@viewer_1221: "ወንድ ልጅ አያለቅስም!" ይህን ቃል ማን አስተማረን? ማን ነው እንባን ከወንድነት ጋር ያጣላው? ማን ነው ወንድ ልጅ ሲያዝን እንዳይናገር፣ ሲጎዳ እንዳያለቅስ፣ ሲደክም እንዳይጮህ ያስተማረው? እውነት ግን... ወንድ ልጅ አያለቅስም ያለው ማነው? ወንድም ሰው ነው። ልብ አለው። ስሜት አለው። ይወዳል። ይጎዳል። ይናፍቃል። ይሰበራል። ይደክማል። ወንድ ልጅ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል። አንዳንድ ወንዶች ግን ሕይወታቸውን ሙሉ የሚያለቅሱት በሰው ፊት አይደለም፤ በሌሊት ነው። ሁሉም ሲተኙ... የሚያስቧቸውን ነገሮች አስበው፣ የሚናፍቋቸውን ሰዎች ናፍቀው፣ የሚያምማቸውን ህመም ደብቀው...በጨለማ ውስጥ እንባቸውን ያፈሳሉ። ጠዋት ሲነጋ ግን ፊታቸውን ያብሳሉ። "ደህና ነኝ" ይላሉ። እና እንደገና ወደ ሕይወት ይመለሳሉ። ምክንያቱም ዓለም ከእነሱ የምትጠብቀው ይህንን ነው። "አንተ ወንድ ነህ። ጠንክር!" ነገር ግን ሰው ሁልጊዜ ጠንካራ መሆን የለበትም። አንዳንድ ጊዜ መውደቅ አለበት። አንዳንድ ጊዜ ማልቀስ አለበት። አንዳንድ ጊዜ ሰውን አግኝቶ "በጣም ደክሞኛል" ማለት አለበት። እንባ ድክመት አይደለም። እንባ የልብ ቋንቋ ነው። ልብ ቃላት ሲያጣ እንባ ይናገራል። ስለዚህ ወንድ ልጅ ሲያለቅስ አትሳቁበት። "ወንድ ነህ እኮ!" አትበሉት። ይልቁንም አጠገቡ ቁሙ። "እኔ አለሁልህ" በሉት። ምክንያቱም ዛሬ የምታለቅስ ወንድ ልጅ ነገ ሌሎችን የሚያበረታ ጠንካራ ሰው ሊሆን ይችላል። ዛሬ በሰው ፊት እንባውን የሚደብቅ ወንድ ልጅ ግን... ነገ ህመሙን ብቻውን ለመሸከም እስኪሰበር ድረስ ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ... ወንድ ልጅ አያለቅስም ያለው ማነው? እንባውን ከደበቀ ወንድ አይሆንም። ህመሙን በጸጥታ ተሸክሞ ለሌሎች ደስታን የሚሰጥ ወንድ ነው። እንባውን አፍስሶ እንደገና የሚነሳ ወንድ ነው። የተሰበረ ልቡን ጠግኖ እንደገና መውደድ የሚችል ወንድ ነው። ስለዚህ ወንድሜ ካለቀስክ አትፈር። ከደከመህ እረፍ። ከተሰበርክ እርዳታ ጠይቅ። ከተጎዳህ ተናገር። እንባህን አትጥላው፤ እሱ የሰውነትህ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም እውነተኛ ወንድነት እንባን መደበቅ አይደለም፤ እንባ ካፈሰሰ በኋላ የሚጠብቀውን ሰው፣ የሚወደውን ሰው እና የሚያምነውን ነገር ሳይተው እንደገና መቆም ነው። ወንድ ልጅ አያለቅስም ያለው ማነው? እኔ ግን እላለሁ... ወንድ ልጅም ያለቅሳል። ይወዳል። ይጎዳል። ይሰበራል። ነገር ግን ከእንባው በኋላ እንደገና ይነሳል። ይህ የእኔ እይታ ነው✍️ ሰናይ ቀን🙏 ቀጣይ ሌሎች እይታዎች እንዲደርስዎት የእኔ እይታን ፔጅ Follow, Like, Share, Repost እና Copy Link በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #foryou #fyp #viral #fypシ #viralvideo

የእኔ እይታ
የእኔ እይታ
Open In TikTok:
Region: SO
Thursday 30 July 2026 13:08:13 GMT
11785
719
28
151

