@viewer_1221: አንድ ወቅት ላይ ሕልማችን ትልቅ ነበር። እኛም እንደ ሕልማችን ትልቅ እንሆናለን ብለን እናስብ ነበር። ዓለም በፊታችን የተከፈተች ትመስለን ነበር። የምንፈልገውን ሁሉ እናገኛለን፣ የምንመኘውን ሁሉ እናሳካለን ብለን እናምን ነበር። ዛሬ ግን... ከሕልማችን ጋር ያለን ርቀት እየሰፋ ነው። የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው። እየሠራን ነው። እየተማርን ነው። እየታገልን ነው። እየወደቅን እንነሳለን። እንደገና እንሞክራለን። ግን... የምንፈልገው ቦታ ላይ አልደረስንም። የምንሮጥበት መንገድ ረጅም ሆነ። የምንጠብቀው ቀን እየዘገየ ሄደ። የምናደርገው ጥረት ከምናገኘው ውጤት ጋር አልተመጣጠነም። አንዳንድ ጊዜ ራሳችንን በጸጥታ እንጠይቃለን፦ "ምን ጎደለን?" ምክንያቱም እኛ ስንታገል ሌሎች ያለ ብዙ ጥረት የሚመኙትን ሁሉ ያገኛሉ። እኛ ሌሊት ስንተኛ ስለነገ እንጨነቃለን። እነሱ ግን ሌሊቱን በመዝናኛ ያሳልፋሉ። እኛ አንድ ብር ለማግኘት እንደ ብዙ እንታገላለን። እነሱ ግን በየመሸታ ቤቱ ገንዘብ ሲረጩ ያድራሉ። እኛ ያገኘነውን ትንሽ ገንዘብ ለነገ እናስቀምጣለን። እነሱ ግን ዛሬን ለመኖር የሚያወጡትን እንኳን አይቆጥሩም። እኛ አንድ ብር ለማግኘት ስንሮጥ፣ አንዳንዶች አንድ ብር እንኳን ርቆባቸው ይኖራሉ። እንደምንም አግኝተን ብንይዘውም... የዛሬው አንድ ብር የትናንቱን አንድ ብር አይደለም። ትናንት ብዙ የሚገዛው ገንዘብ፣ ዛሬ ምንም ሊገዛ አይችልም። የሕይወት ዋጋ እየጨመረ ነው። የሰው ጉልበት ግን በዚያው መጠን አይከፈልለትም። እናም አንዳንድ ጊዜ... ሕልማችን ውሸት እንደነበር እንዲሰማን ያደርገናል። እውነቱ ግን ሕልማችን ውሸት ሆኖ አይመስለኝም። ዓለም ሁሌ ፍትሐዊ ስላልሆነች ነው። ሁላችንም በአንድ መንገድ አልጀመርንም። ሁላችንም ተመሳሳይ ዕድል አልተሰጠንም። ሁላችንም አንድ ዓይነት ድጋፍ አላገኘንም። አንዱ ከሚደግፈው ቤተሰብ ይነሳል። ሌላው ግን ራሱን ብቻ ይዞ ከዜሮ ይጀምራል። አንዱ ሲወድቅ የሚያነሳው ሰው አለው። አንዳንዱ ሲወድቅ ደግሞ ራሱን ብቻ ይዞ ይነሳል። አንዱ በሩ ከመከፈቱ በፊት በሩን የሚከፍትለት ሰው አለው። ሌላው ግን በሩ ፊት ቆሞ እስኪደክመው ድረስ ይመታል። ስለዚህ ስኬትን ሁልጊዜ በጥረት ብቻ መለካት አለብን ብዬ አላምንም። ጥረት ያስፈልጋል። ግን ዕድልም አለ። ችሎታ ያስፈልጋል። ግን እድል የሚሰጥ ሁኔታም ያስፈልጋል። ጉልበት ያስፈልጋል። ግን የሚደግፍ ሰውም ያስፈልጋል። ስለዚህ ዛሬ ሕልማችሁ ላይ ስላልደረሳችሁ ራሳችሁን አትውቀሱ። ምናልባት ዘግይታችሁ እየመጣችሁ ይሆናል። ምናልባት መንገዳችሁ ከሌሎች የበለጠ ረጅም ይሆናል። ምናልባት የእናንተ ስኬት በብዙ ሌሊቶች እንቅልፍ ማጣት ውስጥ ተደብቆ ይሆናል። እናም እባካችሁ... ራሳችሁን ከሌላው ሕይወት ጋር አታወዳድሩ። ሌላው በሚያሳየው ውጤት እናንተ የምታዩት የሕይወቱን አንድ ገጽ ብቻ ነው። እናንተ ግን የራሳችሁን ሙሉ ታሪክ ታውቃላችሁ። ስንት ጊዜ እንደወደቃችሁ፣ ስንት ጊዜ እንደተሰበራችሁ፣ ስንት ጊዜ ልትተዉት አስባችሁ ግን እንደገና እንደተነሳችሁ... ይህን ሁሉ እናንተ ብቻ ታውቃላችሁ። ስለዚህ ሕልማችሁን አትተውት። ምናልባት የምትፈልጉት ሁሉ በአንድ ጊዜ አይሳካም። ምናልባት የምትመኙት ቤት አይኖራችሁም። የምትፈልጉት ሀብት አይኖራችሁም። የምታስቡት የስኬት ማማ ላይ ላትደርሱ ትችላላችሁ። ግን... ዛሬ ካላችሁበት አንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ ከቻላችሁ፣ ያ ራሱ ስኬት ነው። ስለዚህ የሕልማችሁን መጠን ሌሎች በገነቡት ዓለም አትለኩት። አንዳንዶች በብዙ ገንዘብ መካከል ብቸኛ ናቸው። እናንተ ግን በትንሽ ነገር መካከል ሰላም ሊኖራችሁ ይችላል። አንዳንዶች በየመሸታ ቤቱ ገንዘብ ይረጫሉ። እናንተ ግን አንድ ብር ለማግኘት በትጋት ትሠራላችሁ። አዎ፣ ሕይወት አንዳንድ ጊዜ ኢ_ፍትሐዊ ትመስላለች። አንዳንዶች ያለምንም ብዙ ጥረት ያገኛሉ። እናንተ ግን ለትንሽ ነገር ብዙ ዋጋ ትከፍላላችሁ። የሕይወት ትልቁ ስኬት ሁሉን ማግኘት አይደለም፤ የሚጎድለን ቢኖርም ተስፋችንን ሳንጥል መቀጠል ነው። ሕልማችን ምናልባት ከእጃችን ርቆ ይሆናል። ግን እኛ እስካለን ድረስ...