@beykage: Beyblade x scalpers beware… #beyblade #beybladex #beybladebattle #beyblades #beybladexbattle

beykage
beykage
Open In TikTok:
Region: US
Saturday 08 August 2026 23:08:22 GMT
878
78
6
2

Music

Download

Comments

drdementicus
Dr. Dementicus Gaming :
This is hilarious
2026-08-10 00:56:44
1
beytalityx
BeytalityX :
This is legendary 🙌
2026-08-09 12:12:36
1
bigonionnc
Big Onion :
2026-08-09 00:41:34
2
To see more videos from user @beykage, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#ወንጌል በገጠር
#ወንጌል በገጠር" #50ኛ ዓመት #የወርቅ ኢዮቤልዩ አዘጋጅ #ኮሚቴና #ለጉራጌ ወንጌላውያን ምዕመናን የቀረበ የእውቅና ጥያቄ "ለታማኝ አገልጋዮች ክብር መስጠት ሰውን ማክበር ብቻ ሳይሆን፣ በእነርሱ የሠራውን እግዚአብሔር ማክበር ነው።" የተከበራችሁ የህብረቱ መሪዎች፣ አባቶች፣ እናቶችና ውድ የጉራጌ ወንጌላውያን ምዕመናን፤ "ወንጌል በገጠር" የ50 ዓመት ሕብረት ጉዞውን በሚያከብርበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ ይህን ታላቅ ሥራ በጸሎት፣ በእንባ፣ በመዝሙር፣ በስብከትና በመሥዋዕትነት ያቆሙ የእምነት አባቶችን ማስታወስና ማክበር የዚህ ትውልድ ሃላፊነት ነው።ያለፉትን አገልጋዮች በማስታወስ፣ በማክበርና ለሚመጣው ትውልድ የታማኝነት አርአያነት ለማስቀመጥ ይህ ታሪካዊ ዕድል ነው። ከእነዚህ አገልጋዮች መካከል ሕይወቱን ያፈሰሰ፣ ወጣትነቱን የሰጠዉ ሐዋርያው ብርሃኑ ከማል ልዩ ስፍራ ያለው አገልጋይ መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን። ለወንጌል ሲል የግል ሕይወቱን፣ ሀብትን ማሳደድን፡ ኢኮኖሚውንና ምቾቱን ወደ ጎን በመተዉ የክርስቶስን ወንጌል በጉራጌ ምድር እንዲስፋፋ ያለመታከት ሠርቷል። በመዝሙሩና በስብከቱ ብዙ ሰዎች ወደ ጌታ እንዲመጡ አገልግሏል፤ በፍርሃትና በባዕድ አምልኮ የታሰሩ ልቦች በክርስቶስ ነፃ እንዲወጡ በፀጋዉ አድርጓል ።ሰባት መዝሙር አልበሞችን በማቅረብ ብዙ ቤቶች የጸሎት ቤት ሆነዋል፤ ብዙ ልቦች በተስፋ ተሞልተዋል፤ ብዙ ወጣቶች ለአገልግሎት ተነሳስተዋል፤ ብዙ ዘማሪዎችም በእርሱ ፈለግ ተከትለው የወንጌል ድምፅ ሆነዋል። ክርስቶስ እንዲታወቅ፣ ወንጌል እንዲሰፋ፣ ሰዎች ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዲመጡ ከተማን በመናቅ መሰረተ ልማት የሌለበት ገጠር በመግባት የወንጌልን ብርሀን በሀይል አብርቷል ። በመዝሙር አገልግሎቱ ብዙ ትውልዶችን አነሳስቷል፤ ብዙ የወንጌል ዘማሪዎችና አገልጋዮች እንዲነሱ መንገድ ጠርጓል። የእርሱ አገልግሎት ግን በመዝሙር ብቻ አልተገደበም። የተቸገሩትን አስቦ ቤት ሠርቷል፤ ተማሪዎችን ደግፏል፤ ለቤተ ክርስቲያኖች በልግስና አገልግሏል። ለእርሱ ወንጌል ማለት ቃል ብቻ ሳይሆን በፍቅር የሚገለጥ ሕይወት ነዉ፡፡ ይህ ጥያቄ የአንድ ሰው ጥያቄ አይደለም፤ ይህ የታሪክ ጥያቄ ነው። ይህ የህሊና ጥያቄ ነው። ይህ የትውልድ ጥያቄ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ "ሽማግሌዎችን እጅግ አክብሩ፤ በተለይም በቃልና በትምህርት የሚደክሙትን" (1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥17) ይላል። ስለዚህ ታማኝ አገልጋዮችን ማክበር የሰው ልማድ ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህም ነው። እንግዲህ ጥያቄያችን ቀላል ነው። እንዲህ ያለ ታማኝ አገልጋይ በዚህ የወርቅ ኢዮቤልዩ ላይ ካልተከበረ፣ መች ይከበራል? ትውልድ የሚማረው ከምን ነው? ወጣቶች የሚነሳሱት ከማን ነው? ታማኝ አገልጋዮችን ማክበር እነርሱን ከፍ ለማድረግ አይደለም፤ እግዚአብሔር በእነርሱ የሠራውን ሥራ ለመመስከር ነው። ይህ ደግሞ ለሚመጣው ትውልድ "ታማኝነት ዋጋ አለው" የሚል መልእክት ያስተላልፋል። ስለዚህ በ"ወንጌል በገጠር" 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ላይ ለሐዋርያው ብርሃኑ ከማል ተገቢው የክብር እውቅና እንዲሰጠው በአክብሮት እንጠይቃለን። ይህ ለአንድ ሰው የሚሰጥ ሽልማት ብቻ ሳይሆን፣ ለወንጌል ታማኝነት፣ ለመሥዋዕትነትና ለትውልድ የተተወ መልካም አርአያ የሚሰጥ ክብር ይሆናል። ታማኞችን ማስታወስ የታማኝነትን ታሪክ ማስቀጠል ነው፤ የእምነት አባቶችን ማክበር ደግሞ የወንጌልን ትውልድ ማክበር ነው። "እንግዲህ ለሐዋርያው ብርሃኑ ከማል የሚገባው የክብር እውቅና በዚህ ታሪካዊ የ50ኛ ዓመት ኢዮቤልዩ ላይ እንዲሰጠው በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ የሚከብሩት ታሪክ የሚያስታውሱ ትውልዶች ናቸው ። እኛም የምናስታውስና የምናከብር ትውልድ እንሁን።የእምነት አባቶችን ማክበር ደግሞ የወንጌልን ትውልድ ማክበር ነው።

About