Music

Download

Comments

user153619725971
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 :
Nice road, good lighting.
2026-07-30 17:26:03
1
negat984
Yeruqi sew aykifaw🥹🇪🇹💞 :
yaleqisal🥹🥹🥹
2026-07-31 07:01:34
0
.h3253
የተቀማሂወት :
ወላሂያለቅሣል ግንለሁሉምሤት ከልቡላፈቀራት ሤት ያዉምሥቅሥቅብሎ 🥺🥺🥺🥺🥺🥺
2026-07-31 01:01:07
1
seid5648
💔 :
ወጉ ደረሰኝ አልሀምዱሊላህ መሞከሩ አይከፋም ትማርበታለህ
2026-07-31 03:24:23
1
usethiopian
Ⓜ & E 💟 :
ሁሉም የሂዎት ውጣ ውረድ ለነሱ ከባድ እንደሆነ እያወቅን ግን ሁሌ ጠንካራ ሁነው ይታያሉ አታፍኑት በሌሊት ስታለቅሱ አወ ፈጣሪ ያያችሗል ግን አንዳንዴም ለሰው አጋሩ ምን አልባት ሌሎች ሌሊቶችን ማቅስ ላይኖርባችሁ ይችላል
2026-07-30 17:37:45
3
ahimad557
I ሰው መሆን :
አዎ ወንድሜ ሁሉም ነገር ከልክና ከአቅም በላይ ከሆነ እነዚህ ያልካቸውን ስሜት ሁሉ ታስተናግዳለህ
2026-07-30 17:14:19
2
farxiyaxashi3
farxiyaxashi3 :
እኔስ ጨነቀኚ እዴት ሁኘስ ማንስ ይስማኚ እዴትስ ይስማኚ መፍቴውን ካገኘው መዳኛ አለኚ
2026-07-31 18:15:49
0
temre.awel
Te ወሎየዋ :
ያዉም የሚያለቅሰዉ ወደዉስጡ ነዉ አብሺር
2026-07-30 21:21:40
1
feysel421
⚡️⚔️ 𝑙𝑖𝑗 𝑓𝑎𝑦𝑎 ➹🕸⚡️ :
ኧረ ማነው ያለው 🥺እዴት አናለቅስ😭
2026-07-31 15:56:32
0
hussen1122mm
@መደድ ላይቀር ጭሡ ገደለኝ🤔 :
ለምን ነዉ እማለቅሥዉ እ
2026-07-31 14:08:08
0
habesha537
Temam Habesha 🤳 :
ሁሉም ልክ ነው 🥺
2026-07-31 13:53:38
0
u498111111
በፌ ሰው አክበር🇪🇹💪 :
👍👍👍👍tenkwu,bero
2026-07-30 18:57:24
1
endalk3802
ENDALK :
Ene
2026-07-30 13:35:54
1
user7077574466547
የነገን ማን ያውቃል :
እውነት ነው
2026-07-31 06:06:41
0
e..g088
E. G :
ማልቀስ እኮ አንደንደዬ በቃላት መናገር ያቃተንን ቃል ይናገራል 😢😢
2026-07-31 07:38:10
1
mesi88679
Mesi :
ብቼኝነት ብቻ ሲቀር አታልቅሱ እኛም ወግ ደሮሶን እናባብላችሁ 🥰🥰
2026-07-30 15:56:32
1
mudinmudin288
ያልፋል :
እምባ ረሱ ጉቦ በፈለገበት ጊዜ እንዴት ይለቀሳል ሆድ ይፍጀዉ ማለት ነዉ
2026-07-31 18:32:44
1
mamonaw.mamonaw
Mamonaw Mamonaw :
bexami yaleqisali
2026-07-30 21:37:22
0
maywllo09
May wllo🇪🇹💞 :
👍👍👍
2026-07-30 17:00:55
1
hewan2572
Hewan👑 :
❤️❤️❤️
2026-07-30 16:16:56
1
user3226009175508za
derje :
🥰🥰🥰
2026-07-31 08:39:38
0
user5555088241611
user5555088241611 :
👌👌👌
2026-07-30 22:11:23
0
slyam006
AIHAMDIUIiIAH 📕📚📚✏️👳‍♂️ :
🥹🥹🥹🥹
2026-07-31 11:15:50
0
user20619584583955
አይንየ 💫 💫(ሙሉ ሽዋ) :
👌👌👌
2026-07-30 19:03:01
1
itisme1421
it's me💖💕 :
🥰🥰🥰
2026-07-30 15:09:53
1
To see more videos from user @viewer_1221, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About