@alemgeleta: የተዋህዶ ልጆችን እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🌺✝️🌺✝️🌺✝️🌺✝️🌺✝️🌺 ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማለት ምን ማለት ነው? ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማን ነው? ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኃገሩ የት ነው? ✝️🕊✝️🕊✝️🕊✝️🕊 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ውድና የተወደዳችሁ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጆች እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሀዊ መታሰብያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን ✝️🤲✝️🤲✝️🤲✝️🥰✝️🤲✝️🤲✝️🤲 ጊዮርጊስ ማለት:-ኮከብ፣ ብሩህ፣ ፀሐይ ማለት ነው። ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ኃገሩ "ፍልስጤም ልዩ ስሟ ል" ሲሆን የተወለደወድ በ277 ዓ.ም ጥር 20 ቀን። አባቱ ዞሮንቶስ ወይም አንስጣስዮስ የልዳ መኳንንት ሆኖ ተሹሞ ይኖር ነበር፤ እናቱ ቴዎብስታ ወይም አቅሌስያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሌላ ማርታና እሰይ የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች። ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐስር ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ ሰለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ አሳደገው። መስፍኑም በጦር ኃይል አሰለጠነው። 20 ዓመትም በሞላው ጊዜ መስፍኑ የ15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወረወሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ጌታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ። ቅዱስ ጊዮርጊስም ኃዘኑን ኀዘኑን ጨርሰው ወደ ቤሩት ሀገር ሄደ። በቤሩት ✝️🌻✝️🌻✝️🌻✝️🌻✝️🌻✝️🌻✝️🌻✝️ ድራጎንን ያመልኩና ሴት ልጆቻቸውን ይገብሩለት ሰለነበር ሰማዕቱ ድራጎኑን በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል። ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግሥቱ ገብቶ በካሃዲያኑ ሰባው ነገሥታት ፊት ክርስቲያን መሆኑን በሆኑን በመመስከር የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ምስክር መሰከረ። ዱድያኖስም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ "አንተማ የእኛ ነህ በዐሥር አህገር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ" አለው። ቅዱስ ጊዮርጊስም "ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬን ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም" አለው። በዚህ ጊዜ ዱድያኖስ እጅግ ተናዶ ብዙ አሰቃቂ መከራዎችን አደረሰበት። ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ግታችንን "ይህን ካሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት" በማለት መከራውን ይታገስ ዘንድ ለመነው። እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰምቶ ፍቃዱን እየፈጸመለት ብዙ በመከራው ሁሉ ጽናትን ሰጥቶታል። 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ሦስት ጊዜም ከሞት አስነሥቶታል ቅዱስ ጊዮርጊስም ያደረሱበት እጅግ አሰቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው በመጀመሪያም ዱድያኖስ በእንጨት ላይ ካሰቀለው በኋላ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው። ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል። ዳግመኛም በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ እናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ ሥጋውንም በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነሰነሰበት ሥጋወንም ተቆራርጦ መሬት ላይ ወደቀ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ከፈወሰውና "ገና ስደስት ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣3 ጊዜ ትሞታለህ በ4ተኛውም ታርፋለህ" ካለው በኋላ በመከራውም ሁሉ እርሱ እንደማይለው ነገረው። ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከዚያ ካደረሰበት አሳቃቂ መከራ ሁሉ ድኖ ፍጹም ጤነኛ መሆኑን በተመለከተ ጊዜ እጅግ ደንግጦ "የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ብዙ ✝️🌺🌺✝️🌺✝️🌺✝️🌺✝️🌺✝️🌺✝️ እሰጠዋለሁ" ብሎ ተናገረ አጥናስዎስ የተባለ መሰርይ(ጠንቋይ) አንዲትን ላም በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ስትሞት ለንጉሡም አሳየው ቅዱስ ጊዮርጊስን እንደሚያሸንፍ ምልክት አሳየ ንጉሡም ያሸንፍልኛል ብሎ ደስ አለው። መሰርይውም ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞበት እንዲጠጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል በዚህም ጊዜ ጠንቋዩ ማረኝ ብሎ ከእግሩ ሥር ወደቀ። 🌺🌺🌺🌺🌺🤲🌻 የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ምልጃና ጸሎት ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን ደህና እደሩ 👏🤲🕊#CapCut #viralvideo #fypシ゚viral🖤tiktok #fppppppppppppppppppp
ኤፍታህ 🤲🕊 ❤️የገብርኤል ልጂ
Region: AE
Thursday 30 July 2026 01:42:15 GMT
Music
Download
Comments
user4221360080279 :
እግዛቤር ይመስገን
2026-07-30 02:52:11
0
merem :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-07-30 02:50:29
0
To see more videos from user @alemgeleta, please go to the Tikwm
homepage.