@wasumohammed: የፍ/ቤቱ ውሳኔዎች ኢ-ሕገመንግሥታዊ ናቸው ተባለ‼ 📌የፌዴሬሽን ም/ቤት የጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን ኢ-ሕገመንግሥታዊ ሲል ሻረ 📌 "በሌላ ሰው መሬት ላይ የተገነባ ቤት የመሬቱን ባለይዞታ ባለቤት አያደርግም" የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ናቸው ሲል ሽሯቸዋል። በዚህም መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሠራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል" በማለት በመዝገብ ቁጥር 30101 እና 36638 ላይ የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረኑ ናቸው በማለት ውድቅ አድርጎታል። የምክር ቤቱ ውሳኔ እንደሚያመላክተው፤ በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ የመሆን እና በመሬቱ የመጠቀም ሕገ-መንግሥታዊ መብቱ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው። በዚህም መሠረት አንድ ሰው የሌላ ሕጋዊ ባለይዞታ በሆነ መሬት ላይ፥ ባለይዞታው ሳይቃወመው እንኳን ቢገነባ የመሬቱ ባለይዞታነትም ሆነ የቤቱ ሙሉ ባለሃብትነት ወደ ቤቱ ሠሪ አይተላለፍም። የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) "በመሬት ላይ ንብረት ያፈራ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ የሚሠራው ሕጋዊ የመሬት ባለይዞታነት መብት ላለው አካል እንጂ፣ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለ ሕጋዊ መሠረት ንብረት ለገነባ ሰው የቤት ባለቤትነት መብት ለመስጠት እንዳልሆነ ምክር ቤቱ አብራርቷል። በመሆኑም ባለይዞታው ሳይቃወም በይዞታው ላይ ቤት የሠራ ሰው የሚኖረው ሕገ-መንግሥታዊ መብት፣ ለግንባታው ያወጣውን ወጪ ወይም ግምት ከመሬቱ ባለይዞታ የመጠየቅ መብት ብቻ መሆኑ ተጠቅሷል። video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 #WasuMohammed #tiktok #foryoupage #breakingnews #foryou
Wasu Mohammed 📌
Region: ET
Wednesday 05 August 2026 14:35:39 GMT
Music
Download
Comments
user7144452489611 :
lik new
2026-08-05 15:59:53
0
Chorrie Sedoma :
"አንድ ግለሰብ ወደ ሌላ ባለ ይዞታ መሬት ሄዶ ቤት ቢሠራ ያ ቤት የዚያ ባለ ይዞታ እንጂ የዚኸኛው ቤቱን የሠራው ግለሰብ ሊሆን አይችልም" ማለት ምን ማለት ነው?
ወደ ሌላ ባለ ይዞታ መሬት ሄዶ ቤት የሠራው ግለሰብ ይዞታውን ገዝቶ ወይስ ሳይገዛ ዝም ብሎ ሄዶ ነው ቤት የሠራው? ዜናው ግልፅ አይደለም !
2026-08-05 16:00:22
6
Sendw Eshetu :
በደሴ ከተማ ልዪ ቦታው ጀሜ የሠይድ ሙሳ ይዞታ የነበር በመሀበር ተደራጂት በ2016..አም 500ሠው አንድ እጣ 40000.አራት መቶሺብር አዋጥተን ከፍለን በድምሩ 250000000.ሁለት መቶ ሀምሳ ሚሊን ተብልት ቀረን ወጀለኞቹን አሳሥርን ፍርድ ቤቶቹ ሙሥና ብልተው ለቀቋቸው ለመንግሥት ጥሪ አቅርብልን የመንግሥት ያለህ ህዝብ ተሠርፎ ቀረ
2026-08-05 18:31:48
2
ማራ ክብሮም ማራ :
😅😆😁😁😆😂🤣አስቂኝ የህግ ትርጉም
2026-08-06 14:05:09
0
hope@fakelife973 :
ወንድም ዋሱ እናመሰግናለን
2026-08-05 15:32:34
1
ፍትህ አልባ ዘመን ድካም ብቻ :
ዋስየ እናመሰግናለን
2026-08-06 06:56:02
0
ማሜ :
ይሄ ገዝቶ ወይስ በምን ምክናያት ሆኖ የሰራዉ የሰዉ ቤት የባለይዞታዉ ይሆናል?
2026-08-06 03:16:52
0
ALI KEDIR :
አዲስ ሁለተኛ ጦርነት
2026-08-05 18:44:44
0
Y :
Chaos !
2026-08-05 22:34:30
0
ኢትዮ ፋሚሊ Tube :
ህዶ ማለት ገስቶ ለማለት ነው
2026-08-05 15:25:05
0
A B :
በትክክል
2026-08-06 00:44:50
0
fefewmamo5 :
እናመሰግናለን
2026-08-06 03:43:34
0
Sendw Eshetu :
ወንድም ዋሡ ሥለፍርድ ቤቶች ያቀረብከው እውነትነው
2026-08-05 18:24:57
0
user5575457309561 :
ተገቢ ማሻሻያ ነዉ
2026-08-06 16:23:55
0
ዘለአለም መንግስቱ :
❤
2026-08-06 09:29:30
0
Taye :
🥰🥰🥰
2026-08-05 21:28:05
0
jimma :
🥰🥰🥰
2026-08-06 08:22:59
0
Ali King👑 :
🥰🥰🥰
2026-08-06 05:09:17
0
Seid Ahmad :
💙💙💙
2026-08-06 00:38:11
0
መኖር በእናት ሆድ ውሥጥ :
🥰🥰🥰
2026-08-06 08:32:03
0
user6034474091380 :
😅😅😅
2026-08-05 21:00:52
0
Kassa Mohammad :
🥰🥰🥰
2026-08-05 18:25:54
0
Mohammed :
🥰🥰🥰
2026-08-05 17:52:41
0
Dr.Alemayehu, Internist :
@እንዳልክ@ሕገ-ልቦና_1987
2026-08-05 17:34:01
0
ኡመር ተዉፊቅ ይባላል :
🥰🥰🥰
2026-08-05 14:42:08
0
To see more videos from user @wasumohammed, please go to the Tikwm
homepage.