ሕልሙ አልሞተም። ምናልባት የደረስንበት ትንሽ ይሆናል። ምናልባት የተሳካልን ከምንመኘው በጣም ያነሰ ይሆናል። ግን እስካሁን እየተጋደልን ነው። እስካሁን እየሞከርን ነው። እስካሁን እየኖርን ነው። እና ምናልባት... የእኛ ታላቅ ስኬት ገና አልመጣ ይሆናል። ስለዚህ ዛሬ ትንሽ ቢሆንም የምትይዙትን አትናቁ። ዛሬ አንድ ብር ቢሆንም ያላችሁን አመስግኑ። ነገ ለማብዛት ዛሬ ያላችሁን በጥበብ ያዙ። እናም ሕልማችሁን እንደ ውሸት አትቁጠሩት። ሕልማችሁ አልዋሸችሁም፤ ጊዜው ብቻ እስካሁን ስላልደረሰ ነው። ዛሬ የምትራመዱት መንገድ ረጅም ቢሆንም፣ እግራችሁ እስካለ ድረስ መንገዱ አለ። እናንተም እስካላችሁ ድረስ... ሕልማችሁም አለ። ይህ የእኔ እይታ ነው ✍️ሰናይ ምሽት🙏 ቀጣይ ሌሎች እይታዎች እንዲደርስዎት የእኔ እይታን ፔጅ Follow, Like, Share, Repost እና Copy Link በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #foryou #fyp #viral #fypシ #viralvideo
የእኔ እይታ
Region: SO
Saturday 01 August 2026 17:42:54 GMT
Music
Download
Comments
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 :
Yes, you're right, immigrants live with advantages and disadvantages, it sucks.
2026-08-03 19:55:24
0
aygiz :
እረ በጣም ትለያለህ ወዳጀ
2026-08-01 20:24:44
2
ጥሩቀን አይምሽ :
ያኔብዙነውታሪኩ🥺🥺🥺
2026-08-01 18:28:39
1
የልቤ ንጉስ :
መቼ ነዉ ያቀን
2026-08-01 17:53:45
1
Seged Dessie :
right
2026-08-03 11:48:00
0
My💔Mom😥 :
እውነትነው
2026-08-04 02:38:55
1
𝕥𝕚𝔾 𝕜𝕒𝕤𝕤𝕒𝕨 :
𝕠𝕗 𝕔𝕠𝕦𝕣𝕤𝕖😢😢😢
2026-08-03 01:33:51
1
Alex :
ኡነት ነው ግን ከመታገል ወደሗላ አለማለት ነው
2026-08-02 17:44:01
0
ጎንደሬው :
ጥሩ እይታ ነው
2026-08-02 11:50:08
0
farxiyaxashi3 :
ትክክል በተስፍ መቆየትም የህሌና እረፍት ነው ይሳካልም እደፈጣሪ ፍቃድ መርዘኞችን ባላቀቀንጂ እማይሆን የለም ታፍኖ የተቀመጠው እራሱ ፈድቶ ይወጣል ትክክል ብለሀል
2026-08-01 23:16:22
2
Ⓜ & E 💟 :
የኔ ህልም እማ ደርሰሽብኛን ነይ አይዞሽ እያለ ስቀርበው ይርቀኛን በየት እንገናኝ🥺
2026-08-01 20:15:55
2
👇🖊🔰ፈርመሽ➳ግቢ✔️❤➰🤟 :
አጀብ አጀብ
2026-08-01 18:25:56
1
Hanan123 :
🥰🥰🥰
2026-08-01 18:46:01
1
Lidya santa :
😭😭😭
2026-08-03 02:55:38
1
ሊነጋ ሲል ይጨልማል :
🙏🙏🙏
2026-08-04 09:41:29
0
Yeruqi sew aykifaw🥹🇪🇹💞 :
🥹🥹🥹
2026-08-03 17:34:14
0
Yismachew Jesus Love Me :
👏👏👏
2026-08-02 07:07:28
0
ZED ነኝ የራያዋ :
🥰🥰🥰
2026-08-04 20:33:08
0
To see more videos from user @viewer_1221, please go to the Tikwm
homepage.