@abebayehuassefatkursew: የሼክ አልአሙዲ ሀብት ከ10 ቢሊዮን ዶላር አለፈ፡፡ የሼክ መሀመድ አልአሙዲ የሀብት መጠን 10.1 ቢሊዮን ዶላር መግባቱን ተከትሎ የአለም ሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ተመልሰው ለመግባት ቻሉ፡፡ ዛሬ ኦገስት 1 ቀን 2026 ይፋ የሆነው የብሉምበርግ የአለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ አልአሙዲ በ375ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ይህንን ደረጃ ለማግኘት የቻሉት በዚህ አመት የሀብታቸው መጠን በ1.67 ቢሊዮን ዶላር ወይንም 19.7 ፐርሰንት ጭማሪ በማሳየቱ ነው፡፡ አልአሙዲ ከጥቂት አመታት በፊት ከነበሩበት የሀብት ማሽቆልቆል አሁን ተመልሰው ወደላይ እየወጡ መሆኑን የሚገልፀው ይህ ሪፖርት በቅርቡ በወጣ መረጃ በአንድ ቀን ሀብታቸው በ33.7 ሚሊዮን ማደጉን አስረድቷል፡፡ እንደሪፖርቱ ለአልአሙዲ ሀብት መጨመር ትልቁን ሚና እየተጫወተ ያለው በስዊድን የሚገኘው ፕሪም የተሰኘው ነዳጅ ማጣሪያቸው ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በብሉምበርግ የአልአሙዲ ሀብት ከ10 ቢሊዮን ዶላር ማለፉ የተገለፀ ቢሆንም በፎርብስ አመታዊ የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ግን ስማቸው አልሰፈረም፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ሁለቱ ተቋማት የቢሊየነሮችን ሀብት የሚገምቱበት የአሰራር መንገድ ስለሚለያይ ነው፡፡ ብሉምበርግ የቢሊየነሮችን መረጃ የሚያሰላው በአለም አቀፍ ደረጃ በየእለቱ በሚከናወኑ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ ፎርብስ ግን ከዚህም በላይ የራሱን ግምገማ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ አንዳንዴ ከባለሀብቶቹም ትክክለኛውን መረጃ ያረጋግጣል፡፡ (ዘ-ሐበሻ ዜና)

ጥቁር ሰው ሚዲያ Tkursew ✅
ጥቁር ሰው ሚዲያ Tkursew ✅
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 01 August 2026 17:17:39 GMT
4220
69
4
2

Music

Download

Comments

teredugn
you zer neme 26.🌷 🇪🇹 :
ከቲሪሊየን ያለፈ እያለ 10 ትለናለህ
2026-08-01 20:03:53
0
naod6380
Nani :
እና ?
2026-08-01 17:26:35
0
desunews_27
DESU-NEWS🌍 :
😏😏😏
2026-08-01 17:24:43
0
mesih801
Mesfn2 :
🥰🥰🥰
2026-08-01 17:37:35
0
To see more videos from user @abebayehuassefatkursew, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About