@sarwitegetagiram: «ፍልሰታ» ማለት «ማለፍ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መፍለስ» ማለት ነው። ይህም የእመቤታችን ዐፅም ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት፣ በኋላም ትንሣኤዋና ዕርገቷ ከተፈጸመ በኋላ ከገነት ወደ ሰማይ ማረጓን ያመለክታል። የምንጾምበት ዋና ምክንያቶች፦ ​1. የሐዋርያት ፈለግ ለመከተል (ሐዋርያት ስለጾሙት)፦ ​እመቤታችን ጥር 21 ቀን በ64 ዓመቷ ባረፈች ጊዜ ሐዋርያት ሊቀብሯት ሲወስዷት አይሁድ «ሥጋዋን አቃጥለን ጥፋቷን እናጥፋ» ብለው ስላደሙ፣ እግዚአብሔር ሥጋዋን በደመና ነጥቆ በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖረው። ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ ተለይቷቸው መኖር ስላልቻሉ «ሥጋሽን ግለጥልን» ብለው ከነሐሴ 1 ጀምረው እስከ ነሐሴ 14 ቀን ድረስ 14 አምስት ቀን ሱባኤ ያዙ። በ14ኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀበሯት። ​2. የእመቤታችንን ትንሣኤና ዐርገት ለማየት፦ ​ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በዕርገቷ ዕለት በደመና ተጭኖ ሲመጣ እመቤታችን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ ስታርግ ያገኛታል። ሰበኗን (መገነዟን) ሰጥታው እርስዋ አረገች። ቶማስ ወደ ሐዋርያት መጥቶ የእመቤታችንን መነሣት ሲነግራቸው ባዩት ነገር ቀንተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ?» ብለው እንደገና ከነሐሴ 1 ጀምረው ሱባኤ ገቡ። በነሐሴ 16 ቀን ጌታችን እመቤታችንን እግረ አበሳ (ቀዳሚት) አድርጎ አምጥቶ፣ እመቤታችንን ቄስ፣ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፣ እስጢፋኖስን ዲያቆን አድርጎ ቅዳሴ ቀድሶ ቁርባን አቀበላቸው። ሐዋርያት ትንሣኤዋንና ዐርገቷን በአይናቸው አይተው ተደሰቱ። ​3. የበረከትና የጸሎት ጊዜ ስለሆነ፦ ​እኛም ዛሬ የሐዋርያትን አርአያ ተከተልን፤ የእመቤታችንን በረከት፣ አማላጅነትና ፍቅር ለመቀበል፣ ከኃጢአታችን ለመንጻትና በሱባኤ ከአምላካችን ጋር ለመገናኘት ይህንን ጾም እንጾማለን። ​መልእክት፦ በዚህ በታላቁ የሱባኤ ወቅት አቅማችን በፈቀደ መጠን በጾም፣ በጸሎት፣ በምጽዋትና በቅዱስ ቁርባን በመወሰን የእመቤታችንን ረድኤት እንቀበል። ​«የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ ጸሎትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!»#2millionviews

@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
Open In TikTok:
Region: BH
Thursday 06 August 2026 12:58:43 GMT
7013
1401
16
25

Music

Download

Comments

worku.kinfe4
workukinfe4 :
ameneamene amene
2026-08-06 13:27:15
0
alualu16
Almi :
2026-08-06 14:58:14
1
azanashmekete
Azanash Mekete :
አሜን 🙏🙏🙏🙏
2026-08-06 14:58:40
1
fanose6631
fanose :
amen amen maem
2026-08-06 14:05:07
1
zewdneshgizaw287
Zewdnesh Gizaw :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰አሜንንን
2026-08-06 13:18:55
0
user9742551313301
memey :
Amen Amen Amen 🙏🙏🙏🙏
2026-08-06 13:27:53
0
user9133556175467
leyla m :
amennnn
2026-08-06 13:23:55
0
rebale21
Rebale21 :
ኣሜን ኣሜን ኣሜን
2026-08-06 13:21:27
0
asmera190
🦁 ዴቨይ ፈዉሲ ልቢ ☦️ 💪 :
🙏🙏🙏
2026-08-06 14:48:57
0
user28017663322796
Masresha tesfsye :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-06 14:05:19
0
gursha.znabi
የተሰፋ ሸጋ እህት :
🥰🥰🥰
2026-08-06 14:00:51
0
mmasdfg4
ድንግል ማርያም ልጁ ነኝ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-06 13:32:35
0
fantabele
h tying :
🙏🙏🙏
2026-08-06 13:17:40
0
danieel8333
dani orthodox :
🙏🙏🙏🙏
2026-08-06 13:13:47
0
user75077993600055
lemlem :
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
2026-08-06 13:03:23
0
feqeri7
ye maryam lji Enate21❤🤲 :
🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽
2026-08-06 15:18:33
0
To see more videos from user @sarwitegetagiram, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About