@gura.ge.dynasty: በዝምድና ቆራጮች አደጋ የወደቀበት የስልጢ እና የቤተ ጉራጌዎች የታሪክና የደም ትስስር ከኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት በፊት በነበረው ዘመን ማንም እንደሚያውቀው እንደ ውልባራግ፣ አዘርነት፣ ዳሎቻ፣ አሊቾ ወረሮ ያሉ አካባቢያዊ ስያሜዎች ነበሩ በዋናነት የሚታወቁት። አንዱ «ውልባራግ ነኝ»፣ ሌላው «አዘርነት ነኝ» ወይም «አሊቾ ወረሮ ነኝ» ይላል... በተረፈ ግን እንደ ማንነት የሚጠቀሰው በጎሳ ደረጃ የሚታወቅበት ጉራጌያዊ የጎሳ ዘሩን ነበር። ይህ በታሪክ ሰነዶችም ጭምር የተደገፈ እውነት ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ (ከአጼ ሚኒሊክ Expansion) በፊት በጣሊያን ጆግራፊ ማህበር በኩል ከጓደኛው አንቶኒዮ ቼኪ ጋር በመሆን የጉራጌን ምድር የጎበኘው ጣሊያናዊው ዶ/ር ጆቫኒ ቺያሪኒ (Dr. Giovanni Chiarini) ከጉዞው መልስ ሮም ከተማ ውስጥ ባታተመው "Da Zeila alle frontiere del Caffa" (ከዘይላ እስከ ከፋ ድንበር) በተሰኘው ታዋቂ መፅሀፉ ላይ ስለ ጉራጌ ህዝብ እጅግ ውድ የሆኑ የታሪክ መረጃዎችን አስፍሯል። ከዚ መሀል ስለ ጉራጌ ጎሳዎች የጠቀሰው ይገኝበታል "ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነው ጉራጌዎች የሞህር፣ የእዣ፣ የቸሃ፣ የጌቶ፣ የአዘርነት፣ የእኖር፣ የጎማሮ እና የኡልባረግ ጎሳዎች ናቸው። የተለመደው አለባበሳቸው ቅባት የነካው (ያደፈ የሚመስል) ሻማ ሱሪ እና በወገብ ላይ በተመሳሳይ ቀለም ክብ ማሰሪያ የሚታሰር ለየት ያለ ንድፍ ያለው ሰማያዊ የጥጥ ቀሚስ ያካትታል። ይህንን ልብስ የሚያገኙት ማዕከላቸውን ምፅዋ ካደረጉ ነጋዴዎች ዕቃዎችን ከሚያስገቡበት ከጅማ ነው..." (Da Zeila alle frontiere del Caffa) ከጣሊያናውያን አሳሾች በተጨማሪ የጎጎት ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ የስልጢኛ ዘዬ ተናጋሪ ስለሆነው ቤተ-ጉራጌ አካባቢያዊ ማንነት ሲያስቀምጥ ""ስልጢ በሚል ስያሜ የሚጠራው ሕዝብ የስልጢ፣ የአዘርነት በርበሬ፣ የመልጋ፣ የወለኔ ገደባኖ እና የአሊቾ ወረሮ ሕዝብን" የሚያካትት እንደነበር ይገልፃል። በታሪክ «ስልጤ» የሚለው ስያሜ ዛሬ የያዘውን አካባቢ የሁሉንም ማንነት በሚገልጽ መልኩ አይታወቅም። የጉራጌ ጎሳዎች የሚኖሩባቸውን እነዚ አካባቢዎች የተቀረው ቤተ-ጉራጌ ጠቅልሎ "ስልጢ ቤተ-ጉራጌ" ብሎ ነበር የሚጠራቸው። በተረፈ «ስልጢ» የሐጅ አልዬ አንዱ ልጅ "ገን ስልጢ" የተባለውን ጎሳ ብቻ የሚገልጽ መጠሪያ እንደነበር ለማንም ግልጽ ነው። ዛሬም ቢሆን የተለወጠ እውነት የለም። ከየት እና መቼ መጡ የሚለው እናቆየውና ሃጅ አልዬ ወደ ደቡብ ሲፈልሱ ብቻቸውን አልነበሩም። ወንድሞቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን