን የህልፈቱን ማስታወቂያ ካነበበች በኋላ ነበር። ዜናው አሳዘናት፤ ነገር ግን ባክ ለእሷ የመጨረሻ ስጦታ እንዳዘጋጀ አላወቀችም። ከገና በፊት ባሉት ጥቂት ቀናት ያልጠበቀችው ዜና ደረሳት። ባክ በኑዛዜው ውስጥ 200,000 ሺህ ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና የ2000 ሞዴል ቅንጡ Buick መኪናውን ለሜሊና ትቶላት ሞተ። ከዚህ በላይ ግን የተተወላት ነገር ገንዘቡ አልነበረም… የዓመታት ትዕግሥቷ፣ የሰጠችው ክብር እና ያሳየችው ሰብአዊነት በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንደነበራቸው የሚያሳይ መልእክት ነበር።❤❤❤ ባክ በሕይወቱ ሳለ ምስጋናውን በቃላት መግለጽ አልቻለም። ግን ከሞቱ በኋላ የተወው ስጦታ አንድ ነገር በግልጽ አስረዳ… "የሰጠችኝን ክብር እና ደግነት ፈጽሞ አልረሳሁትም።"የሚል ይህን ስትሰማ ሜሊና በእጅጉ ተደነቀች። "እስካሁን ድረስ ማመን አልቻልኩም።" ስትልም ስሜቷን ገለጸች። አንዳንድ ሰዎች ምስጋናቸውን በቃላት አይገልጹም። አንዳንዶቹ ፈገግታቸውንም አያሳዩም። ግን ይህ የሰጠኸው ክብርና ደግነት በልባቸው ውስጥ ቦታ እንዳልያዘ አያሳይም። ደግነት ወዲያውኑ ሽልማት ላያመጣ ይችላል፤ ግን መቼም ከንቱ አይሆንም። አንድ ቀን፣ በማትጠብቀው መንገድ ወደ አንተ ተመልሶ ይመጣል።❤❤❤❤ 🔥 ባሲ አስገራሚ እውነታዎች 🔥 እስካሁን ያልሰማችሁትን ዓለም እናሰማችኋለን 👀✨ 💡 ያልተነገሩ ታሪኮች 💡 አስደናቂ ክስተቶች 💡 ልብን የሚነኩ እውነታዎች ሁሉም በአንድ ቦታ 🔥 👉 አሁኑኑ ፎሎ ያድርጉ 👉 ሼር ማድረግ አይርሱ 🔥🔥🔥🔥 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ethiopian_tik_tok #habeshatiktok #viral #foryou

ከ ዓለም GALLERY  🌍🌎🌏
ከ ዓለም GALLERY 🌍🌎🌏
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 28 July 2026 19:13:30 GMT
35494
926
16
22

Music

Download

Comments

humasssssssssccfa
Q SIR :
መልካምነት ከኢትዮጵያ ውጭ ዋጋ እንዳለው ተረድቻለሁ
2026-07-29 07:17:24
15
amentools
Amen Tools አሜን ቱልስ :
👏👏
2026-07-29 07:04:49
2
gedionnebyat
gedionnebyat :
የሜገርም ታሪክ ነው
2026-07-29 09:28:35
1
sis6136
ልቤ በእግዚአብሔር ፀና!!!! :
በማይቻሉ ነገሮች ሁሉን ችለን ካሳለፍን መልካምነታችን ነገ በበጎ ይከፍለናል።
2026-07-29 05:43:28
1
demzeger
Sultan :
dess yelal
2026-07-29 00:58:42
0
shafiylir
shafi lire :
እሷስ ኣግብተለች ?- - - - -
2026-07-29 07:48:03
0
user7607939178153
yabisira silesh :
መልካምነት ይከፍላል
2026-07-28 21:13:46
0
kb4726
user5094579475230 :
ጥሩ ስራ ለክፉ ቀን ስንቅ ናት
2026-07-29 08:58:28
0
tabor.kumelcha
TT :
🥰🥰🥰
2026-07-29 08:54:56
0
sami.6102
Sami :
🥰🥰🥰
2026-07-29 08:53:24
0
zewdu.solomon
Zewdu Solomon :
👍
2026-07-29 08:02:38
0
hadm.seri
Hadm Seri :
🤟🤟🤟
2026-07-29 04:21:18
0
dawit.daniel1
Deva ✞ :
🥰🥰🥰
2026-07-28 19:22:06
0
nerenesib0
nuruhusen nesib 123 :
🥰🥰
2026-07-29 11:24:58
0
To see more videos from user @kealemgallery0, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About