@aman_islamic_media: ሰበር።ከ ኡስማን ኢብኑ አፋን ጠሮ መስጂድ ወጣት ጀምዓ "ከሰሞኑ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚንዙ ብዥታዎች እና የሀሰት መረጃዎች አሁን ካለው የመስጂዱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ፈፅሞ የማይገናኙ መሆናቸውን ስለማሳወቅ" በየአመቱ የመውሊድ በዐል እና የረመዳን ወር ሲደርስ በመስጂዳችን የተለያዩ መስጂዱን የማበጣበጥ እና ሰላሙን የማወክ ድኩም ሙከራዎች በፀረ ሰላም ግብረ ሀይሎች የሚሞከር ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የመስጂዱ ኮሚቴ እና የመስጂዱ ወጣት ማህበር ከህግ ክፍሉ ጋር በመተባበር እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከተልን ሁሉንም ሙከራዎች ማከሸፍ ችለናል። አሁንም ጥቂት ቀናት የቀሩትን የሰይዳችን ሰ.0.ወ መውሊድ ሰበብ በማድረግ ተራ ፕሮፓጋንዳዎች እና በሙስና የተጠላለፉ የአንዳንድ ግለሰቦችን ህገ ወጥ የረብሻ ሙከራዎች እየተመለከትን ሲሆን ካለፉት ግዜያት በጠነከረ መልኩ በፅናት በመቆም የመስጂዱን ሰላም የምናስቀጥል መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። መስጂዱ እንደ ወትሮው ሁሉ ሰላሙ ተጠብቆ መደበኛ የስግደት እና የአስተምህሮት መርሀ ግብሩን እያስተናገደ ሲሆን አንድ ሺህ ተማሪዎች በመደበኛ የደርስ ፕሮግራም ሰማንያ ተማሪዎች በቀን ሙሉ እና በአዳሪ መርሀ ግብር የክረምት ቂርዐታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። በተነዙ የሀሰት መረጃዎች ግርታ ለተፈጠረባቹ ሙስሊም ማህበረሰቦች ሁሉ መስጅዱ ላይ ያለው ተጨባጭ ከላይ በገለፅነው መሰረት ሲሆን መስጅዱ ላይ ማንኛውም የኢማም ፣ የአስተዳደር እና መዋቅራዊ ቅያሪ ያልተደረገ ሲሆን ያለ ማህበረሰቡ ፍቃድ ሊጫኑብን እየታሰቡ ያሉ ማንኛውም ነገራቶች ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው ለማሳሰብ እንወዳለን። የዑስማን ኢብን አፋን (ጠሮ) መስጅድ ወጣት ማህበር

AMAN ISLAMIC MEDIA✅
AMAN ISLAMIC MEDIA✅
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 05 August 2026 17:12:09 GMT
1129
73
3
20

Music

Download

Comments

mohammedalisoresa
mohammed :
አልሀምዱ ሊላህ
2026-08-05 19:14:17
1
sebr4066
sebr :
Alhamdulillah 🥰 balefew ssema allah gne eskemech nw zm mtlachew bye nber🥺
2026-08-05 19:04:15
1
kokosman0913711745
Mhmad kalid :
alhmdila ymrenw gn
2026-08-05 18:38:49
0
To see more videos from user @aman_islamic_media, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About