@keleb_enemamar: #ኢትዮጵያዊቷ_ቅድስት_መስቀል_ክብራ ሐምሌ ሀያ ሰባት በዚህች ቀን ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት መስቀል ክብራ ዕረፍቷ ነው፡፡ ይህችም ቅድስት የቅዱስ ላሊበላ ሚስት ስትሆን አባቷ ስምዖን እናቷ ሶፍያ ሲባሉ የትውልድ ሀገሯ ወሎ ላስታ ቡግና ነው፡፡ ከታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ከቅዱስ ላሊበላም ደገኛውን ይትባረክን ወልዳለች፡፡ ቅዱስ ላሊበላን እና ቅድስት መስቀል ክብራን ሁለቱ እንዲጋቡ ያዘዛቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ዲዛኖችና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር ከመለሰው በኃላ ድጋሚ ተገልጦለት "እንዳንተ የተመረጠች ናት እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል፡፡ ቅዱስ ላሊበላ አስራ አንዱን እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል፡፡ ቅድስት መስቀል ክብራን ወደ ትግራይ እየመራ የወሰዳት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እርሷን በትግራይ ቅዱስ ሚካኤል እንዲጠብቃት ከተዋት በኃላ ቅዱስ ላሊበላን ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ መንግሥተ ሰማያት አውጥቶታል፡፡ ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ሆና መልአኩ እየጠበቃት ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከሠላሳ ስስድስቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል፡፡ ይህችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች፡፡ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዱጠመቁ አድርጋለች፡፡ በቋጥኝ ድንጋይ ላይ በተመሰረተችው በትግራይ በሽረ እንዳሥላሴ ምዕራባዊ ዞባ መደባይ ታብር በምትገኘው ገዳሟ ብዙ ተጋድሎ ከተጋደለች በኋላ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦላት ስሟን ለጠራ፣ ዝክሯን ለዘከረ፣ ቤተክርስቲያኗን ላሳነጸና በጸሎቷና ምልጃዋ ለተማጸነ እስከ አስራ ሰባት ትውልድ እንደሚምርላት ቃልኪዳን ሰጥቷት ሐምሌ ሀያ ሰባት ቀን ዐርፋለች። #ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!እኛንም በእናታችን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎትና በቅድስት መስቀል ክብራ እንዲሁም በከበሩ ቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ጸሎት ይማረን!በረከታቸውና ረድኤታቸው ሀገራችንን ኢትዮጵያን እንዲሁም ቤተክርስቲናችንን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅልን! በሰላምና በጤና ወርኃ ክለምቱን እንደአስጀመረን አስፈጽሞ ለብርሃነ መስቀሉ ያድርሰን! #አሜን_ወአሜን_ለይኩን_ለይኩን!!!
ስለ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ከልብ እንማማር
Region: ET
Monday 03 August 2026 09:16:15 GMT
Music
Download
Comments
Buruk :
ሊቁ ጌች ቃለሕዎት ያሠማልን
2026-08-03 17:41:00
1
Lidia2227 :
@ጌታቸዉ ዘቦሌ
2026-08-03 09:42:21
1
user8137136302581 :
🥰🥰🥰
2026-08-03 10:56:21
1
To see more videos from user @keleb_enemamar, please go to the Tikwm
homepage.