አስከተው እንጂ። የጎጎት ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚገልጸው ከሃጅ አልዬ ጋር አብረው መጥተው በጉራጌ ምድር በአራቱም አቅጣጫ ተበትነው የሰፈሩት ታዋቂ አባቶች መካከል 1ኛ. ሼህ አሊኑር 2ኛ. ሼህ ነስረላ 3ኛ. ሼህ በርከሌ 4ኛ. ሼህ ዑስማን 5ኛ. ሼህ ረዲ 6ኛ. ሼህ መልጋጊሎ 7ኛ. አህመደል በርበር 8ኛ. ኢማም ሲዲ 9ኛ. እናመኪ 10ኛ. በሸህየ / ሼህ በሽር 11ኛ. ለሞ 12ኛ. ኑር የሱፍ 13ኛ. ሠይድ ከቢር ሃሚድ 14ኛ. ሃጂ ጃፋር ... እና ሌሎችም" ይጠቀሳሉ። እነዚህ አባቶች በአንድ ቦታ ብቻ አልተወሰኑም። በጉራጌ ምድር ነባር ሕዝቦች ጋር እየተዋለዱ መሬት እያሰፉ በአራቱም አቅጣጫ ተበታተኑ። ለምሳሌ ሐጅ አልዩ ኡምናን ሼክ መለጋ ጊሱ ኡልባራግ ሼህ በርከሌ መስቃንና ገደባኖ ሼህ ኡስማን መስቃን፣ ሼህ አሊኑር እና ሼህ ነስረላ ገደባኖ አህመደል በርበረ ሙጎ አካባቢ ሰፈሩ። እነዚህ እና ሌሎች እዚ ያልተጠቀሱ ቀደምት አባቶቻችን ከዘቢዳር ተራራ በላይና በታች ሆነው በቸሃ፣ እዣ፣ ጌቶ፣ ጉመር፣ ስልጢ፣ እኖር ኤነር መገር ፣ መስቃን፣ ወለኔ ሶዶ-ክስታኔ ቤተ-ጉራጌ ላይ የወለዷቸው ልጆች ዛሬ ላይ የሚበዙት አውራ ጎሳዎች ሆነው ይገኛሉ። ዛሬ «ስልጤ ዞን» በሚባለው አካባቢ ያሉት የሐጅ አልዬ ልጅ የ«ገን ስልጢ» ዘሮች ብቻ አይደሉም። በተመሳሳይ መልኩ በወለኔ፣ በሰባት ቤት ጉራጌ፣ በሶዶ እና በመስቃን የሐጅ አልዬ እና የወንድሞቹ ልጆች በስፋት ይኖራሉ። ከዘቢዳር ተራራ በላይ ከሃጅ አልዬ የሚዛመዱ ትውልዶች ዛሬ አውራ ጎሳ ሆነው ከሚገኙባቸው ቤተ ጉራጌዎች በጥቂቱ፡ በቸሃ -ሞገመነ በጎማረ -ኢነቋምት በእዣ -ሸራር በጌቶ - በረስየ እና ሌሎችም ይገኙበታል። በጣሊያናውያን የታሪክ ሰነድ (Da Zeila alle frontiere del Caffa) ላይም ሆነ በ«ጎጎት» ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የስልጢ ጎሳዎች ማንነታቸውና ደማቸው ከቤተ-ጉራጌ ወገን እንደሆነ ነው። ከሃያ ዓመታት በፊት ጥቂት በስልጢ ስም የተደራጁ «ዝምድና ቆራጮች» እስኪነሱ ድረስ፣ ከዘቢዳር ተራራ በስተቀር በሁለቱም በኩል ያሉትን የጉራጌ ጎሳዎች የሚለያያቸው ምንም አይነት ጉዳይ አልነበረም። በጉራጌነታቸው ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ ሳይኖርባቸው ሃዘኑም ደስታውንም እየተጋሩ ጦርነቱንም በጋራ እየመከቱ ድሉን በአንድነት እያከበሩ፤ እስከ ዘጠናዎቹ ድረስ በአብሮነት ነበር ዝምድናቸውን ጠብቀው የዘለቁት። «...በምድር ላይ ልታጠፉ፣ ዝምድናዎቻችሁንም ልትቆራርጡ ተቃረባችሁን? እነዚያ አላህ የረገማቸው፣ መስሚያዎቻቸውንም ያደነቆራቸው፣ አይኖቻቸውንም ያወረራቸው ናቸው።» (ሱረቱ ሙሀመድ 47) «እነዚያም የአላህን ቃል ኪዳን ከአረጋገጡት በኋላ የሚያፈርሱ፣ አላህም እንዲቀጠል ያዘዘውን ነገር (ዝምድናን) የሚቆርጡ፣ በምድርም ላይ የሚያጠፉ እነዚያ ለእነሱ እርግማን አላቸው። ለእነሱም መጥፎ መኖሪያ (ገሀነም)አላቸው።» (ሱረቱ አር-ረዕድ 13)” Gurage Land Cc Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል @Gura ge Dynasty @Gura ge Dynasty @Gura ge Dynasty
