@rozabirouk: ጾመ ፍልሰታ (ጾመ ማርያም) ✝️ ፍልሰታ የሚለው ቃል "ፈለሰ" ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም "መለየት፣ ማረግ፣ ወደ ላይ መውጣት፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ" ማለት ነው ✝️ ጾመ ፍልሰታም የእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋዋ ከመቃብር መለየት እና ማረግን ተመልክቶ የሚጾም የዓመቱ የመጨረሻው የዓዋጅ ጾም ነው ✝️ እመቤታችን ካረፈች በኋላ ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ሴሄዱ አይሁድ "እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች፣ ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነው" በማለት ሥጋዋ እንዲቃጠል አዘዙ ✝️ ይህን ጊዜ መላእክት ሥጋዋን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ስር ወስደው አስቀመጡ ✝️ ሥጋዋ ያለበትን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው ሐዋርያት ከነሐሴ ፩ እስ ፲፬ ቀን ከጾሙ በኋላ ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ቀበሩ ✝️ በተቀበረች በ፫ኛውም ቀን እንደ ልጇ ተነስታ ስታርግ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከስብከተ ወንጌሉ ሲመለስ አገኛት፤ ያን ጊዜም ትንሣኤዋን ያየ እርሱ ብቻ መሆኑን ነግራው ሰበኗን ለምልክትነት ሰጠችው ✝️ የትንሣኤዋን ነገር ሳያዩ ቅዱስ ቶማስ ብቻ በማየቱ መንፈሳዊ ቅናት የተሰማቸው ሐዋርያት በዓመቱ ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው እስከ ፲፮ ቀን ማረጓን ያዩ ዘንድ ጾሙ ✝️ ለእኛም ይህ ጾም የሐዋርያትን ጾም ምሳሌ አድርገን የእመቤታችንን እረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷን የምናስብበት ነው ➻ ከበረከትዋ እንድንካፈል፣ ምልጃ ጸሎታችን እንዲሰማልን በየዓመቱ ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፮ እንጾማለን። የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን። #አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንዲት_ጥምቀት #ተዋህዶ #orthodoxchurch
Roza Birouk
Region: LB
Thursday 06 August 2026 19:00:56 GMT
Music
Download
Comments
NOEL samuel PAPI :
አሜን
2026-08-07 07:49:56
0
betiy@123💚💛❤️ :
አመለን
2026-08-06 20:45:30
0
መአዚ የኪዳነምረት 16 ልጅ :
🤲🤲🤲
2026-08-06 19:05:56
1
salam love ❤️ 😍 💖 lamies :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-06 20:40:27
1
meron berhe :
🥰😘🥰💕🙏🙏🙏
2026-08-06 20:03:22
0
melkamfery :
🙏❤️🙏❤️🙏❤️🙏
2026-08-06 22:25:58
1
To see more videos from user @rozabirouk, please go to the Tikwm
homepage.