@dr.tizazu: 👉 በእርግዝና የመጀመሪያዎቹ ወራት (ከ1-3 ወራት) ውስጥ የሚከሰት የፅንስ መቋረጥ አብዛኛውን ጊዜ በሴቶች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ፣ በስራ ወይም በጭንቀት የሚከሰት ይመስለዋል ለብዙ ሰው። 👉 ነገር ግን የአብዛኞቹ ምክንያቶች ከእናቲቱ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ተፈጥሯዊ እና ህክምናዊ ሁኔታዎች ናቸው። 👉 በእነዚህ ወራት ለፅንስ መቋረጥ ዋነኛ ምክንያት የሚሆኑት 5 ምክንያቶች፡ 1. የዘረመል (የጂኔቲክ) መዛባት 👉 በመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ውስጥ ለሚከሰቱ ከ50% እስከ 60% የሚሆኑ የፅንስ መቋረጦች ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው። 👉 እንቁላል እና የወንድ ዘር በሚቀላቀሉበት ጊዜ በሚፈጠር የክሮሞሶም ቁጥር መዛባት ምክንያት ፅንሱ በአግባቡ ማደግ አይችልም። 👉 ይህ አጋጣሚ የሚከሰት እንጂ በቤተሰብ የሚወረስ ወይም እናቲቱ ባደረገችው ስህተት የመጣ አይደለም። 2. የእናት እድሜ መጨመር 👉 የእናት እድሜ እየጨመረ ሲሄድ በእንቁላል ውስጥ የሚኖሩ የክሮሞሶም መዛባቶች የመከሰት ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። 👉 ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ ሴቶች የፅንስ መቋረጥ ዕድላቸው ከ10-15% አካባቢ ሲሆን፣ ዕድሜ ከ40 ዓመት በላይ ሲሆን ግን ይህ አደጋ እስከ 40% እና ከዚያ በላይ ሊያድግ ይችላል። 3. በትክክል ያልታከሙ ስር የሰደዱ ህመሞች 👉 እናት ላይ የሚገኙ አጠቃላይ የጤና ችግሮች በጊዜ ካልተካከሉ እና ካልተቆጣጠሯቸው ለፅንስ መቋረጥ ምክንያት ይሆናሉ። 👉 በትክክል ያልታከመ የስኳር በሽታ: በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከፍተኛ መሆን ለፅንስ መቋረጥ እና ተፈጥሯዊ ጉድለቶች ያጋልጣል። 👉 የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት: የሆርሞን አለመመጣጠን የፅንስ እድገትን ይገታል:: 👉 የበሽታ መከላከል እና የደም መርጋት ችግሮች: ወደ ፅንሱ የሚሄደውን የደም ዝውውር በማስተጓጎል ፅንስ እንዲቋረጥ ያደርጋሉ። 4. የማህፀን መዋቅራዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርፅ ችግሮች 👉 ፅንሱ በማህፀን ግድግዳ ላይ በትክክል እንዳያድግ የሚያደርጉ የማህፀን ችግሮች፡ 👉 ተፈጥሯዊ የማህፀን ከፋይ ግድግዳ (ሴፕተም): በማህፀን ውስጥ የሚኖር ተፈጥሯዊ ግድግዳ የደም ዝውውር ስለሚያንስበት ፅንሱ እንዳያድግ ያደርጋል። 👉 የማህፀን እጢዎች: በተለይ በማህፀን ውስጠኛው ግድግ ላይ የሚወጡ እጢዎች። 👉 የማህፀን ውስጥ ጠባሳዎች: ከቀዶ ህክምና ወይም ኢንፌክሽን በኋላ የሚፈጠሩ ጠባሳዎች። 5. የአኗኗር ዘይቤ እና የአካባቢ ተፅዕኖዎች 👉 ከህክምና ምክንያቶች በተጨማሪ በእርግዝና ወቅት ለፅንስ መቋረጥ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ አደገኛ ሁኔታዎች፡ 👉 ከፍተኛ የሲጋራ/ትምባሆ ተጋላጭነት እና የ አልኮል መጠጥ አጠቃቀም። 👉 ከፍተኛ የሰውነት ክብደት: ከሆርሞን መዛባት ጋር ተያይዞ አደጋውን ይጨምራል። 👉 ለመርዛማ ኬሚካሎች ወይም ጨረሮች በስራ ቦታ ወይም አካባቢ ተጋላጭ መሆን።

ዶ/ር ትዕዛዙ(የማህፀን እና ፅንስ ሃኪም)
ዶ/ር ትዕዛዙ(የማህፀን እና ፅንስ ሃኪም)
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 09 August 2026 11:29:07 GMT
249949
4248
14
190

Music

Download

Comments

user8878208622429
fffffye :
ዶክተር ፅንሱ ከተቋረጠ ቡሀላ እደገና ለማረገዝ ምን ያክል ቀን መቆየት አለብኝ መልስልኝ
2026-08-09 12:19:36
3
solsosc
Ghion Ghion :
hydro cephalis
2026-09-04 18:51:45
0
user9632085617552
burte :
🥰🥰🥰1ኛ
2026-08-13 11:06:32
0
ayish1965
አይሻ ቦንዳ ወራቤ :
🥰🥰🥰 1ኛ
2026-08-09 12:24:55
1
user7537870532524
❤❤❤ኡሙ ሙዓዝ❤❤❤ :
አዎ ዶ/ር ድጋሚ ለማርገዝ ምን ያህል ጊዜ መቆየት አለብን እንዳይከሰት ምን ማድረግ አለብን🥰🥰
2026-08-10 04:40:36
2
mimi.wedajo6
እየሱስ ያድናል :
ትዜ ተባረክ
2026-08-10 17:21:41
1
merry.worku6
Merry Worku :
ምንድነው
2026-08-20 11:04:05
0
bezi.my
mariiii :
🥰🥰🥰
2026-08-14 17:18:13
1
berberomlove
Berberom love :
🥰🥰🥰
2026-08-22 10:44:35
0
user2302455498503
user2302455498503 nezfa :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-02 14:18:12
0
gondariann
tinagin :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-11 06:47:18
0
helugirl1
helina :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-12 06:52:49
0
sirajudin040
ያረብአተአግዘኝ :
🥰🥰🥰
2026-09-06 07:14:15
0
To see more videos from user @dr.tizazu, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About