@kenu_lemma: 1. መራቅ (lack of intimacy)፦ ምንነቱ፡- ከቤተሰብ፣ ከጓደኞችና ከፍቅር አጋር ጋር የሚኖርን አካላዊና ስሜታዊ ቅርበት መቀነስ እና ራስን ከማኅበራዊ ሕይወት ማግለል። ምክንያቱ፡- ይህም የሚሆነው ፖርኖግራፊ ከተፈጥሮ ግንኙነቶች ይልቅ ከፍተኛ ዶፓሚን በሰው አንጎል ውስጥ እንዲለቀቅ ስለሚያደርግ ይህን የተለማመደ አንጎል ከሰዎች ጋር የሚደረግ መቀራረብን ከንቱ እና ጥቅም አልባ አድርጎ ስለሚመለከት ነው፡፡ መገለጫው፡-  ከሰዎች ጋር ላለመገናኘት ምክንያቶችን መደርደር፣ ለብቻ መሆንን ማስቀደም፣ የስልክ ጥሪዎችን አለመመልስ እና ከጓደኞች እና ከቅርብ ሰዎች መራቅ። 2. መናቅ (Objectification)— ምንነቱ፡- ሰዎችን በስብዕናቸው፣ በስሜታቸውና በክብራቸው ሳይሆን ለግል ፍላጎትና እርካታ እንደሚጠቅሙ የወሲብ ዕቃዎች ብቻ አድርጎ የመመልከት አዝማሚያ። ምክንያቱ፡- ፖርኖግራፊ ፍቅርን ራስን ለሌሎች ከመስጠት ወደ ሌሎችን ለራስ መጠቀም ያወርደዋል፡፡ በዚህ ውስጥ ሰዎች ሰብዐዊ ፍጥረት ሳይሆኑ የወሲብ እቃዎች ብቻ ይሆናሉ፡፡ መገለጫው፡-  ንግግሮቻቸው እና ቀልዶቻቸው ሁሉ ወሲባዊ መሆን፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ በአእምሮ እርቃናቸውን መሳል፣ ለሌሎች ሰዎች ስሜት ደንታ ቢስ መሆን፣ የፍቅር አጋርን ወይም ሰዎችን እንደ ፍላጎት መወጫ ቁስ ማየት፣ እና በሰዎች ድካም ወይም ስቃይ ላይ ርህራሔ ማጣት። 3. መደበቅ (Secrecy)፦ ምንነቱ፡- ምንነት፦ ድርጊትን፣ የሚያጠፉትን ጊዜ፣ የስልክ/የኮምፒውተር አጠቃቀምን እና እውነተኛውን ማንነት ከቅርብ ሰዎች መሸሸግ። ምክንያቱ፡- ከትችት፣ ከእፍረት፣ ከውርደትና ከግንኙነት ማጣት ፍርሃት ራስን የመጠበቅ ጥረት ነው። መገለጫው፡- የስልክ/የላፕቶፕ የይለፍ ቃል ደጋግሞ መቀየር ወይም እነዚህን ዕቃዎች ለማንም አለማጋራት፣ ደጋግሞ ስለ ውሎ፣ ስለ ሥራ መዋሸት፣ ከሌሎች ተነጥሎ ለብቻ ለመሆን በተደጋጋሚ መሞከር 4. መቃዠት (Fantasy or Over expectation)፦ ምንነቱ፡- በእውነተኛው ሕይወት፣ በሰዎች፣ በስሜታዊና በፆታዊ ግንኙነቶች ላይ ከተፈጥሮና ከእውነታው የራቀ፣ እጅግ የተጋነነ እና የማይጨበጥ ከፍተኛ ግምት (over expectation) በማስቀመጥ ተስፋ ማድረግ። ምክንያቱ፡- ፖርኖግራፊ በመድኃኒቶች እና በቪድዮ ኤዲቲንግ የተቀናበረ፣ የተስተካከለና የተጋነነ ወሲባዊ ማነቃቂያ (Supernormal Stimuli) ነው፤ በዚህ ምክንያት በጭራሽ እውነተኛው ዓለም ሊተገበር የሚችል ወሲባዊ ድርጊትን እና የፍቅር ግንኙነትን የሚያመለክት አይደለም፡፡ መገለጫው፡- በፍቅር ግንኙነት ፈጥኖ መሰላቸት (ፖርኖግራፊን የሚመስል ግንኙነት መትከል ስላልተቻለ)፣ በትዳር ውስጥ በወሲባዊ ግንኙነት አለመርካት፣ ማንም ሰው እኔ እንደምፈልገው ሊሆን አይችልም ማለት፣ ተስፋ መቁረጥ 5. መዘንጋት (Irresponsibility)፦ ምንነቱ፡- በቤተሰብ፣ በትዳር፣ በፍቅረኝነት እንዲሁም በሌሎች ግንኙነቶች ውስጥ የሚጠበቁ ማኅበራዊ ኀላፊነቶችን አለመወጣት ምክንያቱ፡- የአንጎል የውሳኔ ሰጪና የትኩረት ማዕከል የቁጥጥር አቅሙን በማጣቱ (Executive Dysfunction) ፈጣን ደስታ የሚሰጡ ነገሮችን ቀዳሚ በማድረግ ከማኅበራዊ ኀላፊነቶችን አለመወጣትን ያስከትላል። መገለጫው፡- የቤት ወይም የሥራ ኃላፊነቶችን ማዛነፍ፣ ቀጠሮዎችን መዘንጋት፣ ለትምህርትና ለሙያ እድገት ያለው ተነሳሽነት መሞት እና ጊዜን ባልተገቡ ነገሮች ማባከን።

Kenean Lemma
Kenean Lemma
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 31 July 2026 09:02:50 GMT
5867
42
0
4

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @kenu_lemma, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About