@marta.ye.gebreli: #እንኳን_ለፍልሰታ_ጾም_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን ። ፍልሰታ የሚለው ቃል ፈለሰ ከሚለዉ የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መለየት ፣ ማረግ ፣ ወደላይ መዉጣት ፣ ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ መሄድ ማለት ነዉ ። ፆመ ፍልሰታም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስገዋ ከመቃብር መለየትና ማረግን ተመልክቶ የሚፆም የአመቱ የመጨረሻ የአዋጅ ፆም ነዉ ። እመቤታችን ካረፈች ቡኃላ ሀዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ሲሄዱ አይሁድ እርሷም እንደ ልጇ ተነስታ አረገች እያሉ ሊያዉኩን ነዉ በማለት ስጋዋ እንዲቃጠል አዙዙ ። ይሄን ገዜ መላእክት ስጋዋን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት ከእፀ ህይወት ስር ወስደዉ አስቀመጡ ። ስጋዋ ያለበትን ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ ቀሪዎቹ ቅዱሳን ሀዋርያት ባለማየታቸዉ ከነሐሴ 1-16 ቀን ከፆሙ ቡኃላ ስጋዋን ከጌታ ተቀብለዉ በጌቴሰማኒ ቀበሩ ። በተቀበረችም በ3ኛዉም ቀን እንደ ልጆ ተነስታ ስታርግ ሀዋርያዉ ቅዱስ ቶማስ ከስብከተ ወንጌሉ ሲመለስ አገኛት ያን ጊዜ ትንሳኤዋን ያየ መሆኑን ነግራዉ ሰበኗን ለምልክትነት ሰጠችዉ ። የትንሳኤዋን ነገር ሳያዩ ቅዱስ ቶማስ ብቻ በማየቱ መንፈሳዊ ቅናት የተሰማቸዉ ሀዋርያት በአመቱ ከነሐሴ 1-16 ቀን ማረጓን ያዩ ዘንድ ፆሙ ጌታም ሀሳባቸዉን ፈፀመላቸዉ ። እኛም ይህን የሐዋርያት ፆም ምሳሌ አድርገን የእመቤታችን እረፍት ፣ ትንሳኤና እርገቷን በማሰብ ሁልጊዜ በየአመቱ ከነሐሴ 1-16 እንፆማለን ። የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ሀዋርያት ፀጋና በረከት ይደርብን አሜን ።
Marta Ye Gebreli
Region: LB
Thursday 06 August 2026 17:57:58 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @marta.ye.gebreli, please go to the Tikwm
homepage.