@etanshe0: #CapCut ‎✨ ጾመ ማርያም..ፆመ ፍልሰታ✨ ‎*እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር 21 ቀን በ49 ዓ.ም በ64 ዓመቷ ከዚህ ዓለም አረፈች።ባረፈችም ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሔዱ፡፡ ‎ ‎*በዚህ ጊዜ አይሁድ ‹‹እንደ ልጇ ‹ተነሣች፤ ዐረገች› እያሉ ‎እንዳያውኩን በእሳት እናቃጥላት›› ብለው ሥጋዋን ሊያጠፉ በዓመፃ ተነሡ፡፡ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊም አጎበሩን ይዞ ሊያወርዳት ሲል የእግዚአብሔር መልአክ ሁለት እጆቹን ቀጣው፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ጨምሮ እመቤታችንን በደመና ነጥቆ ወደ ገነት ወስዶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣት፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም እመቤታችን ያለችበት ቦታ እንዲገለጥላቸው ባረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ጀመሩ፡፡ ‎ ‎*ቅዱሳን ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ (ዐሥራ አራት ቀናት) ካደረሱ በኋላም የነገሩትን የማይረሳ፣ የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታቸውን ሰምቶ ነሐሴ 15 ቀን የእመቤታችንን ሥጋ ሰጥቷቸው በክብር ገንዘው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡በሦስተኛው ቀንም እንደ ልጇ እንደ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታለች፡፡ ‎ ‎*ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ሲሰብክ ቆይቶ ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ወደ ሰማይ ስታርግ ጠፈር ላይ አገኛት፡፡በዚህ ጊዜ ትንሣኤዋን ባለማየቱ ኀዘን ስለ ተሰማው ከደመናው ይወድቅ ዘንድ ወደደ።እመቤታችንም ‹‹አይዞህ! አትዘን፤ባልንጀሮችህ ሐዋርያት ያላዩትን ትንሣኤዬን አንተ አይተሃልና ደስ ይበልህ!›› ብላ ከሙታን ተለይታ መነሣቷንና ማረጓን ለሐዋርያት እንዲነግራቸው አዝዛ የያዘቸውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡ ከዚያም እርሷ ወደ ሰማይ ዐረገች፤ እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ወረደ፡፡ ‎ ‎* ቅዱስ ቶማስ ትእዛዟን ተቀብሎ በክብር ከተሰናበታት በኋላ ወደ ሐዋርያት ሔዶ ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ስታርግ ማየቱን ገልጾ እመቤታችን የሰጠችውን ሰበን ለሐዋርያት ሰጥቷቸዋል፡፡ ‎ ‎* ሰበኑ በቅዳሴ ጊዜ ሠራዒ ዲያቆኑ በሚይዘው መስቀል ላይ የሚታሠረው መቀነት መሰል ልብስ፤ እንደዚሁም አባቶች ካህናት በመስቀላቸው ላይ የሚያደርጉት ቀጭን ልብስና በራሳቸው ላይ የሚጠመጥሙት ነጭ ሻሽ የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡ ‎ ‎*በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?›› ብለው ከየሀገረ ስብከታቸው ተሰባስበው ሥጋዋን ይሰጣቸው (ያሳያቸው) ዘንድ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ጌታችንን ጠየቁት፡፡ እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ነሐሴ 16 ቀን እመቤታችንን መንበር፤ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፤ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ እመቤታችንንም ሐዋርያትንም አቍርቧቸዋል፡፡ እነርሱም እመቤታችንን በዓይናቸው ከማየት ባሻገር አብረው ሥጋውን ደሙን ተቀብለዋል (ነገረ ማርያም፤ ትርጓሜ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም)፡፡ ‎ ‎*ይህንን ትምህርት መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከነሐሴ 1 እስከ 15 ቀን ያለው ሁለት ሱባዔ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ኾኖ በምእመናን ዘንድ መጾም እንደሚገባው ሥርዓት ሠርተውልናል (ፍት.ነገ.አን.፲፭)፡፡ ይህ ጾምም ‹‹ጾመ ማርያም (የማርያም ጾም)›› ወይም ‹‹ጾመ ፍልሰታ ለማርያም (የማርያም የፍልሰቷ ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ‹ፍልሰት› የሚለው ቃል ‹‹ፈለሰ ሔደ፤ ተሰደደ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ያመለክታል፡፡ ‹ፍልሰታ ለማርያም› ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን (ማረጓን) የሚያስረዳ መልእክት አለው፡፡ ‎ ‎✨የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን ። አሜን🙏 ‎ ‎✨ጾሙ የበረከት የፍቅር የሰላም የአንድነት ይልቁኑ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን የምንፀልይበት ጾም ያድርግልን ‎ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ። ‎➢ ምንጭ፡ የዓ/ገና/ደ/ም/ቅ/ሚካኤል/ቤ/ክ ‎ ‎ ‎

meklit🥀🔐🦋
meklit🥀🔐🦋
Open In TikTok:
Region: AE
Thursday 06 August 2026 22:06:05 GMT
642
241
16
3

Music

Download

Comments

asigde5
ብሌን 🦋👸 :
❤️❤️❤️❤️
2026-08-07 10:50:07
1
milkii576
Milkii :
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
2026-08-07 05:19:14
1
eyerus7880
Eyerus :
🙏🙏🙏
2026-08-23 05:14:32
0
user7444782913818
marta :
🥰🥰🥰
2026-08-09 19:06:11
0
biruk.nano4
Biruk Nano :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-09 14:35:02
0
bezachebezubeza50
bezachebezubeza50 :
🙏🙏🙏
2026-08-09 05:55:10
0
bekafeda1
Bᵉᵏᵃ ኢትዮጵያ ዘላለም ትኑር ᶠⁱᵏⁱʳ ⁿᵃᵗ! :
❤️❤️❤️
2026-08-08 14:40:11
1
0947609646b2121
bereket 2121 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-08 14:22:39
1
user7656841378160
user7656841378160 :
🥰🥰🥰
2026-08-08 12:27:13
1
sami.dan266
sami dan :
🥰🥰🥰
2026-08-07 10:08:25
1
endegeteshar
ende@getesh@ar :
🙏🙏🙏🙏
2026-08-07 09:49:20
1
yengusbaye
ሔዋን የድንግል ልጅ :
❤️❤️❤️
2026-08-07 06:34:16
1
milkii576
Milkii :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-07 05:19:11
1
ema.aba068
@ema aba❤️💝💞 :
🤲🤲🤲🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-08-06 23:18:36
1
user6748109536825
ሙሉነሽ :
🤲🤲🤲
2026-08-06 22:10:13
1
hana.getachw
eyrus Getachw :
🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰
2026-08-24 16:45:08
0
To see more videos from user @etanshe0, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About