@memher2112: ✍️የቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰትና እርገት👇 የክብር፣ የትሕትናና የፍቅር ታሪክ 👉እስመ ርእየ ሕማማ ለአመቱ ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኵሉ ትውልድ። “እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” (ሉቃስ 1፥48) ቅድስት ድንግል ማርያም በመላው የድኅነት ታሪክ ውስጥ የተመረጠች፣ የተቀደሰችና ለዓለም መድኃኒት የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ የወለደች የማይወሰን መለኮትን በሚወሰን ሥጋ ምላቱን ሳይለቅ! ዳሩ ግን በከዊን የወሰነች ! ልጇ ለአምላክነቱ ተቀዳሚ ተከታይ እንደሌለው እሷም ለእናትነቷ ተቀዳሚ ተከታይ የሌላት እናት ናት። ሕይወቷ ከመጀመሪያው ጀምሮ በንጽሕና፣ በትሕትናና በፍጹም ታዛዥነት የተሞላ ነበር። ወላጆቿ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ሲሆኑ፤ ከልጅነቷ ጀምሮ ለእግዚአብሔር ተሰጥታ በቤተ መቅደስ በቅድስና አደገች። በዚያም በጸሎትና በትሕትና ኖራ ለታላቅ ምስጢር ተዘጋጀች። ከዚያም የመልአኩ ብሥራት ደረሰ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል;;ወቦአ መልአክ ኀቤሃ ወይቤላ፦ “ተፈሥሒ ፍሥሕት፡ ኦ ምልእተ ጸጋ፤ እግዚአብሔር ምስሌኪ፤ ቡርክት አንቲ እምአንስት።”ጸጋ የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ” (ሉቃስ 1፥28) ብሎ አበሰራት። እርሷም በትሕትና “እነሆ የጌታ ባሪያቱ ነኝ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” በማለት ለእግዚአብሔር ፈቃድ ታዘዘች። ከእርሷ የተወለደው ጌታችን ለዓለም መድኃኒት ሆነ። ድንግል ማርያምም በልጇ ሕይወት ሁሉ አብራ ቆመች፤ በልደቱ፣ በመከራው፣ በመስቀሉ እና በትንሣኤው ምስክር ሆነች። ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ “እነሆ ልጅሽ” ብሎ እናቱን ለቅዱስ ዮሐንስ አደራ ሰጠ (ዮሐንስ 19፥26-27)። ከዚያም በኋላ በጸሎትና በቅድስና ኖረች። ✍️የእመቤታችን ፍልሰት!!! የእመቤታችን የዚህ ዓለም ጉዞ ሲፈጸም በታላቅ ክብርና ሰላም አረፈች። ሐዋርያትም በመላው ዓለም ወንጌልን ሲያስተምሩ ነበር፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሰብስበው የእመቤታችንን ዕረፍት አከበሩ። የእርሷ ፍልሰት የመጨረሻ መጥፋት ሳይሆን ወደ ሰማያዊ ክብር መሻገር ነው። ሞት በክርስቶስ የተሸነፈ ስለሆነ፤ የእመቤታችንም ዕረፍት የተስፋ መልእክት ሆነ። ያ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የተነገረውን ተስፋና በቃል የተማረውን የትንሳኤ-ሙታን አምላካዊ ቃል የሚያረጋግጥ ቀዳሚ የማለዳ ጐኅ ሆነ ። 👉እርገቷ!! ከዕረፍቷ በኋላ እመቤታችን በክርስቶስ ፊት በክብር ተገኘች በርግጥ የበለጠውን ለመግለጽ እንጂ ያልከበረችበት ጊዜ የለም መመረጧ ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ ነውና። በቤተ ክርስቲያን የተላለፈው ትውፊት እንደሚያስተምረን ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን በክብር ተቀብሎ ወደ ሰማያዊ ክብር አስገባት(አሳረጋት)። ይህም ለእኛ ታላቅ ተስፋ ነው፤ ሰው በእምነት፣ በቅድስናና በታዛዥነት ቢኖር ወደ ዘላለማዊ ክብር እንደሚደርስ ያስተምረናል። ስለዚህ ጾመ ፍልሰታ የምንጾመው የእመቤታችንን ታሪክ ለማሰብ ብቻ ሳይሆን፤ እንደ እርሷ በንጽሕና፣ በትሕትናና በፍቅር ለመኖር ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃዋንና በረከቷን ታድለን። አሜን። ቀን 30 11 2018 ዓ'ም 🙏 መምህር ኤፍሬም ምናለ✍️

መ'ር ኤፍሬም ምናለ
መ'ር ኤፍሬም ምናለ
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 06 August 2026 07:29:48 GMT
1069
169
16
33

Music

Download

Comments

yichuwor
yichuwor :
እንኳን አብሮ አደረሰን
2026-08-07 12:32:36
0
rekik7920
ረቂቅ የኮልፌ ልጅ (ሕ) :
እንኳን አብሮ አደረሰን🙏🙏
2026-08-06 18:11:00
0
trinego8
ያልፍ ይሆን :
እንኳን አብሮ አደርሰን🙏🙏🙏🙏🥰
2026-08-06 13:44:57
0
sealtamhiret16
mulu21🕊 :
Ameen Ameen Ameen
2026-08-06 17:23:49
0
tewahido12345
✝️አነ ዘክርስቶስ። :
አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን መምህራችን 🥰ቃለ ሕይወት ያሰማልን🙏
2026-08-06 17:09:31
0
betelmidiya
ቤቴል ዘውዱ :
አሜን🙏🙏🙏
2026-08-06 13:47:35
0
mareyami21
emu የክርስቶስ እስረኛ✝️ቃል ስጋ ሆነ✝️ :
ማርያም✝️
2026-08-06 10:11:26
0
user3392610027904
ፍቅርተ-የማረያምልጅ መሠደዴ ለበጎ ሆነልኝ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-06 20:29:11
0
eternallifebygod
ዘክርስቶስ :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-06 18:02:44
0
user99917583800491
መባ ፍሽን ልብሶች :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-06 16:44:37
0
.me68061
ኤሊያና :
🙏🙏🙏
2026-08-06 12:59:22
0
yabesera16
eden Ⓗ :
🙏🙏🙏🙏
2026-08-06 09:17:32
0
kidist.29
Kīdū☦️🤍 :
❤️❤️❤️
2026-08-06 08:10:26
0
user1738653443527
selam :
🥰🥰🥰
2026-08-07 12:28:11
0
To see more videos from user @memher2112, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About