@user395834718124: #duetwith #part3 #የዘመነ ካሴዎች ትግልና የባጫ ደበሌ ኑዛዜ... አራት ኪሎማ ከኛ ወዲህ ማ አለ? ዳንኪረኛው ባጫ ደበሌ፣ በሶ በጥባጩ አትንኩት ምን እያለ ነው? ኮንትሮባንዲስቱ አምባሳደርና ምርኮኛው ጄኔራል ለBBC አማርኛ ስርጭት እንዲህ ሲል ተናገረ "ዘመነ ካሴ አራት ኪሎ ና ቢባልም አይመጣም፤ብቃትም የለውም።" አስቀድመን ፍሬ-ነገሩን የሚንዱ ሀቆችን እናነሳለን። በዋናነት ግን የባጫን ፕሮፖጋንዳ እንድምታ እንናገራለን። ባጫ የዘመነ ካሴ ባውቄን ወደ አራት ኪሎ መምጣት አይችልም ፉከራ ያደረገው የአርበኛ ዘመነ ካሴን ግላዊ ብቃት በማሳነስ ዓይነት ነው። እውነታው ግን ከባጫ ፉከራ የተለዬ ነው። አርበኛው በማስተርስ ዲግሪ የዋንጫ ተሸላሚ ነው። ይህ ዲግሪ በችሮታ የተሰጠ ወይም በትዕዛዝ የታደለው አይደለም፤ በተመሰከረ ብቃቱ ያገኘው ነው። እንዲህ ያለ የተረጋገጠ ዲግሪ ያለው ሰው በባጫ የዳንኪራ ክለብ ውስጥ የለም። አርበኛው ለአስርት ዓመታት የዘለቀ የትግል ልምድ አለው። በዚህ ልምዱ በተግባር የተፈተነ የመምራት፣ የማስተባበር፣ የማደራጀትና የማብቃት ችሎታውን አሳይቷል። ይህ የጸሐፊው ማወደሻ ቃል አይደለም። ታሪክ በደማቅ ብዕሩ እየከተበው ያለ የተኖረ ጀግንነት ነው። ማንም ሊክድው የማይሞክር፣ ሊያስተባብለው ሆነ ሊያሳንሰው የማይቻለው ግዙፍ የታግሎ ማታገል ታሪክ ያለው ነው። በባጫ የዳንሰኞች ክለብ እንዲህ ያለ የለም። ሀቀኛ የኦሮሞን ወጣቶች ትግል የሚጠልፍ አጭበርባሪ እንጅ ታግሎ የሚያታግል አለቃ ኖሮት አያውቅም አትንኩት። አርበኛው ከእነዚህ ሁሉ የሚበልጥ ሌላኛው ብቃቱ በማያቋርጥ ንባብና ማሰላሰል ውስጥ የሚኖር ብርቱ ማንነት ያለው መሆኑ ነው። የአባቶቹን ድርሳን፣ የምሁራኑን ጥናቶችና ሌሎች የታሪክ መዛግብትን ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮንና ሁኔታን በንስር ዓይኖቹ ይመረምራል። የአፍሪካ ቀንድን መልክዓ ፖለቲካ(GeoPolitics) አንብቦት ብቻ ሳይሆን ኖሮት ያውቀዋል። የአትንኩት አለቃ ግን ዓባይን በአዋሽ ለመተካት ከመዳከር በቀር መልክዓ-ፖለቲካውን አይረዳውም። ባጫ ደበሌ እንዲህ ያለውን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሙዚቃ ሊደንስበት ቀርቶ አይሰማውም። አርበኛው ደንበኛ የአማራ ብሄርተኛ ነው። የታወቀና የማያሻማ ውግንና፣ ዓላማና ግብ አለው። የሚኖርለት ዓላማ የሚሰዋለት እውነት አለው። የአማራ ብሔርተኝነትና ኢትዮጵያዊነትን፣ የሌሎችን ብሔሮች ጥያቄዎችና የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች እንደ ዋሸራ ቅኔ በሰምና ወርቅ ያዋድደዋል። ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በእኩልነት፣ በነጻነትና በአንድነት የሚመሩበትን የህግ፣ የኢኮኖሚክስ፣ የሰላምና ጸጥታ፣ የዲፕሎማሲ እውቀቶች ብቻ ሳይሆን የጠራ የሞራል ልዕልናንም ታጥቋል። ኮንትሮባንዲስቱ ባጫ የኖረበት ክለብ ውስጥ እንዲህ ያሉ ሰዎች የሉም። ዳንኪረኛው ባጫ ከኮንትሮባንድ ንግዱ ፋታ በመውሰድ ፋኖዎች ብቃት የላቸውም በሚል አዝማች የተከሰተው ለምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ዋናው ቁምነገሩ የታጨቀበት ነው። ባጫ የአማራን ወጣት፣ አዲሱን ትውልድ አያውቀውም። የአማራ ሴቶች እንደ ፋንቱ ተስፋዬ ያሉ ይመስሉታል። እልፍ ጣይቱ ብጡሎች እንዳሉት አልተረዳም። የአማራ ሴቶች እንደ ዝናሽ ያሉ ኤልዛቤሎች ይመስሉታል። በእውቀት፣ በምግባርና በሞራል የተገነቡ የፍትህና የእውነት ቀንዲሎች መሆናቸውን አያስተውልም። ባጫ የአማራ ሰው እንደ ተመስገን ጥሩነህ ወይም እንደ ይርጋ ሲሳይ ሰነፍና ተቅበዝባዥ ይመስለዋል። የአማራ ወጣት ከእኩልነትና ከነጻነት በቀረ ሌላ ለምንም የማይበገር የአባቶቹ ልጆች መሆኑን ልብ አላለም። ትልቁ ቁምነገር ደግሞ ዘመነ ካሴ ባውቄ ብቻውን አለመሆኑ ነው። ምርኮኛው ባጫ አርበኛውን በስም ጠቅሶ ውሸቱን በማሰራጨቱ አርበኛውን በስም ጠቀስን እንጂ ከአርበኛው ውጭ፣ የገዘፈ ሞራል፣ ብቃትና ህልም ያላቸው ብዙ የአማራ ልጆች አሉ። የነጻነት ስሜቱንና የሞራል ልዕልናውን ተጋርተው የተመሙ ሚሊዮን ዘመነ ካሴዎች አሉ። