@nonohuynh68: 30k Áo ba lỗ thun mát cho chó mèo . Từ 1kg-20kg . Giá có thể thay đổi hết chương trình khuyến mãi #thucung #quanaothucung #phukienthucung

Nô Nô Huỳnh68
Nô Nô Huỳnh68
Open In TikTok:
Region: VN
Wednesday 05 August 2026 17:24:22 GMT
509
1
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @nonohuynh68, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

*📌 የአረብ ሀገር እህቶች እውነታ፦ በኩሽና ውስጥ የተደበቁ ጀግኖች! 🕊️✨*  የተለያዩ ሀገራት ላይ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በአረብ ሀገራት ስላሉ እህቶች ያላቸው ምልከታ እጅግ የተንሸዋረረ መሆኑን ሁልጊዜ እታዘባለሁ። ዛሬ አንዱ፦ “አረብ ሀገር ከሄዱ በኋላ ከመዳም ቤት ጠፍተው የሚሰሩ ሰዎች ስራቸው ምን እንደሆነ ስሰማ አዘንኩ” ሲል አነበብኩ... ስለማታውቀውና ስላልኖርከው እውነታ ዝም ብለህ የምትፅፈው አንተ ነህ የምታሳዝነን! እኛ ጠፋንም አልጠፋንም—የአረብ ሀገር ህይወት ማለት ክፍያ ያለው ግን «እስር ቤት» እንደሆነ ነው እኔ የምረዳው። (አሁን ላይ ጠፍቶ መስራት ከጥቅሙ ጉዳቱ ቢያመዝንም እንኳ።) ኮንትራት ቤት ያሉት እህቶቻችን ከወር ወር ያለ እረፍት ይሰራሉ፤ ደመወዛቸው ይቆጥራል። የቤት ኪራይ፣ የምግብ ወይም የሳሙና ወጪ የለባቸውም። ነገር ግን—ስራው እያመማቸው፣ ወገባቸውን አስረው ይሰራሉ። ቢደብራቸው «እስኪ ወጣ ብዬ ንፋስ ልቀበል» የሚባል ነገር የለም። እንባቸውን እያፈሰሱ፣ ሰው ሲመጣባቸው እየጠረጉ፣ ምንም ያልተሰማቸው አስመስለው በውሸት ፈገግ እያሉ ይሰራሉ! ከኮንትራቶቹ የሚለየን በውጭ ያለነው ደግሞ—ካልፈለግነው ስራ በቀላሉ መውጣት እንችላለን፤ ሲያመን «ሆስፒታልሄጄ ልመለስ» የማለት እድል አለን። ነገር ግን፣ ስራ አጥተው የሚበሉትና የሚጠጡት አጥተው ለወራት እቤት የሚቀመጡትን ቤቱ ይቁጠራቸው! በተለይ አሁን ባለንበት ጊዜ የቤት ኪራይ በየወሩ በተነሳ ቁጥር ተሸማቀው የሚኖሩት ስንትና ስንት ናቸው? በሰው ሀገር እድሜያቸው ከ20 እስከ 30 እና ከዚያ በላይ ሆኖ፣ 10 እና 12 ዓመታት ኖረው—ዛሬም በሰው ቁጥጥር ስር ያሉ፣ ውጭ ወጥተው ታክሲ ይዘው ቤታቸው መመለስ የማይችሉ ስንቶች አሉ? በምትኖርበት አከራይ «የከሌ ልጅ» ተብላ ትጠራለች፤ በፈለገችበት ሰዓት መውጣት አትችልም፣ «አልተፈቀደልሽም» ትባላለች። ምን ያህል ጭቆና ውስጥ እንደምንኖር ሳታውቁ—አፋችሁ እንዳመጣላችሁ «የአረብ ሀገር ሴት» እያላችሁ አትናገሩ! ሰዎች የማይረዱት ነገር ቢኖር—እናንተ ዝቅ አድርጋችሁ በምትገምቱበት ቦታ ውስጥ ማንም ያላያቸውና ያላወቃቸው ብዙ ታላላቅ ሰዎች (እንደ ጣሉት) አሉ! በሱረቱል በቀራህ ላይ አላህ የጣሉት (ጣሉትን) ታሪክ ሲነግረን፦ ጣሉት እረኛ ነበር፤ በበኒ እስራኤሎች ዘንድ ቦታ አልነበረውም። አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ግን   عَالِمُ الْغَيْبِ (የሩቁን አዋቂ) ነውና በእነሱ ላይ ንጉሥ አድርጎ ሾመው። እነሱም፦ ﴿قَالُوا أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ الْمُلْكُ عَلَيْنَا﴾ «በእኛ ላይ ንግሥና ለእሱ እንዴት ይኖረዋል?» አሉ! አላህ ግን እነሱ ማስተዋል ያልቻሉትን አቅሙን ነገራቸው፦ ﴿قَالَ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمِ ۖ وَاللَّهُ يُؤْتِي مُلْكَهُ مَن يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ﴾ (ነቢያቸውም) አለ፦ «አላህ በእናንተ ላይ መረጠው፤ በዕውቀትና በአካልም ስፋትን ጨመረለት። አላህም ንግሥናውን ለሚሻው ሰው ይሰጣል፤ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው።» (ሱረቱል በቀራህ፡ 247) አረብ ሀገር ያሉ ብዙ አዋቂዎችና ጥበበኞች አሉ! በአረብ ኩሽና ውስጥ ሆነው፣ ያችን ትንሽ የእረፍት ሰዓታቸውን ተጠቅመው፣ ከእንቅልፋቸው ቀንሰው ቁርአንንና የተለያዩ ኪታቦችን ተምረው ሌሎችን የሚያስተምሩ ብዙ ጀግኖች የአረብ ሀገር እህቶች አሉ! ጥፋት ይሰራሉ የሚባሉ ካሉም በእርግጠኝነት ከ100 ሁለቱ ወይም አምስቱ አይሆኑም። በነሱ ሰበብ ግን የ95 በመቶዎቹን መልካም ስም እያጠፋችሁ መሆኑን አስተውሉ! አንዳንዶች ቸርነታችንን ሞኝነት ይመስላቸዋል። እኛ ከስስታም ሰዎች ጋር አይደለም የምንኖረው፤ ደመወዝ የመጣ ቀን ቤታቸውን ሞልተው፣ በ15ኛው ቀን ከሰራተኛቸው ብር ከሚበደሩ ሰዎች ጋር ነው የምንኖረው!  እና እንዴት ሆኖ ነው ቋጣሪና ስስታም መሆን የሚቻለው? 😉  ስስትንና «ለኔ ብቻ» ማለትን አልተማርንም! ሰው የሚኖረው የሚያየው የሚሰማውን እኛ ደግሞ ስስትን አላየንም 😊 ✨ የአረብ ሀገር እህቶቻችን ጥናት፣ ትዕግስትና ልፋት አላህ ዘንድ ዋጋው ታላቅ ነው! ❤️

About