Gura ge Dynasty
Region: ET
Tuesday 04 August 2026 11:46:49 GMT
Music
Download
Comments
𝙎𝙄𝙇𝙏𝙀𝙔𝘼✸ :
በጣም ይቅርታ ነገር ግን አንድ አደለንም
2026-08-13 04:46:09
4
amuri :
በዚህም መጣህ አረ ተፋታን😁
2026-08-10 16:53:57
2
A.kaf.enatu.nafaቂ :
ልክነህ አንዱም ምስክር የኔ ባለቤት
2026-09-08 21:07:32
0
Gura ge Dynasty :
“ጎጎት የጉራጌ ብሄረሰብ ታሪክ ባህልና ቋንቋ” Page 54
“Da Zeila alle frontiere del Caffa” Page 60
2026-08-04 13:07:03
1
🇫🇦🇫 :
ጊዜ እንደፈቀደው ይሁን አንድነቱን በ ፖለቲካ ጠላልፈው እንዳይነሳ አድርገው ጥለውታል
2026-08-18 05:28:38
3
♧ :
what is the ethincty of haji aliye? im confused
2026-09-02 12:39:31
0
AB ايمن :
ማሻአላህ የመጨረሻ መደምደምያ ማስረጃህ
2026-08-16 04:31:44
0
ቺቻሪቶ 🌙 :
ብዙ ውሸትና
2026-08-18 08:25:14
0
M...R...F :
ብዙ ጉራጌዎች አሉ ብዙ ስልጤዎችን ያገቡ የተዋለዱ ለዚህ ማሳያ በሩቅም በቅርብም አይቻለው ይበልጥ ደግሞ የኔ የራሴ ቤተሠብም ምስክር ።።።
በመጨረሻ "ከቁርአን " መጥቀስህ ደግሞ በጣም እንዳከብርህ አደረገኝ👍👍🙏🙏🙏
2026-08-15 07:19:10
0
yasin3837151725695 :
ል
2026-08-10 09:13:55
1
Dr.Nesre D.Ahmed :
እስኪ የቀረውም ጉራጌ በሰላም ይኑር ; ለኛ አዲስ የሌለ ስያሜ ቢሰጠን ወደንዋል ;ቀቤና ,ወለኔ ,መስቃን ህዝቦች ላይ ምን እየታደረጋ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው 😴 እዛው ሰላም ሁኑ 👋👋👋
2026-08-15 18:21:42
4
My inner Gurage :
የሚቆረጥ ከሆነ እኮ ቀድሞም ዝምድና አይደለም። ብቻ ምን አለፋህ ስልጤም ሆነ ወለኔም ማንነቴ አይደለም ካለ አለ ነው።
2026-08-24 20:50:04
0
FAHMI :
silte= Arab
2026-08-24 03:09:18
0
Gerad Adoli :
ውሸት። ስልጤ ማለት ሀድያ ወይም እስላም ነው። ቢጋቡም የተለያዩ ብሄሮች ናቸው።
2026-08-15 15:26:51
0
moges :
🙏
2026-08-04 18:59:06
1
😻😻 :
😂😁😁
2026-08-10 09:17:39
0
To see more videos from user @gura.ge.dynasty, please go to the Tikwm
homepage.