@musictube369: ቂም አልይዝም ባንቺ 🤒 ✍️"ፍቅር በደልን አይቆጥርም " ማለት አይሮፕላን ሰው አይገጭም እንደማለት ነው ! ምክንያቱም ከፍ ብሎ ስለሚበር ! ከፍ እያልክ ስትሄድ ነገሮች ትንንሽ መሆን ይጀምራሉ " የሚለው ድንቅ አባባል በዘፈን ጥበብ ሲገለጥ ! በይልማ ገ/አብ ብዕር ተወልዶ በሞገስ ተካ የዜማ ባህር በኤፍሬም ታምሩ ድምፅ የተጠመቀ ጥንቅቅ ያለ የፍቅርና የይቅር ባይ "ልብ " የመጨረሻው ጥግ ! ማሳያ ነፍስ ያለው ሙዚቃ👌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የ70ዎቹን ሙዚቃ አብዝቶ ይወድ ነበርና ከ1970ዎቹ ጀምሮ ገናና ስም የነበረውን ኤፍሬም ታምሩ እንዲያዜምለት በልዩነት መረጠ ለወትሮውም ዜማ እና ግጥምን በጥንቃቄ በመምረጥ እና ለአድማጭ በመጠንቀቅ የሚሰራው አንጋፋው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ጊዜያዊ መኖሪያውን ካደረገበት ሀገረ አሜሪካ የሙዚቃ አልበም ለመስራት ወደሀገሩ የመጣበት ወቅት ስለነበር ይህን ማራኪ ግጥም እና ዜማ በመቀበል በታሪኩ ባለቤት አማኑኤል ይልማ እና በታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ አቀናባሪነት በግሩም ሁኔታ ተሰርቶ የአልበሙ መጠሪያ ለመሆን በቃ ። በእውነተኛ ታሪክ ላይ በተመሰረተው ሙዚቃ የተመሰረተው "ኋላ እንዳይቆጭሽ" አልበም ይህ በ1998 አ.ም መገባደጃ በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ለአድማጭ የደረሰው የኤፍሬም ታምሩ አልበም ልክ ዛሬ እንደጋበዝኳቹ ቂም አልይዝም ባንቺ ሁሉ በታላቁ የግጥም ደራሲ ይልማ ገ/አብ ተደርሶ ዜማው በሞገስ ተካ የተሰራው በማህበራዊ ኑሮ ደስታ እና መከራ መውረድ እና መውጣት ማግኘት እና ማጣት ላይ መሰረቱን አድርጎ ሁሌ በከፍታ ሁሌም በዝቅታ መኖር እንደሌለ ከሁሉም በላይ ሀያል በሆነው በጊዜ ውስጥ ሁሉም ተለዋዋጭ ስለመሆኑ የሚያስረዳው “ሰው መሰረቱ” አይነት ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ይዟል ይህ አልበም በፍቅር ውስጥ ቁንጅናን፣ መለየትን፣ ናፍቆትን፣ በደለን፣ ይቅርታን፣ አግራሞትን እና እድለኝነትን መሰረት ያደረጉ 12 ሙዚቃዎችን አካቶ የያዘ በእጅጉ ተደማጭ የሆነ እንዲሁም በሀገራችን ሙዚቃ ትልቅ ስም እና አሻራ ያላቸው ባለሙያዎች የተጣመሩበት በእጅጉ የተዋጣለት አልበም ነው ይልማ ገ/አብ፣ ሀብታሙ ቦጋለ፣ መሠለ ጌታሁን፣ አማኑኤል ይልማ በግጥም ቴዲ አፍሮ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ሞገስ ተካ፣ እንዳለ አድምቄ፣ ፋንታሁን ወጨፎ በዜማ እንዲሁም ታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ ጨምሮ አማኑኤል ይልማ፣ሳምሶን ጎሳዬ በቅንብር የተሳተፉበት ሲሆን እራሱ አንጋፋው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ሳላስበው፣ሙሉ ጎጃም፣ ቂም አልይዝም ባንቺ በተሰኙ በ3 ስራዎች ላይ በሙዚቃ ማቀናበርም ተሳትፎበታል ። 📌የአይንሽ ዛጎላማ ነው የደሞ ጀመረኝ የኋላ እንዳይቆጭሽ .... ኤፊያችን ባህርዳር ቢወለድም አብዛኛው የህይወት ትዝታው የከተመው ግን ከአባትና እናቱ አገር ደጀን ነው፡፡ የፖስታ ቤት ስራ አስኪያጅ የነበሩት አባቱ የሥራ ዝውውር ምክንያት ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ክፍል ያለውን ጊዜውን ባህር ዳር፤ደብረማርቆስ፤ዲላ፤ወሎ ጠቅላይ ግዛት፤ አዲስ አበባ በመዘዋወር ተምሯል፡፡ በአባቱ የጤና እክል ምክንያት ቤተሰቡ ወደ ደጀን ተመልሶ ትምህርቱን እዛው ቢቀጥልም በስካውት ; የትያትርና የሙዚቃ ክለቦችም በመሳተፍ የነፍሱ ጥሪ የሆነውን የሙዚቃ ችሎታውን የተረዳበት ወቅትም ነበር፡: በወቅቱ የተለያዩ ከተሞችን በመዘዋወር የሙዚቃ ስራቸውን ከሚያቀርቡ ባንዶች ጋር ከቤተሰቡ በመደበቅ የክረምትን ሁለት ወራትን አብሮ ያሳልፍ ነበር ፡፡ የቤተክርስቲያን ሰዎች የነበሩት ወላጆቹ በተለይም አባቱ ይህንን በመቃወም በእግር ብረት እስከማሰር ቢደርሱም ሙዚቃ በቤቷ ልታነግሰው ወዳለችና በቀጣይ ክረምቶችን በተመሳሳይ የሙዚቃ ስራ ያሳልፍ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት በጎጃም 7ቱም አውራጃዎች መካከል በዘመናዊና ባህላዊ ሙዚቃ ውድድር ሲደረግ በዘመናዊ ሙዚቃ አንደኛ በመውጣቱ በደብረማርቆስ ሃይስኩል ውስጥ የነበረው የብሉናይል ኦርኬስትራ ይህንን በማየት ቀጥሮት ከባንዱ ገቢ 18 ፐርሰንት እየተከፈለው ከደጀን ደብረማርቆስ እየተመላለሰ የጥላሁን ገሰሰን ሙዚቃ ያቀርብ ነበር፡፡ ዝነኛው ኤፍሬም ታምሩ የሚለው ስያሜም ከዛን ወቅት ጀምሮ ያገኘው ይመስላል፡፡ በህይወቱ ትልቅ ቦታ እንዳለው የሚመሰክርለት ድምፃዊ አያሌው መስፍን ጋር ለመስራት ባገኘው አጋጣሚ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ዛምቤዚክ የተባለ የምሽት ክለብ ስራ ጀመረ፡፡ በታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ ድምፃዊ አሊ ቢራ ፈታኝነት በቀን 3 ብር ደሞዝ የተጀመረው የሥራ ህይወቱ ቬነስ ክለብ፤ ሆቴል ዲ-አፍሪክ ፤ ራስ ሆቴል ፤ ጊዮን ሆቴል ፤ሂልተን ሆቴል፤ በመጫወት ቀጥሏል:: “ገና ልጅ ነኝ ጋሜ“ የመጀመሪያ አልበሙ ሲሆን ከታዋቂዎቹ የግጥምና ዜማ ደራሲዎች ይልማ ገ/አብ እና ዶ/ር አበበ መለሰ ጋር የሰራው “ነይልኝ“ ከህዝብ ጋር የተዋወቀበት የምንግዜም ልዩ ስራው ነው፡፡ ለአድናቂዎቹ ባበረከታቸው 12 አልበሞች ፍቅር፤ትዝታ፤ሀገር፤ናፍቆት፤መለያየት:ይቅርታ በማራኪ ጥበብ በድምፁ ተዘክረዋል፡፡ አድናቂዎቹ የድምጻዊው ስራዎች የፍቅር ህይወታቸው አጋፋሪ፤ የትዝታ መሰላል; የሃዘን ማስረሻ እንደሆኑላቸው ይመሰክራሉ እኔን ጨምሮ ለዛም ነው ዛሬ እናመሰግነው ዘንድ ይሄን ሙዚቃ ከ11ኛ አልበሙ "ኋላ እንዳይቆጭሽ" ላይ መርጬ ጋበዝኳቹ ፈጣሪ ዕድሜን ከጤና ጋር ጨምሮ ይስጥህ እናመሰግንሃለን 🙌🥰 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #ኤፍሬምታምሩ #ቂምአልይዝምባንቺ #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 31 July 2026 19:38:32 GMT
109205
11032
60
746