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአማራ ጭንቅላቶች በዘመነ ዙሪያ መኖራቸውን ያውቅ ዘንድ የባጫ ማሰቢያ አይቻለውም። ትግሉ ለዘመነ ወይም ለአንድ ነጠላ ጉዳይ ወይም እንደ ባጫና አብይ አህመድ አሊ ለጥቂት ጎረምሶች ብልግና የሚደረግ አይደለም። ባጫ እንዳለው ለገንዘብ ፍላጎት የሚደረግም አይደለም። የአማራ ትግል የህልውና ትግል ነው። ለዚህ የህልውና ትግል ደግሞ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሳይቀመጥበት ሁሉም አማራ እየተዋደቀበት ያለ ነው። ከዚህ ሁሉ የሚበልጠው ግን ባጫ ደበሌ በዚህ ጊዜ የፋኖ መሪዎችን በስም እየጠቀሰ "አራት ኪሎ መምጣት አይችሉም" ማለት የተገደደበት ምክንያት ምንድን ነው? የሚለው ነው። ለስሙ ያህል ባጫ ዲፕሎማት ነው፣ ባጫ ጄኔራል ነው፤ ለወጉ ያህል አትንኩት የብልጽግና ከፍተኛ አመራር ነው። ይህን ሁሉ ማዕረግ የደረደረው ባጫ ተራ የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ተሰማርቶ መገኘቱ ለምንድን ነው? መልሱ አጭርና ግልጽ ነው። አለቃው አብይ አህመድ አሊ በፕሮፖጋንዳ ልሳኖቹ እየዞረ በአማርኛ የተናገረውን በኦሮሞኛ እየሻረ፣ በአፋን ኦሮሞ የተናገረውን በትግርኛ እየካደ የህዝብ ትግል የጠለፈበትን አጨብርባሪነቱን በአዲስ የሙዚቃ ስልት፣ የምክክር ኮሚሽን በሚባል አታሞ አጅቦ መዝፈን ለጀመረው ድግስ ባጫ መውረግረግ መጀመሩ ነው። በዘመነ ካሴዎች የሚመራው የአዲሱ ትውልድ ሀቀኛ ትውልድ በችሮታ፣ በጥሪና በማጭበርበር ሳይሆን በሀቅ፣ በእኩልነትና በአንድነት መርሆች እየተመራ አራት ኪሎ ይገባል። ይህ እንዲሆን የባጫ ምስክርነት፣ የአብይ አህመድ ፍቃድ አያስፈልገውም። ባጫ ጮሆ ሊደብቀው የፈለገው አንድ ጉዳይ አለ። በአራት ኪሎ ምኒልክ ቤተ-መንግስት የሚጠቅም ሰው አለመኖሩንና መሪ አልባ ነን የሚለውን ስምምነት ለማስተባበል ጥሯል። ዛሬ ላይ ቤተ-መንግስቱ ከሞራልም፣ ከእውቀትና ከቅንነትም አርባ ክንድ የራቁ ማፍያዎች፣ ሌቦች፣ ጨፍጫፊዎችና ኮንትሮባንዲስቶች የተሰባሰቡበት እንጅ የህዝብ መሪዎች የሉበትም። ትግላችን ለህዝብ ሰላምና ደህንነት፣ እድገትና መሻሻል፣ እኩልነትና ነጻነት፣ ዴሞክራሲና ብሩህ ተስፋ የሚተጉ መሪዎችን በአራት ኪሎ ቤተ-መንግስት ከመሰየም የሚያስቀረው አንዳች ኃይል የለም። ሼር ይደረግና ይድረሰው ለባጫ!!
አንድነት 🇨🇬ኃይል ነው✊💪💪
Region: BH
Thursday 06 August 2026 21:24:14 GMT
Music
Download
Comments
user33242865129027 :
be strong and polite
2026-08-07 06:44:51
0
Jemal Mohammed :
2026-08-07 04:32:52
0
Badriya :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-07 02:11:55
0
የጁ/예주 :
🤣🤣🤣🤣
2026-08-07 08:16:34
0
Nibret Einyew :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-07 05:19:31
0
የራያው :
😆😆😆😆😆
2026-08-06 21:58:48
0
Sisay Mokoya :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-06 21:49:22
0
chalhaw :
❤❤❤❤❤❤
2026-08-07 10:12:06
0
To see more videos from user @user395834718124, please go to the Tikwm
homepage.