@israel.du: በቤተ ክርስቲያን ደወል!!! ለምን ይደወላል? ትርጓሜው? መቼና እንደት ይደወላል? ደወል የተጀመረው በኖኅ ዘመን እንደ ነበረ አባቶች ያስተምራሉ ሰው ካህናት ለአገልግሎት እንዲወጡ ለመጥሪያነት ያገለግል ነበረ። ደወል፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከብረት፣ እና ከመሳሰሉት ድምጽ ሰጪ ነገሮች ሊሰራ ይችላል በክብ ቤተክርስቲያን ከሆነ የደወል ቤት ተነጥሎ ይሰራል በመስቀል ቅርጽ የተሠራ ቤተክርስቲያን ከሆነ ደግሞ ከቤተ መቅደሱ ጋር ተያይዞ እረዘም ብሎ ይሰራል። ደወል በተለያዬ ሰዓት በቤተክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት ይደወላል ነገር ግን ለሁሉም አገልግሎት አንድ አይነት ደወል አይደወልም። ፩ኛ #የተጋብኦ #ደወል ለአገልግሎት የተመደቡ ካህናት እንዲሁም ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን እንዲሰበሰቡ የሚደወል ደወል ነው ሰዓታት ማህሌት፣ ኪዳን፣ ቅዳሴ፣ ከመግባቱ የቤተክርስቲያን በር ከመከፈቱ ይህ ደወል ይደወላል የተጋብኦ ደወል የትንቢተ ነቢያት ምሳሌ ነው። የትንቢት ምሳሌ ነው ነቢያት ሕዝቡን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሱ የጌታ ልደት ለአዲስ ኪዳን እንዲዘጋጁ ያደርጉ ነበር። ይህ የተጋብኦ ደወልም ምዕመናንን እና ካህናት ከእንቅልፍ ኃጢያት እንዲነቁ ለጸሎት ያዘጋጃል። ፪ኛ.#የቅዳሴ #መግቢያ #ደወል ካህናቱ መስዋቱን አክብረው ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ሲመለሱ እና ቅዳሴ ሲገቡ የሚደወል ደወል ነው በእነዚህ ጊዜ ምዕመናኑ ሁሉ በአክብሮት ዝቅ ይላሉ *አምስት ጊዜ ይደወላል *አምስት ጊዜ መደወሉ የአምስቱ አዕማድ ምሳሌ ነው ምሳሌነቱ የዚህኛው ደወል ምሳሌ እመቤታችንን ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና እያለ ያበሰራትን የመላእኩ የቅዱስ ገብርኤልን ብስራት ምሳሌ እደሆነ ሊቃውንቱ ይናገራሉ። ይሄ ደወል ቅዳሴ መግባቱን መሥዋት የሚሰዋበት ጊዜ መሆኑን እንደሚገልጽ ቅዱስ ገብርኤልም የክርስቶስን መወለድ አብስሩአል ልደቱም በቤተልሔም ተፈጽሟል። አንድም ይህ ደወል መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እነሆ የአለምን ኃጢያት የሚያስተሰርይ የእግዚአብሔር በግ (ዮሐ 1፥19) ብሎ የጮኸው ድምፅ ምሳሌ ነው። ፫ኛ. የወንጌል ደወል ወንጌል ከተነበበ በኋላ ዲያቆኑ "ፃዑ ንዑስ ክርስቲያን ብሎ ሲያውጅ የሚደወል ሲሆን ሶስት ጊዜ ይደወላል ሶስት ጊዜ መደወሉ የሥላሴን ሚስጢር ያሳያል ምሳሌነቱ ቅዱስ ዮሐንስ፣ የሐዋርያት እና የሰብአ አርድዕት ምሳሌ ነው ጌታችን በወንጌል ከማስተማሩ በፊት የሰዎችን ልብ ለንስሐ ለማዘጋጀት መንገድ ጠራጊው አዋጅ ነጋሪው መጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ትምህርት አስተምሩል (ሉቃ 1:31) ፬ኛ. በፍሬ ቅዳሴ ላይ ገባሬ ሠናይ ካህኑ ተጨማሪ ካህናት እና ምዕመናን እየተቀባበሉ 41 ጊዜ ክርስቶስ ይባላል። *አስራ ሁለት ጊዜ ይደወላል *የ12 ሐዋርያት ምሳሌ ነው ምሳሌነቱ በዚህ ጊዜ የሚሰማው የደወል ድምፅ እመቤታችን እና የወንጌላዊው ምሳሌነቱ የለቅሶ ድምፅ ምሳሌ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ሲሰቀል ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በእግረ መስቀሉ ስር አልቅሰዋል (ዮሐ 19:25) ዛሬም ምዕመናን እግዚኦታ ሲደረስ መስቀሉን እያሰቡ እንደ እመቤታችን እና እንደ ዮሐንስ እንዲያዝኑ እንዲያለቅሱ ይህ የደወል ድምፅ ይሰማል። ፭ኛ. ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ ተፈትቶ ለምዕመናን ለማቀበል ካህናቱ ከመቅደስ ወደ ቅድስት ሲወጡ የሚደወል ደወል ነው። ምሳሌነቱ በዚህ ሰዓት የሚደወለው ደወል የቅዱስ ዮሴፍ እና የቅዱስ ኒቆዲሞስ ለቅሶ ምሳሌ ነው እንዲሁም (ሉቃ 23:50) ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ ጌታን ከቅዱስ መስቀሉ አውርደው እያለቀሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘእይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሰሐለነ እግዚኦ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘእይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ዘተሰቅለ ዲበ እፀ መስቀል ተሰሐለነ እግዚኦ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ዘእይመውት ዘተንሰአ እናት ቤተክርስቲያን ሁሉንም ነገሯ መጽሐፋዊ ነው በፍጹም ልማዳዊ ነገር አታደርግም

እስራኤል
እስራኤል
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 30 July 2026 11:35:24 GMT
6553
769
4
78

Music

Download

Comments

israel.du90
መዝሙር :
🥰
2026-08-05 16:30:26
0
guesh.gremariyam
Guesh;TDF :
🙏🙏🙏
2026-07-31 09:38:36
1
mesfin3877
Mesfin :
🙏🙏🙏
2026-07-30 16:04:52
1
user5809010776881
⛤🅰ምኞት ኣይከለከልም✡ :
🙏🙏🙏
2026-07-31 12:29:35
1
To see more videos from user @israel.du, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About