@birhanu.shewayeparenting: 🌱ልጅ እስከ 3 ዓመት ድረስ እንደ ለጋ ቡቃያ ነው ብዙ ነፃነት እና ትዕግስት እንጅ ብዙ ጫና፣ቁጥጥር፣ሃይል አይፈልግም። ገበሬ ሰብል ሲዘራ፣ አረሙም አብሮ ይበቅላል ነገር ግን ሰብሉ ገና ለጋ ቡቃያ ሲሆን፣ ገበሬው ወደ እርሻው ገብቶ አረሙን አይነቅልም። ምክንያቱም አረሙን ለማውጣት ሲሞክር፣ ለጋውን ቡቃያ ሊረግጥና ሊጎዳው ይችላል። ስለዚህ ቡቃያው እስኪጠነክር ይጠብቃል። ወላጆችም እንዲሁ ናችሁ። ከ1 እስከ 3 ዓመት ያሉ ልጆች በጣም ስሱ ናቸው። በዚህ ዕድሜ ውስጥ ዋናው ሥራቸው ዓለምን መመርመር፣ መንካት፣ መጫወት እና መማር ነው። በየደቂቃው "አትንካ!" "አትሂድ!" "አታድርግ!" ስንል፣ እድገታቸውን ሳናውቅ ልንጎዳ እንችላለን። ነፃነት ስጧቸው… ግን ደህንነታቸውን በሚጠብቅ ወሰን ውስጥ። ለጋ ቡቃያ በመጫን አያድግም፤ ለማደግ ምቹ አካባቢ ሲያገኝ ይጠነክራል። ልጅን አትቸኩሉ… አሳድጉት። 🌱። #creatorsearchinsights #gentleparentingfortoddlers #Healthyparenting #Ethiopianparents #parentingwisdom

BSPP
BSPP
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 30 July 2026 12:16:03 GMT
3584
285
7
126

Music

Download

Comments

amthewayandthetruthandth
meki -yegeta :
አረፈድኩ 3 አመቷ በጣም ፈሪ ድንጉጥ ሆነች
2026-07-30 20:13:59
1
frehiwot163
ፍሬ🧚‍♀️ :
በጩኸቴ በጣም ፈሪ ሆናለች ኮንፊደንሷን እንድታዳብር እንዴት ላግዛት?
2026-07-30 16:16:28
0
mistremelese
@Miss💃🏻💐 :
2026-07-30 14:51:12
0
justice_piku
justice_piku :
🥰🥰🥰
2026-07-30 12:55:56
1
zereyaw
ሰርሳሪው 🗽 🇺🇸 🦂 :
👍👍👍
2026-07-31 03:06:10
0
To see more videos from user @birhanu.shewayeparenting, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About