@selihom.eye.clini: 🎙️ "የዓይን መቅላት ሁልጊዜ ቀላል ችግር አይደለም! አንዳንድ ጊዜ እይታዎን ሊያሳጣ የሚችል የኮርኒያ በሽታ ሊሆን ይችላል።" Keratitis ማለት የዓይን ፊት ለፊት ያለው ግልጽ ሽፋን የሆነው ኮርኒያ ሲያብጥ ወይም ሲያዝ የሚፈጠር በሽታ ነው። ይህ በባክቴሪያ፣ ቫይረስ፣ ፈንገስ ወይም በዓይን ጉዳት ሊከሰት ይችላል። በተለይ ኮንታክት ሌንስን በአግባቡ የማይጠቀሙ ሰዎች ለዚህ በሽታ የበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ዋና ምልክቶቹ የዓይን ህመም፣ መቅላት፣ ብርሃንን ማየት መቸገር፣ ብዙ እንባ መፍሰስ፣ እይታ መደበዝዘት እና ዓይን ውስጥ አንድ ነገር ያለ የሚመስል ስሜት ናቸው። ⚠️ እነዚህ ምልክቶች ካሉዎት በራስዎ የዓይን ጠብታ አይጠቀሙ። የተሳሳተ ሕክምና ችግሩን ሊያባብስ እና ኮርኒያው ላይ ጠባሳ በማስቀረት እይታን ሊጎዳ ይችላል። 👁️ የዓይን ህመምን ችላ አይበሉ። ፈጥነው የዓይን ሐኪምን ያማክሩ። SELIHOM EYE CLINIC "የዓይንዎ ጤና ቅድሚያችን ነው።"
selihom eye clinic
Region: ET
Wednesday 05 August 2026 11:23:38 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @selihom.eye.clini, please go to the Tikwm
homepage.