@gura.ge.dynasty: ተወዳጁ የስልጥኛ ሙዚቀኛ መሀመድ ሲርጋጋ እዚ ቪድዮ ላይ ስለ ስልጥኛ ሙዚቃ አጀማመር ታሪክ ግልፅ መልስ አስቀምጧል። ከአነጋገሩ መረዳት እንደሚቻለው ማሜ መጀመሪያ ላይ የታዋቂውን ድምፃዊ መሀመድ አወልን ስም በቀጥታ ማንሳት የፈለገ አይመስልም ነበር። "አንድ የጎረቤታችን ድምፃዊ" ብሎ ለማለፍ አስቦ የነበረ ቢሆንም ቀጥሎ የተሾመ ወልዴን ስም ከጠቀሰ በኋላ ግን የህሊና ወቀሳ ይዞት በሚመስል መልኩ የመሀመድ አወልን ስም የግድ ማንሳት እንዳለበት አምኖ ስሙን ጠርቶታል። መጀመሪያ ላይ "አንድ የጎረቤታችን ድምፃዊ" የተባለው በርግጥም መሀመድ አወልን ነበር። ባህልና ጥበብ ታሪክ የአንድን ህዝብ አብሮነት አፅንተው አስተሳስረው የሚይዙ መገለጫዎች ናቸው። የአለማየሁ ወልዴ የሙዚቃ ቪድዮም ሆነ መሀመድ አወል በሁሉም የቤተጉራጌ ቋንቋ ዘዬዎች በካሴት የሰሯቸው ሙዚቃዎች ለራሳችን ህዝብ ታስበው የተሰሩ የጥበብ ውጤቶች እንጂ ለጎረቤት ተብለው የተሰሩ አልነበሩም ወደፊትም አይሆኑም። የአለማየሁ ወልዴ የሙዚቃ ቪድዮ አስተዋፅኦ እንዳለ ሆኖ በስልጥኛ ዘዬ ሙዚቃን በካሴት ቀርፆ ለህዝብ በማድረስ የመጀመሪያው ባለታሪክ ድምፃዊ መሀመድ አወል ነው። መሀመድ አወል ራሱ በቃለመጠይቁ ላይ እንዳብራራው በ1975 ዓ.ም አካባቢ በኢቲቪ ላይ እንዲተላለፉ በቪድዮ የተቀዱ ስራዎች ነበሩት። ሆኖም የመጀመሪያውና በሰፊው ህዝብ ዘንድ የደረሰው ታዋቂው የካሴት ስራው "ሲጎ ሲጎሌ" ወደ ህዝብ የደረሰው በሀበሻ አቆጣጠር 1979 ነበር። @Gura ge Dynasty @Gura ge Dynasty @Gura ge Dynasty
Gura ge Dynasty
Region: ET
Sunday 02 August 2026 15:36:27 GMT
Music
Download
Comments
nesre :
Mam Manew Alzfnm Yalw
2026-08-05 05:27:05
0
Abu mujahedin :
ማህሙድ. አህመድ. ነው. በኔ. አፍ. ስልጥኛ. አልዘፍንም. ያለው. ። መደባበቅ. አይሰራም
ብዙ. ታሪኮችን. አውቃለሁ. ።
2026-08-04 21:33:29
0
@ታሪኳ የምርወጉ :
መሀመድ አወል የጥበብ ሰው እንወድሀለን እናከብርሀለን🙏
2026-08-02 21:28:22
2
Shekur Man :
ስልጥኛ አልዘፍንም ያለው በጉራጌ አርቲስት ዋቢ አብደለረህማን ነው
2026-08-02 21:33:33
0
𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓶𝓮𝓷𝓪𝓷 :
ታላቁ መሀመድ አወል💪💪🥰🥰
2026-08-02 19:56:16
4
Ebro mana :
መሀመድ አዋል እንከንም ዋደድኩክ
2026-08-04 04:02:52
0
jm 109 :
ማህሙድ አህመድ ነው አልዘፍንም ያለው
2026-08-03 18:24:24
0
ነጃ ወራቤዉ :
የሀ/ሻሚል ሁልሰቦ ግጥም ነበር
2026-08-03 12:16:40
1
fibula :
እና ምን እናድርጋችሁ በቃ ተለያየን እኮ 🤔 እየመጣችሁ አትነዛነዙብን !
2026-08-03 19:44:26
0
maryamin :
manew
2026-08-03 04:14:35
0
ነጃ ዙልፋ🤐19,96 ሸገር :
❤👌❤❤👌
2026-08-03 19:58:37
1
Bezawit :
🙏🏻🙏🏻🙏🏻
2026-08-02 16:57:22
2
Gura ge Dynasty :
@peace የመሀመድ አወል ታሪካዊ የጥበብ ስራዎች ስለላክልኝ እጄግ አድርጌ አመሰግናለው ወንድሜ 🙏🏿
2026-08-02 17:34:49
2
Mesay Fikadu :
🙏🙏🙏
2026-08-03 05:49:11
1
tofik አርሤ :
🥰🥰🥰
2026-08-05 04:27:51
0
Abdulfeta kemal Rahman :
🥰🥰🥰
2026-08-03 20:48:46
0
Amiza Alla :
😂😂😂
2026-08-05 16:18:20
0
@Hayatu122 :
🥰🥰🥰
2026-08-06 10:04:08
0
To see more videos from user @gura.ge.dynasty, please go to the Tikwm
homepage.