@enduplus: እኔስ ናፍቀሽኛል ፡ ናፍቀሽኛል ብልሽ ቃሉን አሳንሼ፤ ቃላት ቢቸግረኝ መዛግብት አስሼ፤ ፡ እንዳትቀየሚኝ ፡ ቋንቋ ባጣ ኖሯል ፤ እንዲ እንደዋዛ ያልኩት ናፍቀሽኛል፡፡ ፡ ናፍቀሽኛል ስልሽ ናፍቀሽኝ ከልቤ ሳቁ፡ ጨዋታሽን፡ ኩርፊያሽን ተርቤ ፡ ያ የዋርካ ዛፍ ፥ ፍቅር ያወጋንበት ያ ውብ ጎዳና፥ ዘውትር ምንሄድበት ያዳመጥነው ዘፈን የፈጠርነው ዜማ ፤ ያካለልነው ሰፈር ያ ሰፊ ከተማ... ፡ አብረን ያሳለፍነው ያንን ሁሉ ጊዜ እኔ አልጠራልሽም ፤ 'ትዝታሽ ትዝ አለኝ' ብዬ አላደክምሽም፡፡ ፡ ግና ብቻ ውዴ የፍቅርሽን ጦም፥ የፍቅሬን ሁዳዴ ፤ ልባችን ውስጥ ያለ ባዳ የማያውቀው ፤ 'ሆድ ይፍጀው' ብያለው ሆድሽ ስለሚውቀው፡፡ ፡ ... #ethioviral #creatorsearchinsights #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #habeshatiktok #foryoupage

E N D U  +
E N D U +
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 30 July 2026 18:28:08 GMT
403
28
1
11

Music

Download

Comments

enduplus
E N D U + :
ለራቅሽኝ 😢
2026-07-30 18:28:30
0
To see more videos from user @enduplus, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About