@hewi.hewi298: ጀብደኛው 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ለተከታታይ 6ወራት ያሰለጠናቸውን የኮማንዶ ሰራዊት አስመርቋል። በምርቃ ስነ-ስርዓቱ የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት አስተላልፏል‼️ ሐምሌ26/2018 ዓ.ም =================== √ጤና ይስጥልኝ እንዴት ሰነበታችሁ? በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ፥ ቴዎድሮስ እዝ፥ 206ኛ ኮር፥ 34ኛ ክፍለጦር የመጀመሪያ ዙር ኮማንዶ ተመራቂዎች ከስድስት ወራት ጠንካራ ወታደራዊ ስልጠና በኋላ ለምርቃት በመብቃታችሁ እንኳን ለዚህ ቀን አበቃችሁ፥እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። እናንተ የምትመረቁበት ዛሬ ሃምሌ 26 ቀን በአማራ የህልውና ትግል ውስጥ እጅግ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀኖች አንዱ ነው። ሃምሌ 26-2015 አም የባሶ ሊበን፥ የደብረ ኤልያስ፥ የአዋበል፥ የአነደድ፥ የጎዛመንና የደብረማርቆስ ጀግኖች በተቀናጄ አኳኋን ተወርውረው ደብረማርቆስ ከተማን በቁጥጥር ስር በማድረግ የጠላትን መዋቅር ፍርስርሱን ያወጡበት ቀን ነው። የፋኖው የተደራጄ የህልውና ትግል ድፍን ሶስት አመት ሆኖታል።በነዚህ ሶስት አመታት ውስጥ ለቁጥር የሚታክቱ አውደ ውጊያዎች ተከናውነዋል፥ ቃላት የማይገልፃቸው ጀግንነቶች ታይተዋል፥ ብዙ ግዙፍ ድሎች ተመዝግበዋል። ፋኖ በመላው አማራ ከሌሎች የጠላት ታጣቂዎች ውጭ የጠላትን 10 ሙሉ እዝ መክቶ ለወረራ በመጣበት ጉልበቱ እያንበረከከው ይገኛል።ይህ የታሪክ ገፆች የማያውቁት አዲስ ገድል ነው። በአማራ ልጆች ለአለም የታዬ አዲስ ክስተት ነው። በነዚህ አመታት አንድም ቀን ሳንዋጋ አንድም ቀን ሳናሰለጥን፥ አንድም ቀን ሳናደራጅ፥ አንድም ቀን ሳናስታጥቅ ውለን አናውቅም። ይህ እስከ ድላችን የሚቀጥል የቀን ተቀን ስራች ይሆናል። ጓዶች ሆይ፦በአማራ ህዝብ ማህበረሰባዊ ታሪክ፥ በኢትዮጲያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ፥ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ ወሳኝ የታሪክ ምእራፍ ላይ እንገኛለን። በዚህ ምእራፍ መቀመጥ አይቻልም። በዚህ ምእራፍ አይንን ለአንድ ደቂቃ እንኳን መክደን አይቻልም። በዚህ ምእራፍ መሳሳት አይቻልም። መቀመጥም፥ መተኛትም መሳሳትም ዳግሞ እድልና ይግባኝ የሌላቸው መጥፊያዎች ሆነዋልና።ስለዚህ ለወርቃማው አላማችን ሌት ተቀን እንሰራለን፥ በስሌት እንጓዛለን።እናሸንፋለን።ቢስማርክ እንዳለው "እውነት በያዝነው መሳሪያ የተኩስ ርቀት ውስጥ ትኖራለች"ና በፍጥነት ማሸነፍ ስላለብን እንበርታ።በድል እንገናኝ። ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ! አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ሃምሌ 26-2018 አም ©አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር!

(እውነት የህሊና ህግ ናት)
(እውነት የህሊና ህግ ናት)
Open In TikTok:
Region: QA
Sunday 02 August 2026 18:20:03 GMT
727
155
11
54

Music

Download

Comments

emushamtataw
የአማራ (Fano)🦅 :
2026-08-02 18:23:01
1
binyam0673
ashenafi :
2026-08-02 19:59:41
1
bellll6991
ዋርካው ጥላየ :
🥰🥰🥰
2026-08-03 12:36:20
0
yohanis12dig
yohanis dig :
🥰🥰🥰
2026-08-03 04:37:12
1
aman.setegne
Aman setegne :
🥰🥰🥰
2026-08-03 12:32:29
0
user901283267852662
(ባላገሯ👸💙) :
🥰🥰🥰💪💪💪
2026-08-02 18:21:52
1
gesetdejen
geset dejen :
🥰🥰🥰
2026-08-03 07:18:56
0
user15949861355112
user15949861355112 :
🥰🥰🥰
2026-08-03 03:45:15
0
helen.atopia
ለአግዚአብሔርቂርቆሰማፅቱ ❤️🙏 :
❤️❤️❤️❤️❤️💪💪💪💪
2026-08-02 18:48:13
1
user5361901600218
bene geto :
💪💪💪
2026-08-03 05:07:38
1
To see more videos from user @hewi.hewi298, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About