@pazi1221: #እመቤታችን_በሰባቱ_ዕለታት_ትመሰላለች (ውዳሴ ማርያም አንድምታ) 👉በዕለተ እሑድ ትመሰላለች። በዕለተ እሑድ አራቱ ባሕርያት አሥራወ ፍጥረታት ተገኝተዋል። ዘኮነነ ምክንያተ ፍጥረት በህላዌሁ እንዲል የአራቱ ባሕርያት አሥራወ ፍጥረታት ምክንያት የሚሆን ጌታም ከእርሷ ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። 👉በዕለተ ሰኑይ ትመሰላለች። በዕለተ ሰኑይ ከዚህ እስከ ብሩህ ሰማይ ድረስ ውኃ ሞልቶ ይዞት ነበር። ያንን ከሦስት ከፍሎ ✔️አንዱን እጅ ውኃ በመካከል አጽንቶ የብርሃን መመላለሻ አድርጎታል ይህ የምናየው ሰማይ ነው ጠፈር ይባላል። ✔️አንዱን እጅ ውኃ ከጠፈር በላይ አኑሮታል (ሰቅሎታል)ሐኖስ ይባላል። ይኸውም ኃያል ተሐዋኪ ብጽብጽ ውኃ ነው። ✔️አንዱን እጅ ውኃ በዓለሙ ዙሪያ ምድሩን አጎድጉዶ ወስኖታል ውቅያኖስ ውቅያኖስ ይባላል። ጠፈር የእመቤታችን ፥ ብርሃን የጌታችን ምሳሌ። ይህማ በዕለት ትመሰላለች አልን እንጂ መች በጠፈር ትመሰላለች አልን ብሎ፦ ዕለት የእመቤታችን ፥ ብርሃን የጌታችን ጠፈር ከእርሷ የነሣው ሥጋ ምሳሌ። 👉በዕለተ ሠሉስ ትመሰላለች። በዕለተ ሠሉስ ለታብቁል ምድር ዘርዐ ወሐመልማለ ሣዕር ዘይዘራዕ በበዘርኡ ወበበአምሳሊሁ ወበበ ጽጌሁ ወበበ ፍሬሁ ባለ ጊዜ ለሥጋውያን ምግብ የሚሆኑ ሦስት ፍጥረታት ተገኝተዋል። እሊህም በምሳር የሚቆረጡ ዕፀዋት ፥ በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕት ፥ በጥፍር የሚለቀሙ አትክልት ናቸው። ምግበ መንፈሳውያን ጌታም ከእርሷ ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። 👉በዕለተ ረቡዕ ትመሰላለች። በዕለተ ረቡዕ ለያብርሁ ብርሃናት ውስተ ጠፈረ ሰማይ ባለ ጊዜ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት ተገኝተዋል። ብርሃነ ሕይወት ጌታም ከእርሷ ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። 👉በዕለተ ሐሙስ ትመሰላለች። በዕለተ ሐሙስ ለታውፅእ ባሕር ዘይሐወስ ዘቦ መንፈሰ ሕይወት ባለጊዜ በልባቸው የሚሳቡ ፥ በእግራቸው የሚሽከረከሩ ፥ በክንፋቸው የሚበሩ ፥ በደመ ነፍስ ጸንተው ሕያዋን ሁነው የሚኖሩ ሦስት ፍጥረታት ተገኝተዋል። ዕለቱን በረው በረው የሄዱ አሉ ከዚያውም የቀሩ አሉ። በረው በረው የሄዱት የኢጥሙቃን ፥ ከዚያው የቀሩት የጥሙቃን ምሳሌ። ይህስ ወባረኮሙ ለክልኤሆሙ በአሐቲ በረከት ይላል ብሎ ✔️በልባቸው የሚሳቡ አንዲት ሴት አግብተው በሕግ ተወስነው አሥራቱን በኵራቱን ቀዳምያቱን አውጥተው ፥ እግረ ፈላስያንን አጥበው ፥ ሥጋውን ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ የሰብአ ዓለም (የምእመናን) ምሳሌ። ✔️በእግራቸው የሚሽከረከሩ የባህታውያን ምሳሌ፤ ከገድል ወደ ገድል ፥ ከትሩፋት ወደ ትሩፋት ይሄዳሉና። ✔️በክንፋቸው የሚበሩ ተመስጦ ጸጋ ያላቸው የሰማዕታት ምሳሌ። ዕለት የእመቤታችን ፥ ባሕር የጥምቀት ምሳሌ። 👉በዕለተ ዐርብ ትመሰላለች። በዕለተ ዐርብ ንግበር ሰብአ በአርኣያነ ወበአምሳሊነ ባለ ጊዜ አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል። ዳግማይ አዳም ጌታም ከእርሷ ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። 👉በዕለተ ቀዳሚት ትመሰላለች። በዕለተ ቀዳሚት ወአመ ሳብዕት ዕለት ወአዕረፈ እግዚአብሔር እምኩሉ ግብሩ ዘአኃዘ ይግበር፤ እንዲል ሥጋዊ ዕረፍት ተደርጎባታል። የመንፈሳውያን ዕረፍት የሚሆን ጌታም ከእርሷ ለመገኘቱ ምሳሌ ነውና። 🤲እመቤታችን ሆይ ምልጃሽ አይለየን ክፉውን ነገር ኹሉ ከሀገራችን አስወግጅልን አሜን!#ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኩራቴ😘ኢትዮ #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹
ጳዝዮን ዝክረ ቅዱሳን🦅⚡️
Region: LB
Tuesday 11 August 2026 06:04:13 GMT
Music
Download
Comments
tekilt :
AMEN AMEN AMEN
2026-08-11 18:52:17
0
selam :
🙏
2026-08-11 15:43:03
0
Sêrkē ዘ_ክርስቶስ :
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን🥰
2026-08-11 14:24:55
0
merion Getachew :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-11 16:18:08
0
Christina :
🥰🥰🥰
2026-08-11 14:03:56
0
Eyuye :
🥰🥰🥰🙏
2026-08-11 13:43:09
0
asefu41 :
🙏🙏🙏
2026-08-11 10:17:31
0
ሜሎና🕊 :
🥰🥰🥰
2026-08-11 18:05:46
0
To see more videos from user @pazi1221, please go to the Tikwm
homepage.