@yeprotocolguday: የቪአይፒ፣ የክብር እንግዶች፣ የመሪዎች እና የኃላፊዎች አሽከርካሪዎች ማወቅ ያለባቸው የፕሮቶኮል እና ሥነ ሥርዓት ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የኃላፊ ወይም የVIP ሹፌር መሆን ከማሽከርከር ጥበብ በላይ የፕሮቶኮል እውቀትን ይጠይቃል፡፡ * የክብር መቀመጫ ቦታን መለየትና በዚሁ መሰረት በር ከፍቶ ማስቀመጥ እና ከፍቶ ማውረድ፣ VIPው ወይም እንግዳው የት መቀመጥ እንዳለበት ያውቃሉ? በፕሮቶኮል ህግ የመሪ ወይም የክብር እንግዳው ቦታ ከሹፌሩ በስተጀርባ ያለው የቀኝ ወንበር ነው! (ይህ እንደ ተሽከርካሪው የመሪ አቅጣጫ በየአገሩ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ) * ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ (Confidentiality): መኪና ውስጥ የሚወሩ ማናቸውንም የቢዝነስ፣ የፖለቲካም ሆነ የግል ወሬዎች መኪናው ውስጥ ይቀራሉ። ስለዚህ የVIP ሹፌር ማለት የድርጅቱ ወይም የኃላፊው የመጀመሪያው የፕሮቶኮል ፊት ነው! ተጨማሪ የሚሏቸውን የፕሮቶኮል ዝርዝሮች በአስተያየት መስጫው ያጋሩን! #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #Respect #viral #vip #carservice #ProtocolMatters #habeshatiktok
yeprotocolguday
Region: ET
Saturday 08 August 2026 10:46:15 GMT
Music
Download
Comments
Attraction Ethiopia Tours :
አንተ ያልከዉ እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ! መኪናዉ ሁል ጊዜ ቆሞ ሲነሳ ወደ ሚሄድበት አቅጣጫ ነዉ መቆም ያለበት ! ሞተር በፍፁም መጥፋት የለበትም እንዲሁም የመኪናዉ AC መጥፋት የለበትም ፣ በጉዞ ግዜ መኪናዉ ከዉስጥ በሴንትራል ሎክ መቆለፍ አለበት ! ማንኛዉም በር ከዉጭ በኩል በፍፁም መከፈት የለበትም ! ቪ አይ ፒ እንግዳዉ በጭራሽ እራሱ በር ከፍቶ ከመኪና መዉረድ አይችልም ሾፌሩ ወይን ከሹፌሩ ጋር ያለ ሰዉ ነዉ ለቪ አይ ፒ እንግዳዉ በር መክፈት ያለበት ! መኪናዉ ላይ ግዴታ GPS ሊኖረዉ ይገባል ! ለ ቪ አይ ፒ የሚቀርቡ ዉሀ ፣ የለስላሳ መጠጦች ፣ ወይም ኩኪሶች ቀርበዉለት እንግዳዉ ዉሀዉን ወይም ለስላሳዉን ከፍቶት ጀምሮት ቢተወዉ ከመኪናዉ ወርዶ ሲመለስ የተከፈቱት መጠጦች ወይም ኩኪሶች ተነስተዉ በአዲስ መተካት አለባቸዉ ! ለማንኛዉም የ ቪ አይ ፒ መስተንግዶ እና ስኩሪቲ ድራይቨር ልናገለግልዎ ዝግጁ ነን !
2026-08-08 11:34:25
518
Robson :
training kalachu please
2026-08-08 12:58:05
0
Wndye向上Bly :
9 ወር ሰርቼአለው.. በጣም አዛ ስራ ነው
2026-08-09 05:18:15
24
@abukiwogene1632 :
Please defensive driving yet mew miseletinew tebaberugm
2026-08-09 10:19:54
0
Samson megerssa :
የ ከፍተኛ ባለስልጣን ሚኒስተር ሹፌር ነኝ 6 አመቴ አለቃየ ተከፍቶ ገብቶ አያቅም እራሱ በር ከፍቶ ይገባል አጃቢ 4 አለ ተጨማሪ የ አጃቢ መኪና አለ አንድም ቀን በር ክፈቱ ብሎ አያቅም
2026-08-08 12:27:37
37
Tesfish TA 19 :
Best lesson
2026-08-09 10:43:54
0
Beza Negussie :
"ፕሮቶኮል ስርዓት ነው፤
ስርዓትን ማወቅ ደግሞ ስልጡንነት ነው"!!!