Music

Download

Comments

joshuaking705
Joshua king :
ሁሌም አንተ ትለይብኛለህ ማርያምን🙌🙌
2026-07-31 19:52:22
16
blaugrana_k
Blaugrana 🔵🔴 :
Who's የኔሰው ተፈራ ግን 😭 I saw bro's name in some songs but I've never seen him in any media
2026-08-01 10:26:00
3
na.ni425
...Ephremawit.🦋 :
ephremn gn endene miwedew ale🫶❤️‍🩹
2026-07-31 21:02:45
6
naodilove42
Naodilove42🥰🤗🔥 :
ኤፊን ስሰማዉ የሚሰማኝ ስሜት🥺😫
2026-08-01 08:56:02
6
leule.cr7
leule.M :
endet fexari hulun neger amualto yisexal ere efi 👏👏👏
2026-08-02 17:59:05
1
tadee718
Tadee :
Ephemen baxem now miwodo🔥
2026-08-03 17:03:52
0
yemicole47
🤎 :
jealous of whoever with this kind of heart 😭
2026-08-01 08:34:34
2
saidhuseen11
saidhuseen11 :
epu yilayali eko🥰
2026-07-31 21:21:20
1
gukoo27
𝕘𝕦𝕕𝕕𝕖💙❤💚 :
lubishaa💞💞💞💞💞
2026-08-03 03:05:33
0
jo_19_21livelife
john ye 19 lije :
ምን ኣይነት ዘፈን ነዉ❤️❤️❤️
2026-08-03 06:43:59
0
michaeltaye4
michaeltaye4 :
ሞገስ ተካ ግን
2026-08-01 14:08:56
1
mussie208
Mussie208 :
ለፍቅረኛየ 5 ጊዜ ጋብዣት ወፍ😭
2026-08-01 06:16:27
2
fker.mhert
fker mhert :
@🇯🇲𝚕𝚒𝚍𝚞𝚗𝚊 🦋.. 🥀
2026-08-01 13:29:08
1
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-31 20:17:07
2
alax83
Alax keyo :
🥰🥰🥰
2026-08-01 09:09:22
1
kevinbonii27
bini oroo ♦️♦️♦️ :
🥰🥰🥰
2026-08-01 13:11:28
1
nuuraa331
Jo. Joo. ኑ ራ 🌹🌹 :
😁😁😁
2026-08-01 14:22:21
1
solomon.sol31
SOLOMON Sol :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-31 19:40:53
1
melesmeles715
Melsew Andualem715 :
🥰🥰🥰
2026-08-01 03:25:02
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About