@musictube369: ቀረሁኝ ተክዤ 🤕 ✍️ በነጮቹ 1997 ነበር አሜሪካን ላይ የግጥም እናት የሆነቺው አለምፀሀይ ወዳጆ፣እራሱ ቴዲ ታደሰ፣ አበጋዝ ሺሆታ እና የቤዝ ጊታር ሊቆቹ ሄኖክ እና ፍሲል ከሌላኛው ጀግና ድራመር ሳምሶን ጁፋር ከባህር ማዶ ከተቀላቀሏቸው እጅግ የተከበሩ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና ሙዚቀኞች ጋር በመሆን በAIT Recordsሱ ባለሟል አማን አድነው አዘጋጅነት ከአልበሙ ሽፋን ጀምሮ ትዝታን የተሸከመውን የኢትዮጵያን ሙዚቃ አንድ እርምጃ ያራመደ ረቀቅ ያለ አንድ አልበም ሊሰሩ ተገናኙ አለምፀሀይ ወዳጆ የተነበየች ቢሆንም ቅሉ የክፍለ ዘመኑን ምርጡ አልበም እንደሚሆን ግን አልጠበቁም ነበረ ለአልበሙ ለዘጠኝ ሰራዎች አለምፀሀይ ወዳጆ ግጥም ሰጠች የ8ቱን መዚቃ ዜማዎች እራሱ ቴዲ ሰራቸው አንዷን "በጉዴ እወጣና"ን ዮናስ ሙላቱ ተራቀቀበት የተቀረቺውን አንድ ሙዚቃ "አልቦ"ን እራሱ ቴዲ በብዕሩ ከትቧት ዜማዋን ለታሪኩ ብዙዓለም ሰጣት በስራው የማይነጥፈው የዘመናዊ ሙዚቃ ቁንጮ የሆነው ትውልደ ጃፓናዊው ታላቁ የኢትዮጵያ ባለሟል አበጋዙ በተባረከ እጆቹ አቀናበራቸው አማን አድነው ከፊት ቀደመ እኔ ፕሮዲውስ አደርገዋለው አለ እውነት ድንቅ ጥምረት ለመሆን ቻለ በዚህ ጥምረትም የኢትዮጲያ ሙዚቃ ትልቁ ክስተት "ዝምታ" አልበም ተወለደ🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ዘመኑን በመቅደሙ በወቅቱ ጆሮ ሳይሰጠው እንደዘበት ሳይሰማ ችላ ተብሎ የነበረው ይህ አልበም ጊዜን በጊዜ ላይ ሲረማመድ እንደ ወይን እየጣፈጠ ከንግስናው ማማ መቀመጡ ላይቀር ለቴዲ ታደሰ የኑሮ መዛባት ምክንያት ይሆናል ብሎ የጠበቀ አልነበረም 😥 ግን የፈጣሪ ፍቃድ ሆነና ያለታሰበው ነገር ሁሉ ተከሰተ የቴዲ ታደሰ የትዳሩ ፉቺ ዋነኛ ሰበብ ሆነበት ያሳዝናል የቴዲ ታደሰ ማናጀሩ የነበረችው ሚስቱ አሜሪካ ነው መኖር ምፈልገው አለች እሱ ደግሞ እዚው ሀገሩ ላይ … ብቻ ፍቅር በለጠና የሚወዳት ሀገሩን "እምዬ ኢትዮጲያ" የሚላት ሀገሩን ትቶ እሱም ኑሮውን በአሜሪካ አደረገ ግን አልበሙን ሊሰማለት አልቻለም ቴዲ ብር አስፈልጎት አሳታሚዎቹ ጋር እየደወለ እንዴት ሆነ ይላቸዋል እነሱም አሪፍ አልበም ነው ግን አልተሸጠም ይሉታል ከማናጀር ባለቤቱ ጋር አለመግባባት ይፈጠራል ከዛም ይጣላሉ ነብሳቸውን ይማርና የክብር ዶ/ር አሊ ቢራ እና ሌላኛው አንጋፋው ድምፃዊ የትዝታው ንጉስ የክብር ዶ/ር መሀሙድ አህመድ ሽምግልና ሄደው ያስታርቋቸዋል ታርቀው የትዳር ኑሮአቸውን ቀጠሉ ቢሆንም ግን በድጋሚ ተጣሉ ባለቤቱም በአሜሪካ ፍርድ ቤት ቀርባ ፍቺ አደረገች ጭራሽ ልጆቼ ላይ እንዳይደርስ ከእኔ እና ከልጆቼ በ500 ሜትር ይራቅልኝ የሚል ዘመናዊ ክስ አስገባች ፍርድ ቤቱም ክሷን ተቀበላት… almost ቴዲ አጅጉን ልቡ ተሰበረ በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ማደር ጀመረ ኑሮ ተዛባ ይሄ በኢትዮጲያ ደረጃ የምንግዜውም ምርጡ አልበም የተባለለት እያንዳንዱን ሰው በሚያስማማ ደረጃ ቁጥር አንዱ አልበም ዝምታ ነው ያሉለት ለቴዲ በሽታ ይዞበት መጣ🥺 ለኛ ለወዳጆቹ ደግሞ የሙዚቃ ጥም ቆራጭ ሲሆን ለሱ እያንዳንዱ ሙዚቃ ቁስሉን የሚመዘመዙ ትዝታዎች ሆኑበት አልበሙን ሰጥቶን እራሱን አጣናው ከዚህ በላይ ምን ህመም አለ😥 📌እጅግ የምንወደው ቴዲ ታደሰ አሁን ላይ ጤናውም የተመለሰ በጥሩ ሁኔታ እንደሆነ ሰምተናል🙏 ምንም እንኳ "መስከረም" ሲል የሰየመውን እንደ አደይአበባ እንደ መስከረም የፈካ ዜና የያዘ ብስራት ቢያሰማንም ከምንም በላይ እሱን በጤና ማየት ለኛ ለቴዲ ወዳጆች አድናቂዎች ከአስርም አልበም ብስራት ነውና እጅጉን ደስ ብሎናል🥰 እኔም ለዛሬ ከዚህ አልበም ላይ ከነፍስ የሚያላውሰውን "ቀረሁኝ ተክዤ"ን ጋብዤያቹ ከዚህ ታሪከ ብዙ ከሆነው አልበም ጀርባ ያለውን አሳዛኝ ታሪክ በጥቂቱ ከተለያዩ ቦታዎች ያገኘሁትን መረጃ ለእናንተ እንዲሆን አድርጌ በዚህ መልኩ አጋርቼያቹ ረጅም ዕድሜን ከጤና ጋር እጅግ ለማከብረው ቴዎድሮስ ታደሰ እየተመኘው ይሄን ውብ ሙዚቃ ጋብዤያቹ አበቃሁ🙏🙏 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #ቴዎድሮስታደሰ #ቀረሁኝተክዤ #ethiopianmusic #musictube369
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Region: ET
Sunday 02 August 2026 18:08:24 GMT
Music
Download
Comments
JOE :
The song that made me fall in love with Teddy Tadesse🧡
2026-08-03 20:39:17
3
Mihretab :
don't do this to me bro
2026-08-03 18:42:21
1
jerry alex :
my weakness teddye🥰🥰🥰
2026-08-04 19:04:03
0
Helil Nur :
music name
2026-08-04 12:40:41
3
Mekdelon :
your dedication on music's are extraordinary❤️. thankyou for the story telling captions beside the music.
2026-08-02 18:38:12
8
bonbe :
በቃ ትችላለህ ቃላት የለኝም !
2026-08-04 10:55:53
1
𝖙𝖍𝖊 𝙶𝚞𝚗𝚗𝚎𝚛𝚜💨 :
teleyalh nw mileh keberlegn 🙌
2026-08-03 16:38:04
1
AB በቸርነቱ :
ሙዚቃ ተከፈተ 🎶🎶🎶
2026-08-03 16:58:52
6
Hanna ማርያም :
የልቡን ላይሞላ 😢
2026-08-03 13:14:46
4
Slow-Burn-B E K 🧊 :
2026-08-03 17:40:04
1
Robi zemikael :
ቴዲሻ 😍😍😍
2026-08-04 14:26:42
2
JOE :
This Song
2026-08-03 20:36:23
1
Elijah メ𝟶 :
ababi eski ye bzuayehun "wey edaye " 🙏🏾🔥
2026-08-03 18:13:49
1
Abrish :
አረ ዜማው የአበበ ብርሃኔ ነው
2026-08-02 20:25:37
0
Genetu Gedlie :
አልቦ ከሚለው ዘፈን ወጭ የዘጠኙ ዘፈን ግጥም ደራሲ አለም ፀሐይ ወዳጆ ነች
2026-08-03 07:13:39
2
Ela mobile :
[Sticker]
2026-08-02 20:39:14
1
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.