2026-08-08 10:56:18
256
Gediyon B 4649/97 :
ልዩ ልዩ መጠቀሚያዎች፣ቢቻል የትኛውንም አይነት የስልክ ባትሪ መሙያ ገመዶች፣ማስታወሻና ብዕር ቢኖር ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ።
2026-08-08 12:03:02
19
ኮዬ ፈጬ :
በመንገድ ላይ ለሚገጥሙት ማንናቸውም
አሉታዊ ነገሮች በፍፁም መረጋጋት ሳይረብሽ እና ሳይረበሽ መንቀሳቀስ አለበት እኔ ታክሲ ሹፌር ነኝ
2026-08-08 18:29:26
32
beßa :
💯 ትክክል ነህ ! ነገር ግን በዋነኝነት የደህንነት የዙሪያ ቅኝት ማድረግ ከምንም በላይ ትልቅ ቦታ የሚይዝ ጉዳይ ነው ! መኪና ማሽከርከር ብቻ ትልቅ ቦታን የሚያሰጥ አይደለም ! “ከፊት, ከኋላ እርቀትን ጠብቆ ማሽከርከር ! መታጠፊያ ቦታ ፍጥነትን በመቀነስ እንዲሁም ደርቦ የሚመጣ መኪናን ደርበህ የምታለፍው መኪና, የውስጥ ስፔኪዮ በመጠቀም ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴን መቆጣጠር እና የመኪናውን ቀለም ከነ ታርጋው ለተወሰነ ደቂቃ ወይም የጀመርከውን መንገድ ለቀህ እስክትወጣ ድረስ በአይምሮህ ውስጥ በደምብ መያዝ አለብህ ! ምክንያቱም ለዚያ VIP ተጠቃሚ ሰው የመጀመሪያ ፍላጎት ደህንነቱ ነው።
አመሰግናለሁ 🙏🏾😊
2026-08-08 14:50:26
17
Teklu official :
የታሸገ ውሃ ከመጠጣታቸው በፊት አሽከርካሪው ውሃው ያልተመረዘ መሆኑን ጨመቅ አድርጎ የማየት ሃላፊነት አለበት
2026-08-09 04:01:56
9
Pharmacy World👉የፋርማሲ አለም :
በተጨማሪ
-በጉዞ ወቅት ትኩረትን እንግዳው ላይ እና መኪናችን ላይ መሆን ይኖርበታል
-እንግዳው ካላወራን በቀር አለማውራቱ እንዳለ ሆኖ የምናወራው ነገር ጥንቁቅ መሆን ይኖርብናል
2026-08-08 17:47:43
14
gezu :
So we have got many vip in our society!
2026-08-09 08:36:22
0
Miki Shawel :
በዝርዝር ስናየው፣ መጀመሪያው ጥሩ የአሽከርከር ችሎታ መኖሩ ነው። ይህም አደጋዎችን መከላከል የሚችል፣ ምቹ የመንዳት ዘዴን የሚጠቀም እና ተሽከርካሪውን በጥሩ ሁኔታ የሚንከባከብ መሆንን ያመለክታል።
የፕሮቶኮል እውቀት ደግሞ የስልጣን እርከኖችን መረዳት፣ ሰዎችን በአግባቡ መቀበልና ማስተናገድ፣ እንዲሁም በሚስጥር አጠባበቅ ላይ ጥንቃቄ ማድረግን ይጨምራል።
በተጨማሪም፣ ከፍተኛ ታማኝነት፣ ሚስጥር የመጠበቅ ችሎታ፣ ሰዓት አክባሪነት፣ እና የተረጋጋ መንፈስ ለስራው ስኬት ወሳኝ ነገሮች ናቸው።
2026-08-08 18:25:34
9
Amen Wk553 aki :
Big respect
2026-08-08 11:34:24
1
Dr B :
thank u
2026-08-08 17:42:48
1
የደም ፀሐይ :
ያልካቸው ሁሉ እንዳለ ሆኖ የክብር እንግዳውን ከአደጋ መጠበቅ ፤የክብር እንግዳውን ሰአቱን ባግባቡ እንዲጠቀም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት፣ከተቻለ ሚሊተሪ ሳይንስ መማር🙏🙏🙏
2026-08-08 19:16:28
13
teme4456❤❤❤ :
በጣም ትልቅ ትምህርት !
2026-08-08 13:19:48
5
compromise :
ቲክቶክ አሁን ገና አማረበት አቦ አረካሸኝ....🙏🙏🙏 እኔ ሹፌር ነበርኩ vvip እና ያልሸው በጠቅላላ እውነት ነው በተጨማሪ ግን መንገዶችን ማወቅ ትልቁን ድርሻ ይይዛል በርታልን።
2026-08-08 18:23:31
6
Awcho Media :
ለኣሁን ባይጠቅመኚም ለቀጣይ ስለሚጠቅመኝ በደምብ ላዳምጠዉ
2026-08-08 10:50:41
7
home of pets 🐶🐕🦮🦁🐇🦜 :
አዲስ መስሪያቤት ለመቀጠር ስኔድ ማረግ ያለብንን እና ልንጠየቅ ምንችለውን መልስ ብትነግረን
2026-08-08 12:36:11
5
የንጉስ ልጅ 🤴 :
እኔም የኘሮቶኮል ሹፌር ነኝ። በጣም በምኖድና በምናከብር በአንተ አንደበት በዚ መልኩ ሞያችን ለተተኪው ማስተማር በጣም ደስ ብሎኛል። ተጨማሪ ብዬ የማስበው ተክለ ሰውነት በጣም ወሳኝነት አለው ከመጠን ያለፈ ውፍረትና በጣም ቀጫጫ መሆን ተገቢ አይደለም። በርታልን ቆንጆ ነገር ነው እያደረክ ያለው።
2026-08-08 12:36:55
5
Cherinet Ayele Aba muda :
ከልብ አመሰግናለው ከአስር አመት በላይ የአመራር ሹፌር ነኝ ዛሬ ደግሞ ይበልጥ ጠንካራ እንድሆን አደረከኝ አመሰግናለው
2026-08-09 11:00:36
6
Assefa Degefa :
🙏🙏🙏🙏በትክክል ትልቅ ትምህርት ነው
2026-08-09 04:53:08
2
dani 27🙏🙏🙏 :
የምር ገና ጀማሪ ነገርኩ ነገር ግን አለቃዬ ይረዳኝ ነበር ግን ከሀሁን በኋላ ተምሪያለው አመሰግናለው🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2026-08-09 05:50:55
6
To see more videos from user @yeprotocolguday, please go to the Tikwm
homepage.